የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ

የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ (ቻይነኛ፦ 中華人民共和国 /ጆንግኋ ሬንሚን ጎንግሄጐ/)በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው ቤጂንግ ነው። በአገሪቱ ውስጥ 1.404ቢሊዮን ሕዝብ ይኖራል። ይህም ከሁሉም አገራት በላይ ነው።

ደግሞ ይዩ፦ ቻይና

የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ
中华人民共和国

የቻይና ሰንደቅ ዓላማ የቻይና አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር "义勇军进行曲"

የቻይናመገኛ
ዋና ከተማ ቤጂንግ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ቻይንኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ሪፑብሊክ ሶሻሊስት
ዢ ጂንፒንግ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
9,596,961 (3ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት
 
1,373,541,278
ሰዓት ክልል UTC +8
የስልክ መግቢያ 86
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .cn
ሁ ጂንታው

ሁ ጂንታው ከ1995 እስከ 2005 ዓም ድረስ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ነበሩ።

ሃይናን

ሃይናን (ቻይንኛ፦ 海南 ወይም /ሓይናም/) በደቡብ ቻይና ባሕር የሚገኝ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ታላቅ ደሴትና ክፍላገር ነው።

የሃይናን ትርጉም «ከባሕር ደቡብ» ነው። የሃን ቻይናውያን ሰዎች ከ118 ዓክልበ. ጀመሮ ሠፈሩበት። አሁን 84% ይቆጠራሉ። ከነርሱ ቀድሞ የኖሩበት ኗሪዎች ሊ ብሔር ወደ ደቡብ ይገኛሉ፣ 15% ናቸው። የሁላቸው መደበኛ ቋንቋ ፑቶንግኋ ቻይንኛ ሲሆን፣ ቻይናውያን ደግሞ ሚንኛ (ሃይናንኛ)፣ ሊ ብሔርም ደግሞ ሕላይኛ ይናገራሉ። ባብዛኛው የደሴት ኗሪዎች የቡዲስም ምዕመናን ሲሆኑ፣ አንዳንድ እስላም ወይም ክርስቲያን ይገኛሉ። ዋናው ሰብል ሩዝ፣ ከዚያም ኮኮነት ዘምባባ፣ ቃጫ፣ አናናስ፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ሻይ፣ ቡና፣ ሸንኮራ አገዳ፣ ጎማ ዛፍ ሁሉ ይታረሳሉ። የሃይናን ቢጫ ፋኖስ ሚጥሚጣ ለሃይናን ደሴት ብርቅዬ የቻይና ሚጥሚጣ አይነት ነው። ለማዳ እንስሶች በተለይ ፍየል፣ በሬ፣ የውሃ ጎሽ፣ ዶሮ፣ ዚዪ፣ ዳክዬ አላቸው።

ሃይናን በጣም ትልቅ የቱሪስም መድረሻ ሆኗል፤ በቅርብም የቻይና መንግሥት መላው ክፍላገሩ «ዓለም አቀፍ ነጻ ንግድ ክልል» እንዲሆን ለማድረግ እያቀደ ነው።

የሃይናን ባህል ስለ አበሳሰሉ ይታወቃል፤ በተለይ የበግ፣ ሠርጣን፣ ዳክዬ፣ ዶሮ፣ ዚዪ፣ አሳ፣ አሳማ አሠራሮች አላቸው። «የሃይናን ዶሮ በሩዝ» የሚል አሠራር በመላው ደቡብ-ምሥራቅ እስያ በተለይም በሲንጋፖር የተወደደ ሆኗል።

በሃይናን ደሴት ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ አትክልትና እንስሳት ዝርዮች አሉበት። በተለይም

ከአትክልት፦

የሃይናን ቢጫ ፋኖስ ሚጥሚጣ የCapsicum chinense አይነት

የሃይናን ነጭ ጥድ Pinus fenzeliana

የሃይናን ዝግባ Cephalotaxus hainanensisከእንስሳት፦

የሃይናን ጸጉራም ትድግ Neohylomys hainanensis

የሃይናን ቆቅ Arborophila ardens

የሃይናን ጣዎስ Polyplectron katsumatae

የሃይናን ጥቁር-ጉትያ ጊቦን ጦጣ Nomascus hainanus

የሃይናን መንትሌ Lepus hainanus

የሃይናን ነብር-ድመት Prionailurus bengalensis alleni የነብር-ድመት ንዑስ ዝርያ ነው።

የሃይናን ቅጠል ተንጫጪ ወፍ Phylloscopus hainanus

ማርክሲስም-ሌኒኒስም

ማርክሲስም-ሌኒኒስም በተለይ በካርል ማርክስና በቭላዲሚር ሌኒን ትምህርት የተመሠረተ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነው።

ማርክሲስም-ሌኒኒስም የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና በመሆኑ፣ በሃይማኖት ፈንታ እንደ የመንግሥት ሃይማኖት ያህል ያለ ሚና አጫውቷል።

በአሁኑ ሰዓት በይፋ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ያላቸው አገራት የሚከተሉ ናቸው፦

