ፋሲካ

ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።

ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ።

አዲስ ኪዳን ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ በእግዚአብሔር ኃይል ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለፍርድ ቀን በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በክርስትና ወይም በአብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው።

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አማራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።

ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የናይል(ኣባይ) ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው።

ኢየሱስ

ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም አማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው ።

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለትም ከሥላሴ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ

እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።

እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

እየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም አማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው።

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ

እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።

እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

እዩሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም አማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው።

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ

እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።

እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

ዓርብ

ዓርብ የሳምንቱ ስድስተኛ ቀን ሲሆን ከሐሙስ በኋላ ከቅዳሜ በፊት ይገኛል።

ዓርብ በኃይማኖትም ዘንድ ለየት ያለ ዋጋ ካላቸው ቀኖች አንዱ ነው። በክርስቲያኖች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በዕለተ ዓርብ በመሆኑ ለየት ያለ ክብደት ይሰጠዋል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች ዘንድ ከዘመነ ፋሲካ ውጪ ዓርብ የጾም ቀን ነው። ለሙስሊም ወንዶችም ዓርብ ቀትር ላይ በመስጊድ ተገኝቶ የጋራ ጸሎት ማድረግ ግዴታ ነው። በመስጊድ መሰባሰብ ግዴታ አይሁን እንጂ ለሴቶችም የጸሎት ቀን ነው።

የሉቃስ ወንጌል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈው።

ቅዱስ ሉቃስ ሙያው ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለነበረ ወንጌልንም ሲፅፍ ትልቅ ጥንቃቄ እያደረገ ለምሳሌ ከቃሉ ምንጭ ከሆነች ከእመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ዘንድ ድረስ እየሄደ በማነጋገር እንደፃፈ ይነገርለታል። በተጨማሪም የሐዋርያት ሥራን የፃፈ ይሄው ቅዱስ ነው። ከቅዱስ ጳውሎስ ጋርም ብዙ ቦታዎች ላይ ተገኝቷል። እንዲሁም ጌታ ከሙታን ተለይቶ ምትን ድል አድርጎ በተነሣበት ቀን በፍኖተ ኢማሑስ (በኢማሑስ መንገድ) ጌታችን ከተገለጠላቸው ከሁለቱ ደቀመዛሙርት አንዱ ቅዱስ ሉቃስ እንደሆነ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስተምራሉ።

ወንጌላዊው ሉቃስ በላህም ይመሰላል ምክኒያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለዱን በእለተ ልደቱም የከብት እረኞች ከመላእክት ጋር መዘመራቸውን ከሌሎች ወንጌላውያን ሠፋ አድርጐ ስለሚተርክ ነው። (ሉቃ፡፪.፰-፲፰) ከዚህ ሌላ ላህም በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት እንሰሳ ሲሆን ሉቃስም የክርስቶስን መስዋትነት በፍሪዳ ምሳሌ ጽፎአል። (ሉቃ፡፲፭.፳፪-፳፬) ላም የቀንድ ከብት ነው በዚሁም መሠረት ወንጌላዊው ሉቃስ ክርስቶስ ቀርነ መድኃኒት እንደሆነ ነብዩ ዘካርያስ የተናገረውን ትንቢት በመግለጽ ስለፃፈ የላህም ምልክት እንደተሰጠው መተርጉማን ሊቃውንት ይናገራሉ።

ሰዐሊም ነበረ

የሉቃስ ወንጌል

የማቴዎስ ወንጌል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ እንደ ጻፈው ። ከአራቱ ወንጌላት አንደኛው ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን ውስጥ ከሁሉ በፊት ይገኛል። በዕብራይስጥና በአርማይስጥ ቋንቋ ማቴዎስ ማለት ሀብተ አምላክ ወይም የአምላክ ስጦታ ማለት እንደሆነ ይነገራል ። በአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የስም ዝርዝር ውስጥ በሁለተኛውና በሦስተኛው ማለትም በማርቆስና በሉቃስ ወንጌል በተራ ቁጥር ሰባተኛ ሲሆን ስሙም ማቴዎስ በመባል ተመዝግቦአል (ማር.፫:፲፮-፲፱ ፡ ሉቃ.፮:፲፬-፲፮) ።

ራሱ በጻፈው ወንጌልና በሐዋርያት ሥራ ደግሞ በተራ ቁጥር ስምንተኛ ሆኖ ማቴዎስ በመባል ተመዝግቦአል (ማቴ.፲: ፪-፬ ፡ የሐ.ሥ.፩-፲፫) ሌዊ ለሐዋርያነት ከመመረጡ በፊት የተጠራበት ስሙ ሲሆን ማቴዎስ ደግሞ ለወንጌል አገልግሎት በሐዋርያነት ከተጠራ በኋላ የተጠራበት ስሙ ነው ።

የዮሐንስ ወንጌል

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው። ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ይወደው የነበረው የዘብዴዎስ ልጅ ዮሐንስ በፍልስጤም ከፍልስጤምም ውጪ ክርስትና እንድትስፋፋ ያደረገ ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲያገለግላት አደራ የተቀበለ የእመቤታችን የአደራ ልጅ ነው (ዮሐ. ፲፱፡፳፮)።

