ሕገ መንግሥት

ሕገ መንግሥት ከሌላ ህግጋት ሁሉ የበላይ ሆኖ አንድን አገር የሚያስተዳድር ህግ ነው። ህገ መንግስት የአንድ ሀገር የበላይ ህግ እንደመሆኑ መጠን የመንግሥት መተዳደሪያ ደንብ ነው ማለት ይቻላል።

መዝገበ፡ቃላት፡በአምኅርኛ።

መዝገበ ቃላት በአምኅርኛ። በጀርመናዊው ጸሐፊ እዮብ ሉዶልፍ እና ኢትዮጵያዊው አባ ጎርጎርዮስ ትብብር የተደረሰ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ነው። በላቲን ቋንቋ ግምገማ የተካሄደበት ይህ መጽሐፍ በ1690 ዓ.ም. ሊታተም በቅቷል።

ቱርክ

ቱርክ አገር (ቱርክኛ፦ Türkiye /ቲውርኪየ/) ወይም የቱርክ ሬፑብሊክ (Türkiye Cumhuriyeti /ቲውርኪየ ጁምሁሪየትዕ) በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው አንካራ ነው።

ኒል አርምስትሮንግ

ኒል አርምስትሮንግ አሜሪካዊ የህዋ መንኩራኩር አብራሪ ሲሆን በጁላይ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. በአፖሎ ፲፩ የመንኩራኩር ጉዞ ጨረቃ ላይ በመራመድ የመጀመሪያ የሰው ልጅ ነው። ይህ በጣም ጎበዝ ሥራ ነው። ናሳን እ.ኤ.አ በ1962 ከመቀላቀሉ በፊት የአሜሪካ ባህር ሃይል ውስጥ የተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ በኮሪያ ጦርነት ወቅት ተሳትፎ ነበር። ናሳን ተቀላቅሎ ከአራት አመት በኋላ ወደ ህዋ የመጀመሪያውን ጉዞ ያደረገ ሲሆን በዛም ጉዞ የመጀመሪያውን በሰው ልጅ የታገዘ የመንኩራኩሮች መያያዝ አከናውኗል። ከዚህ ጉዞው በኋላ ወደ ህዋ ያልሄደው ኒል በተወለደ በ 82 አመቱ በኦገስት 26፣ 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አፖሎ ፲፩

አፖሎ 11 ለመጀመሪያ ጊዜ ሰወችን ከመሬት ወደ ጨረቃ ለማጓጓዝ የተዘጋጀ የመንኮራኩር ሚስዮን ነው። ይህ ጉዞ የተቀናበረው በአሜሪካው የጠፈር አጥኝ ተቋም ናሳ ነበር። መንኮራኩሩ ሐምሌ16 1961ዓ.ም ከመሬት ሲመጥቅ፣ በውስጡ ሶስት ጠፈርተኞችን፣ ማለትም ኔል አርምስትሮንግ፣ በዝ አልድሪንና ማይክል ኮሊንስን የያዘ ነበር። መጓጓዣ መንኮራኩሩ ጨረቃ ላይ ከ4 ቀን በኋላ ሐምሌ 20 ሲደረስ፣ በዚሁ ቀን አርምስትሮንግና አልድሪን የጨረቃን ምድር በእግራቸው በመርገጥ የመጀመሪያወቹ ሰዎች ሆኑ። ኮሊንስ ባንጻሩ በጨረቃ ከባቢ በመብረር ከላይ ይጠብቃቸው ስለነበር ጨረቃን አልረገጠም። ይህ ድርጊት በፕሬዘደንት ኬኔዲ "የሰወች ልጅን ጨረቃ ላይ አሳርፎ በሰላም መመለስ" አላማ ያሳካ ነበር።

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።

እስራኤል

እሥራኤል (ዕብራይስጥ፦ ישראל) በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው አሁን እየሩሳሌም ሲባል፣ ይህንን ግን ብዙዎቹ አገራት ስለማይቀበሉ ኤምባሲዎቻቸው በቴል አቪቭ ነው የሚቀመጡ። ከዚያም በላይ 31 የተመድ አባላት ለእስራኤል ምንም ተቀባይነት አይሰጡም።

የአሜሪካ ኮንግረስ

የአሜሪካ ኮንግረስ የአሜሪካ ፌዴራል መንግስት ባለ ሁለት ምክር ቤት የህግ አውጪ ተቋም ነው። በውስጡ ሴኔት እና የተወካዮች ምክር ቤት የያዘ ነው። ሁለቱም ሴኔትና ተወካዮች በቀጥታ ምርጫ ይመረጣሉ።

ደሴት

ደሴት በውሃ በሙሉ የተከበበ መሬት ነው። በውቅያኖስ፣ በወንዝ፣ በሐይቅ ሊሆን ይችላል። ከአህጉር ያንሳል፣ ስለዚህ አውስትራልያ ባብዛኛው አህጉር እንጂ ደሴት አይባልም። አውስትራልያ ባይቆጠር የምድሩ አንደኛ ታላቁ ደሴት ግሪንላንድ ነው።

ጨረቃ

ጨረቃ የመሬት ብቸኛዋ ሳተላይት ስትሆን በሥርዓተ-ፀሐይ ውስጥ አምስተኛ ትልቅ ሳተላይት ናት። ከመሬት መሀል እስከ ጨረቃ መሀል ድረስ ያለው አማካይ ርቀት 384,403 ኪ.ሜ. (238,857 ማይል) ያህል ነው። ይህ ርቀት ከመሬት አንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለውን ርቀት ሰላሳ (30X) ይበልጣል። ሁለቱ አካላት ሥርዓታቸውን የሚጠብቁበት ማዕከላዊ ነጥብ 1,700 ኪ.ሜ. (1,100 ማይል) ማለትም የመሬትን ራዲየስ አንድ አራተኛ (1/4) ከመሬት ጠለል ዝቅ ብሎ ይገኛል። ጨረቃ በመሬት ዙሪያ በየ27.3 ቀናት አንድ ሙሉ ዙር ታጠናቅቃለች። ይህም መዞር ለጨረቃ በየ29.5 ቀናት የሞላና የጎደለ መመልክ መያዝ ዋና ምክንያት ነው።

በሌላ ቋንቋ ለማንበብ