ኦሪት ዘጸአት

ኦሪት ፡ ዘጸአትመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳንና የኦሪት ሁለተኛው መጽሐፍ ነው። ስለ ሙሴ ልደት፣ እብራውያን ከጌሤም ወደ ሲና ልሳነ ምድር በተአምራት እንዳመራቸውና አስርቱ ቃላትሕገ ሙሴንም እንደ ሰጣቸው ይገልጻል።

ሌዊ

ሌዊ (ዕብራይስጥ፦ לֵּוִי‎ /ለዊ/) በብሉይ ኪዳን ዘንድ ከያዕቆብ ፲፪ ወንድ ልጆች አንዱ ሲሆን ከእስራኤል ፲፪ ነገዶችም የሌዋውያን አባት ነበረ።

ሌዊ ከሮቤልና ከስምዖን በኋላ የያዕቆብና የልያ ፫ኛው ልጅ ነበር፤ በፓዳን-አራም ተወለደ። በኦሪት ዘፍጥረት ፴፬፡፳፭፣ ቤተሠቡ በከነዓን ሲኖር ስምዖንና ሌዊ ስለ እኅታቸው ዲና የሴኬም ባላባት ኤዊያዊው ኤሞርን አሸነፉ፣ የሴኬምን ሠፈር አጠፉ። ስለዚህ አባታቸው ያዕቆብ ገሰጻቸው (፴፬፤፴)።

የሌዊ ወንድ ልጆች ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ተባሉ፤ እነዚህ ሁሉ ወደ ጌሤም ፈለሱ። በኦሪት ዘኊልቊ ፳፮፡፶፱ ሴት ልጁን ዮካብድን ይጠቅሳል፤ እርስዋም የቀዓት ልጅ እንበረም አግብታ አሮንን፣ ማርያምንና ሙሴን ወለደች።

በያዕቆብ በረከት ኑዛዜ (ኦሪት ዘፍጥረት ፵፱፡፭-፯) ሌዊ ግን ከወንድሙ ስምዖን ጋር ይረገማል፦

«ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው፤ ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው። በምክራቸው፣ ነፍሴ፣ አትግባ፤ ከጉባኤአቸውም ጋር፣ ክብሬ፣ አትተባበር፤ በቊጣቸው ሰውን ገድለዋልና፣ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና። ቊጣቸው ርጉም ይሁን፣ ጽኑ ነበርና፤ ኲርፍታቸውም፣ ብርቱ ነበርና፤ በያዕቆብ አከፋፍላቸዋለሁ፣ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።»ኦሪት ዘጸአት ፮፡፲፮ የሌዊ ሕይወት ዘመን ፻፴፯ ዓመታት እንደ ነበር ይነግረናል። በኋላ ዘሮቹ ሌዋውያን ከከነዓን የራሳቸውን ርስት አልተቀበሉም፣ ነገር ግን የካህናት መደብ ሆነው በነገዶቹ መካከል ተበተኑ።

በሙሴም በረከት ኑዛዜ (ኦሪት ዘዳግም ፴፫፡፰-፲፩)፣ ሙሴ ስለ ነገደ ሌዊ እንዲህ ይላል፦

«ቱሚምህና ኡሪምህ ለቅዱስህ ሰው ነው፣ በማሳህ ለፈተንኸው፣ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፣ ስለ አባቱና ስለ እናቱ፦ አላየሁም ላለ፣ ወንድሞቹንም ላላስተዋለ፣ ልጆቹንም ላላወቀ፤ ቃልህን አደረጉ፣ ቃል ኪዳንህንም ጠበቁ። ፍርድህን ለያዕቆብ፣ ሕግህንም ለእስራእል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣንን፣ በመሥዊያህም የሚቃጠል መሥዋዕት ይሠዋሉ። አቤቱ፣ ሀብቱን ባርክ፣ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፣ የሚጠሉትም አይነሡ።»በትንቢተ ሚልክያስ ፪፡፬-፮፣ እግዚአብሔር ካህናቱ (ሌዋውያን) ስለ ሌዊ ጽድቅ እንደ ተመረጡ ይገልጻል፦ «ቃል ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ትእዛዝ እንደ ሰደድሁላችሁ ታውቃላችሁ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና ሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፤ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፣ እርሱም ፈራኝ፣ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ። የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፣ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፣ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፣ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ።»