ከዚህም ጋር ከቅዱስ ጳውሎስ ዕረፍት በኋላ ከኢየሩሳሌም ወደ ኤፌሶን ሄዶ በትንሽዋ እሲያ ወንጌልን የሰበከ በሮማዊው ቄሣር በዶሚቲያኖስ ዘመነ መንግሥት ወደ ፍጥሞ ደሴት ተሰዶ በእስር ቤት ሳለ ራእይን የጻፈ ነው ።

ከዶሚቴያኖስም ሞት በኋላ ወደ ኤፌሶን ተመልሶ " ልጆቼ እርስበርሳቹህ ተፋቀሩ " እያለ ያስተማረ በስሙ የሚጠሩትን ወንጌልን እና ሦስቱን መልዕክታት የጻፈ ንባቤ መለኮት የሚል ስያሜ የተሰጠው ሐዋርያ ነው። ወንጌሉም ጌታ ከዐረገ በኋላ በሠላሳ ወይም በሠላሳ አምስት ዓመት ኔሮን ቄሣር በነገሠ በስምንት ዓመት በየናኒ ቋንቋ ጻፈው በልሳነ ጽርዕ የሚልም አብነት አለ። ከአራቱ ወንጌል መጨረሻ ላይ የተጻፈ ነው።

ፊልጶስ አረባዊ

ፊልጶስ አረባዊ ከ236 እስከ 241 ዓ.ም. ድረስ የሮማ መንግሥት ንጉሠ ነገስት ነበረ።

«አረባዊ» የተባለው ቤተሠቦቹ ከአረቢያ ስለመጡ ነበር። እሱ በ196 ዓ.ም. አካባቢ በሶርያ አውራጃ ተወለደ።

በሮሜ ንጉሥ አሌክሳንድር ሴቬሩስ ዘመን ፊልጶስ የፕራይቶርያን ጠባቂዎች (የንጉሡ ልዩ ዘበኞች ክፍል) አባል ሆነ። በኋለኛውም ንጉሥ በ3ኛ ጎርዲያኖስ ዘመን በ235 ዓ.ም. ፊልጶስ የዘበኞች አለቃ ሆነ። ይኸው ንጉሥ ግን ልጅ ስለ ሆነ፣ ፊልጶስ እንደራሴ የሚመስል ሚና አጫወተ። ከዚህ ትንሽ በኋላ ጎርድያኖስ ሞተና ፊልጶስ በዚያን ጊዜ ንጉሥ ሆነ። በዚያው ጊዜ የሮማ ነገሥታት ሁሉ የተነሡ በሠራዊት ፈቃድነት ነበርና።

ንጉሥ ፊልጶስ ሰላም ከፋርስ መንግሥት ጋር ካዋጀ በኋላ በጀርመናዊ ጎሣዎች ላይ ዘመቻ አደረገ። በየጊዜው ሠራዊቶቹ ጣውንት ንጉሥ በማቆም ያምጹ ነበር፤ ነገር ግን ሳይከናውኑ ቆይተዋል። በ240 ዓ.ም. የሮሜ ሺህኛው አመት በዓል አፈጸመ። ለዚህ በዓል አንድ ሺህ የጨዋታ ወታደሮች (gladiator) እና ብዙ እንስሶች መስዋዕት ሆኑ። በሚከተለው አመት ግን አንዱ ሠራዊት አለቃቸውን ዴቅዮስ ንጉሥ ሆኖ ስላቆሙት፣ ፊልጶስ ከነሱ ጋር ለመታገል ሂዶ ተገደለና ዴቅዮስ የዛኔ ንጉሥ ሆነ።

በኋለኛው ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ዘንድ፣ ንጉሥ ፊልጶስ አንድ ጊዜ ፋሲካ በዓል ለማስታወስ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ። ሳይገባም ጳጳሱ ንስሐ እንዲገባ አደረጉት ተባለ። ከዚህ በላይ በየወቅቱ በክርስትያኖች ላይ የተካሄዱት እልቂቶች በፊልጶስ ዘመን የተቋረጡ ይመስላል። ስለዚህ ይህ ንጉሥ ምናልባት የሮማ የመጀመርያው ክርስቲያን ንጉሥ ባይሆንም እንኳን የክርስትና ተቆርቋሪ ሊባል ይቻላል ባዮች አሉ። ሆኖም በዘመኑ በወጡ መሐለቆች መሠረት እምነቱን ከሮማ አረመኔ ሃይማኖት መቸም የቀየረ አይመስልም።

ፋሲካ ደሴት

ፋሲካ ደሴት (እስፓንኛ፦ Isla de Pascua /ኢስላ ዴ ፓስኩዋ/፤ ኗሪ ስም /ራፓ ኑዊ/) በፓሲፊክ ውቅያኖስ ውስጥ የሚገኝ የቺሌ ደሴት ነው።

ፖሊኔዥያ

ፖሊኔዥያ በኦሺያኒያ የሚገኝ የደሴቶች አውራጃ ነው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.