ድንጋይ ዘመን

ድንጋይ ዘመን በ«ሦስቱ ዘመናት» አስተሳሰብ ከናስ ዘመን አስቀድሞ የነበረው ዘመን ነው። በአጠቃላይ እንደ ተለመደ ከ3125 ዓክልበ. ያህል በፊት ያመልክታል። በዚህ ዘመን አብዛኞቹ መሣርያዎችና እቃዎች የተሠሩ ከድንጋይ ነበር።

ናስ ጥቅም በጥንታዊ ግብጽ ከ3125 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ይታወቅ ነበር። ይህም ደግሞ በአለም ላይ የጽሑፍ መጀመርያ ወቅት ስለነበር፣ የታሪክ መጀመርያ ደግሞ ይባላል። እንግዲህ የ«ድንጋይ ዘመን» እና የ«ቅድመ-ታሪክ» ትርጉም አንድላይ ሊሆን ይችላል።

የዚህ አከፋፈል ዋጋ አጠያያቂ ነው። በብዙ ቦታዎች የናስና የብረት ዕውቀት የገቡት በአንድ ጊዜ ነበረ። ለምሳሌ በስሜን አሜሪካ በኩል፣ አውሮፓውያን 1500 ዓም ያህል ሳይገቡ ኗሪዎቹ የብረታብረት ቀለጣ እንደነበራቸው አይታስብም፤ ከተደቀደቀ መዳብወርቅብር በቀር ብዙ የብረታብረት እቃዎች አላወቁም ነበር። የመዳብና የነሐስ ቀለጣ ግን በደቡብ አሜሪካ ይታወቅ ነበር፣ ከ800 ዓም ግድም ጀምሮ በመካከለኛ አሜሪካ ደግሞ ይታወቅ ነበር።

ታሪክ

ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል። ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ-ታሪክ ይባላል።

በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም «ቅድመ-ታሪክ» ነው።

በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት አጠያያቂ ተብለዋል። ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል።

ከግብጽ ጥንታዊ መንግሥት ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የኩኔይፎርም ጽሑፍ መዝገቦች ከመስጴጦምያ ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የቻይና መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1200 ዓክልበ. በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1600 ዓክልበ. በፊት የነበረውንም የሥያ ሥርወ መንግስት የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ «አፈ ታሪክ» ሊባል ይችላል።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.