ቬትናም - ከ1937 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1982 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «የሆ ቺ ሚን ሃሣብ» ተብሏል።

የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ - ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1970 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «ሶሻሊስም ከቻይናዊ ጸባይ ጋራ» ተብሏል።

ኩባ - ከ1951 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።

ላዎስ - ከ1967 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።

ስሜን ኮርያ - ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ በይፋ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1964 ዓም ጀምሮ ከማርክሲስም የተደረጀው ርዕዮተ ዓለም «ጁቼ» ኰሙኒስም ተብሏል። በ1983 ዓም ደግሞ «ማርክሲስም» በይፋ ተተወ።ርስት ሁሉ የመንግሥት መሆኑ እንጂ የግል ርስት አለመኖሩ የሚገኝበት ሁናቴ የጀርመን ፋላስፋ የካርል ማርክስ ፍልስፍና ውጤት ነው። በተጨማሪ ማርክስ የሃይማኖት ወዳጅ ባለመሆኑ መጠን፣ ባለፈው ጊዜ በማርክሲስም-ሌኒኒስም በተገዙት አያሌ አገራት ውስጥ የሃይማኖት ወይም የኅሊና ነጻነት አልተገኘም።

በካርል ማርክስም ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽጉ መቆጣጠር የመንግሥት ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ «ለሴ ፈር» ከ«ካፒታሊዝም» ጽንሰ ሀሣብ ጋር ይዘመዳል።

ማው ፀ-ቶንግ

ማው ፀ-ቶንግ (ቻይንኛ፦ 毛泽东፣ በፒንዪን፦ Māo Zèdōng) (1886 -1968 ዓም) ከ1942 እስከ 1968 ዓ.ም. ድረስ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ዋና መሪና አለቃ (ሊቀ መንበር) ነበር።

ምስራቅ እስያ

ምስራቅ እስያ የእስያ ክፍል ሲሆን በተለምዶ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፣ የቻይና ሪፐብሊክ፣ ጃፓን፣ ሞንጎሊያ፣ ስሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ ማለት ነው።

ሢንጅያንግ

ሢንጅያንግ ዊግር ራስ-ገዥ ክልል የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ክፍላገር ነው።

ሺ ጂንፒንግ

ሺ ጂንፒንግ ከ2005 ዓም ጀምሮ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ናቸው።

Liu Xiaobo

አረናቸል ፕረዴሽ

አረናቸል ፕረዴሽ በስሜን ምሥራቅ የምትገኝ የሕንድ ክፍላገር ናት።

የቻይና መንግሥታት ደግሞ በግዛቱ ላይ ይግባኝ ማለት ጥለዋልና ለአጭር ወራት በ1955 ዓም የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሥራዊት በጦርነት ያዘው። ከጦርነቱ በኋላ ግን ወደ ሕንድ ተመለሰ።

እግር ኳስ ለወዳጅነት

እግር ኳስ ለወዳጅነት በ PJSC Gazprom የሚተገበር ዓመታዊ የአለምአቀፍ የልጆች ማህበራዊ ፕሮግራም ነው። የፕሮግራሙ ግብ በወጣቱ ትውልድ ላይ በእግር ኳስ በኩል የጤናማ አኗኗር አስፈላጊ እሴቶችን እና ፍላጎትን ማስረጽ ነው። በፕሮግራሙ መዋቅር ውስጥ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ዕድሜያቸው 12 ዓመት የሆኑ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በዓመታዊ የአለምአቀፍ ልጆች መድረክ፣ የ«እግር ኳስ ለወዳጅነት» አለም ዋንጫ፣ አለምአቀፍ የእግር ኳስ ቀን እና የጓደኝነት ላይ ይሳተፋሉ ።

የ ዓለምአቀፍ ፕሮግራሙ አስተባባሪ AGT Communications Group (ሩሲያ)

ኰሙኒስም

ኰሙኒስም በፖለቲካ ወይም [[ኅብረተሠብ ጥናት ማለት የምረታ ባለቤትነት ሁሉ የጋራ እንዲሆን የሚጥረው ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም፣ ፍልስፍናና እንቅስቃሴ ነው። ቃሉ ከሮማይስጥ /ኮሙኒስ/ «የጋራ» ደርሷል።

በአለማችን የታወቀው ኰሙኒስም ማርክሲስም-ሌኒኒስም ሲሆን የኰሙኒስት ርዕዮተ-አለም ካሉት አምስቱ መንግሥታት አራቱ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ናቸው። እነርሱም ቬትናም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ፣ ኩባ፣ እና ላዎስ ናቸው። አምስተኛው ወይም ስሜን ኮርያ «ጁቼ ኰሙኒስም» የተባለው ርዮተ አለም ሲኖረው ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ እርሱ ደግሞ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ይባል ነበር፤ እንዲሁም በርካታ ሌሎች አገራት ከ1983 አስቀድሞ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆነው ነበር። ሆኖም ብዙ ጊዜ የማርክስ መርሆች በተግባር ወደ እውነትኛ ኰሙኒስም ወይም ለሕዝቡ ጸጥታና ደኅንነት ሳይሆን ወደ ግፍና አምባገንነት ይመሩ ነበር።