በመጽሐፈ ኩፋሌ መሠረት፣ ሌዊ በ2127 ዓ.ዓ. ተወለደ። ኩፋሌ ፳፩፡፲፱ እንዲህ ይላል፦

«እነርሱም በእውነተኛነት እንደ ተቈጠሩ የሌዊም ልጅ ለክህነት እንደ ተመረጠ፣ እኛ (መላዕክት) በዘመኑ ሁሉ እንዳገለገልን፣ ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ዘንድ እንደ ተመረጡ እይ። እውነት ነገር ይሠራ ዘንድ ፍርድንም ይፈርድ ዘንድ በእስራኤል ላይ በጠላትነት ከሚነሡ ብድራትን ይመልስ ዘንድ ቀንቶአልና ሌዊ ይክበር ልጆቹም ለዘላለም ይክበሩ።»በዚህ መጽሐፍ ፳፪፡፲፪-፲፮፣ ያዕቆብ ሌዊን ባረከው እንጂ አልረገመውም። በ፳፪፡፴፬፣ «ሌዊም እንደ ሾሙት፣ ለልዑል አምላክም እርሱን አገልጋይ እንዳደረጉት፣ ልጆቹንም እስከ ዘላለም ድረስ አገልጋይ እንዳደረጉአቸው ሕልም አየ።» ያንጊዜ አባቱ ያዕቆብ ሌዊን ቄስ አደረገው። በኩፋሌ ፳፬፡፳፮ የሌዊ ሚስት ስም ሜልካ ተባለ፣ «ከቃራ (ወይም በሌሎቹ ቅጂዎች ታራ) ልጆች ወገን ከሚሆን ከአራም ልጆች የተወለደች»።

በኋላ ዘመን ያዕቆብ በጌሤም በምድረ ግብፅ ባረፈው ወቅት፣ የአባቶቹን መጻሕፍት ሁሉ የወረሰው ሌዊ ሆነ (ኩፍ. ፴፪፡፱)።

ሕገ ሙሴ

ሕገ ሙሴ በብሉይ ኪዳን ዘንድ ከአስርቱ ቃላት ቀጥሎ ከኦሪት ዘጸአት ፳፩ ጀምሮ የሚገኝ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ለሙሴ የገለጸው ሕግ ነው።

የእስራኤል ልጆች በዘፈንና በወርቃማ ላም ጣኦት ከተገኙ በኋላ፣ ያህዌ የከበደ ሕግ ሰጣቸው። የሕዝቡ ዘር ለተነበዩ በረከቶች እንዲዘጋጅ፣ ለሙሴ ዘመን የተመጣጠነ ሕግ እንዲሆን፣ የሰው ልጆችን በመቸኰል ሳይሆን በመታገሥ ወደ ሥልጣኔ እንዲያስለምዳቸው፣ ከጎረቤቶቹ ከመስጴጦምያ አገሮች ሕግጋት የተሻሸሉ ብያኔዎች እንደ ወሰነ ሊታይ ይቻላል። ከሕገ ሙሴ (ምናልባት 1661 ዓክልበ. የተገለጠ) አስቀድሞ ከወጡት ሕገጋት በተለይ ተመሳሳይ ኹኔታዎች የቆጠሩት የኡር-ናሙ ሕግጋት (1983 ዓክልበ.)፣ የሊፒት-እሽታር ሕግጋት (1832 ዓክልበ.)፣ የኤሽኑና ሕግጋት (1775 ዓክልበ. ግድም) እና የሃሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ.) ይታወቃሉ።

በታሪካዊ ልማዶች ዘንድ፣ የአክሱም መንግሥት ግማሽ ከ950 ዓክልበ. ግድም እስከ 317 ዓ.ም. ድረስ ደግሞ በሕገ ሙሴ ሥር ነበረች። እንዲሁም በአይሁድ መንግሥታት ለምሳሌ የስሜን መንግሥት (317-1619 ዓም) እና ኻዛሪያ (ከ732-1008 ዓም ግድም) ተገኘ።