የቻይና ቀለብቶና መንገድ እቅድ

የቻይና ቀለብቶና መንገድ እቅድ ወይም በሙሉ «የሐር መንገድ ምጣኔ ሀብት ቀለብቶና የ21ኛው ክፍለ ዘመን ባህራዊ ሓር መንገድ» የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ያመነጨው የእስያ፣ አውሮፓና አፍሪካ ምጣኔ ሀብቶች በየብስም ሆነ በባሕር ላይ ለማጠናከር ያለው እቅዱ ነው።

በዚህ እቅደ በዋናነት የተፈጸመው ሥራ የቻይና መንግሥት ከፓኪስታን አንዱን ወደብ፣ ጓደር ወደብን በመከራየቱ ነው። ይህም ባለፈው ዘመን ቻይና ሆንግ ኮንግን ለዩናይትድ ኪንግደም፣ ማካውን ለፖርቱጋል ወዘተ. ለመቶ ዓመታት ያህል እንደ ማከራየቱ ነው።

የቻይና እግር ኳስ ማህበር

የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ ማህበር ወይም የቻይና እግር ኳስ ማህበር የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1924 እ.ኤ.አ. በቤዪጂንግ የተመሠረተ ሲሆን የፊፋ አባል የሆነው በ1931 እ.ኤ.አ. ነው። ከየቻይና የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ እንደገና በ1955 እ.ኤ.አ. የተቋቋመ ሲሆን፣ በ1979 እ.ኤ.አ. እንደገና የፊፋ አባል ሆኗል።

የኅሊና ነፃነት

የኅሊና ነፃነት ማለት ማንኛውም ግለሠብ ምንምን ሀሣብ፣ እምነት ወይም አስተያየት በጽናት ለመያዝ የሚረጋገጥበት ነጻነት ነው። የሌላ ሰዎች እምነት ምንም ቢሆንም፣ ይህ ነጻነት ለየግለሠቡ ጽኑእ ሆኖ ይቆጠራል።

ጨረቃ

ጨረቃ የመሬት ብቸኛዋ ሳተላይት ስትሆን በሥርዓተ-ፀሐይ ውስጥ አምስተኛ ትልቅ ሳተላይት ናት። ከመሬት መሀል እስከ ጨረቃ መሀል ድረስ ያለው አማካይ ርቀት 384,403 ኪ.ሜ. (238,857 ማይል) ያህል ነው። ይህ ርቀት ከመሬት አንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለውን ርቀት ሰላሳ (30X) ይበልጣል። ሁለቱ አካላት ሥርዓታቸውን የሚጠብቁበት ማዕከላዊ ነጥብ 1,700 ኪ.ሜ. (1,100 ማይል) ማለትም የመሬትን ራዲየስ አንድ አራተኛ (1/4) ከመሬት ጠለል ዝቅ ብሎ ይገኛል። ጨረቃ በመሬት ዙሪያ በየ27.3 ቀናት አንድ ሙሉ ዙር ታጠናቅቃለች። ይህም መዞር ለጨረቃ በየ29.5 ቀናት የሞላና የጎደለ መመልክ መያዝ ዋና ምክንያት ነው።

የጨረቃ ከአንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለው ርቀት 3,474 ኪሜ (2,159 ማይል) ሲሆን ከመሬት ተመሳሳይ አንድ አራተኛ (1/4 X የመሬት ዲያሜትር) በትንሽ ይበልጣል። የመሬትን አንድ አራተኛ ስፋት ሲኖራት ይዘቷ (volume) ግን የመሬትን ሁለት በመቶ (2%) ብቻ ነው። የጨረቃ ስበት የመሬት ስበትን አስራ ሰባት በመቶ (17%) ጋር ይነጻፀራል።

ጨረቃ የሰው ልጅ ያረፈባት ብቸኛዋ የጠፈር አካል ናት።

በ2011 የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሳይንቲስቶች ሮቦቶችን ወደ ጨረቃ ልከው የጎመንዘር አይነት (Brassica napus)፣ የድንችና የጥጥ ዘሮችን በጨረቃ ላይ በመያያዣ ውስጥ ማብቀል እንደተቻለ አስረዱ። ወደፊት ሰዎች ወደ ጨረቃ ቢመልሱ ኖሮ፣ በነዚህ ሦስት ምርቶች፦ ጎመንዘር ለዘይት፣ ድንች ለምግብ፣ ጥጥም ለልብስ፦ እንደሚረዷቸው አሉ። እንዲሁም የድንጋይ ፌጦ (Arabidopsus spp)፣ እርሾና የፍራፍሬ ዝንብ በሙከራው ውስጥ እየታደጉ ነበር። ሆኖም ከ፫ ቀን በኋላ ናሙናዎቹ ሁሉ ከጨረቃ አየር ሙቀት የተነሣ በርደው አርፈው ነበር።

እስያ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
Asia (orthographic projection)

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.