በትንቢተ ሚክያስ 6:8 መሠረት በሕጉ በድምሩ አስፈላጊ የሆኑት ፫ ጽንሰ ሀሣቦች ፍርድ፣ ምኅረትና ትሕትና ናቸው።

ወደ ፊትም ከሕገ ሙሴ መሠረት ሕገ ወንጌልና በሕገ ወንጌል የተመሠረቱ ሕግጋት (ለምሳሌ እንደ ፍትሐ ነገሥት) ተደረጁ። በኢየሱስ ትምህርት፣ ከሁሉ ትልቁ ሕግ ኦሪት ዘዳግም ፮፡፭ «አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ» የሚለው ሲሆን፣ ሁለተኛው ትልቁ ኦሪት ዘሌዋውያን ፲፱፡፲፰ «ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ» ነው። አለበለዚያ በሃዋርያት ሥራ ፲፭፡፳፱ ዘንድ፣ ከሕገ ሙሴ ለክርስቲያናት አጥብቀው መጠበቅ ያሉባቸው ደንቦች (ቅጣቶቹም ባይሆኑም) «ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደምም፣ ከተናቀም (ከመብላት)፣ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ» የሚሉት ናቸው። የተረፉት የአይሁዶች ሕግጋት ግን ለማጥናትና ለማወቅ ለብዙ ክርስቲያናት ቁም ነገሮች ናቸው።

መጽሐፈ ኩፋሌ

መጽሐፈ ኩፋሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት አንዱ ነው። በሌሎቹ አብያታ ክርስትያናት ግን ዛሬ የማይቀበል መጽሐፍ ወይም ሲውዴፒግራፋ ይባላል። ነገር ግን ለቀድሞው የቤተ ክርስቲያን አበው ታውቆ የጥቅስ ምንጭ ሆነላቸው። የመጽሐፉ ግሪክ ትርጉም የሚታወቀው ከቅዱስ ኤፒፋንዮስ ጥቅሶች ባቻ ሳይሆን እንዲሁም በዩስቲን ሰማዕት፣ በኦሪጄን፣ በዲዮዶሮስ ዘአንጥያክያ፣ በኢሲዶር ዘሰቪላ፣ በአሲዶር ዘእስክንድርያ፣ በዩቲክዮስ (አቡነ እስክንድርያ)፣ በዮሐንስ ማላላስ፣ በጊዮርጊስ ሱንኬሎስና በቄድሬኖስ ጥቅሶች በከፊል ይታወቃል።

ሆኖም መጽሐፉ በአይሁድ ሳንሄድሪን ከ1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት አልተቀበለም ነበር። አንዳንድ ክፍል በቁምራን ዋሻ በ1939 ዓ.ም. እስከተገኘ ድረስ፣ የመጽሐፉ ዕብራይስጥ ትርጉም በሙሉ ጠፍቶ ነበር። ስለዚሁ ሁኔታ (የዕብራይስጥ ትርጉም በማጣት) መጽሐፉ በኋላ ዘመን በሮማ ቤተ ክርስቲያን አለቆች አልተቀበለም። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ እንዲሁም በቤተ እስራኤል አይሁዶች ዘንድ፣ መጽሐፉ በግዕዝ ስለ ተገኘ እስከ ዛሬ ድረስ ቅዱስ ተብሎ ተከብሯል።

መጽሐፉ እንደሚለው መላእክት የዓለሙን ታሪክ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ኦሪት ዘጸአት ድረስ (2,410 ዓመታት ሲቆጠሩ) ለሙሴ በደብረ ሲና ይተርካሉ። ዘመናት በኢዮቤልዩ ወይም በ49 ዓመታት ይከፋፈላሉ። ኢያንዳንዱ ኦዮቤልዩ 7 ሱባዔ ወይም የዓመት ሳምንት (7 አመት) ነው። ከማየ አይህ አስቀድሞ ደቂቃ ሴት ከእግዚአብሔር አምጸው ወደ ቃየን ልጆች እንደ ሔዱና እንደ ከለሱ ይላል። ክልስ ልጆቻቸውም ክፉ ረጃጅሞች (ናፊሊም) ሆነው በማየ አይህ ጠፉ። ከዚህ በኋላ የኖህን ልጆች አሳቱ። ጣኦት ሠሩ፣ መንግሥት አጸኑ፣ የኖህ ልጆች ምድርን ሁሉ ያካፈላሉ፣ የባቢሎን ግንብ ከወደቀ ቀጥሎ ወደ ርስቶቻቸው ተበተኑ። መላእክትም ለአብርሃም ቅዱስ ቋንቋን አሳውቁት።

ከተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውጭ እንደ «ሲውደፒግራፋ» በመቆጠሩ አንዳንድ ሊቃውንት በ150 ዓክልበ. ገደማ እንደ ተሠራ ይገምታሉ። ለዚሁ አስተሳሰብ ግን ምንም ማስረጃ አልተገኘም።

ሙሴ

ሙሴ (ዕብራይስጥ፡ מֹשֶׁה /ሞሼህ/) በብሉይ ኪዳን ከሚጠቀሱት ታላላቅ ነብያት አንዱ ነው። ሙሴ በተወለደበት ዘመን የእስራኤል ልጆች በግብጽ ውስጥ በባርነት ተገዝተው የነበርበት ሆኖም ግን ቁጥራቸው እየበዛና እየተጠናከሩ የነበርበት ጊዜ ነበር።

በዚህ ዘመን ግብፅን ያስተዳድር የነበር፣ ስሙ በብሉይ ኪዳን ያልተጠቀሰው የግብፅ ፈርዖን፣ የእስራኤል ልጆች ከውጭ የግብፅ ጠላቶች አግዘው ሊወጉን ይችሉ ይሆናል በሚል ፍራቻ ማናቸው የእስራኤል ወገን የሆኑ ወንድ ልጆች በተወለዱ ጊዜ እንዲገደሉ አዘዘ። ሆኖም የሙሴ እናት፣ ዮካብድ፣ ልጇን ደብቃ ታኖር ነበር። ከሶስት ወር ድበቃ በኋላ ልጁን በደንገል ሳጥን አድርጋ በአባይ (ናይል) ወንዝ አጠገብ አስቀመጠችው። ሳጥኑ እየተንሳፈፈ የፈርዖን ልጅ እምትታጠብበት ስፍራ ደረሰ፣ የፈርዖንም ልጅ ለህጻኑ ስላዘነች በፈርዖን ቤት አደገ።

ማጫ

ማጫ በጥንት በየትም አገር አሁንም በብዙ ኅብረተሠቦች የሚገኝ የጋብቻ ልማድ ወይም ሕግ ነው።

እንበረም

እንበረም (ዕብራይስጥ፦ ዐምራም፣ አረብኛ፦ ዒምራን) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የሙሴ፣ የአሮንና የማርያም አባት ነበረ። ኦሪት ዘጸአት ስለ እንበረም ጥቂት መረጃ ቢገኝም፣ በመጽሐፈ ኩፋሌ፣ በቁራንና እንዲሁም በሌሎች ምንጮች ተጨማሪ ልማዶች አሉ።

እጸ ፋርስ

እጸ ፋርስ (Cannabis sativa) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም የሚገኝ ተክል ነው።

በአንዳንድ ምንጭ ኣጠፋሪስ ወይም አስተናግርት ደግሞ «እጸ ፋርስ» ተብሏል፤ ይህ በፍጹም ሌላ ዝርያ (Datura stramonium) ነው። C. sativa ደግሞ ቃጫ ተብሏል፣ ይህም ለሌላ ዝርያ (Agave sisalana) ይገባል።

ፋሲካ

ፋሲካ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል የተነሳበትን የትንሳዔ ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።

ስሙ ፋሲካ የመጣው ከአረማይክ /ፓስኻ/፣ ግሪክኛ /ፓስቃ/፣ ዕብራይስጥ /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ የአይሁድ ፋሲካ በዓል ዕብራውያን በሙሴ መሪነት ከግብፅ ፈርዖን ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘጸአት ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ፋሲካ ከዚያው ቃል ደረሰ።

በአዲስ ኪዳን ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በመጨረሻው እራት ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ በእግዚአብሔር ኃይል ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለፍርድ ቀን በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በክርስትና ወይም በአብያተ ክርስቲያናት በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.