እግዚአብሔር

እግዚአብሔርግዕዝ ቋንቋ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም እግዚእ ማለት ገዢ ወይም ጌታ ሲሆን፤ ብሔር ማለት ደግሞ የሰው ስብስብ ወይም አገር ማለት ነው። የተሟላ ትርጉም ፡ የብሔር ገዢ ከሁሉ በላይ የሆነ ፡ ዓለምን የፈጠረ ፡ ብቸኛ አለቃ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጻፉት በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን የመጀመሪያው ክፍል በዕብራይስጥና በአረማይክ እንዲሁም የኋለኛው በግሪክ መሆኑ ይታወቃል። እግዚአብሔር በሚለው የግዕዝ ቃል የተተካው ስም በዋነኞቹ እና በመጀመሪያዎቹ ቅጅዎች የፈጣሪን ስም የሚወክሉት አራት የእብራይስጥ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ የነበረ ሲሆን አጠራራቸውም ዮድ ሄ ዋው ሄ ነው። በቀድሞ ዘመን ተነባቢዎች ብቻ የሚጻፉ ሲሆን አናባቢዎችን የሚጨምረው አንባቢው በመሆኑ በዘመናችን የእነዚህን አራት ፊደላት ትክክለኛ አነባበብ በእርግጠኛነት የሚያውቅ የለም። ሆኖም ወደ ትክክለኛው በእጅጉ የሚቀርቡ ሁለት የአማርኛ አጠራሮች ይገኛሉ። እነሱም ይሖዋ እና ያህዌህ የሚሉት ሲሆኑ በ1879 የአማርኛ ትርጉም መፅሓፍ ቅዱስ አንድ ጊዜ (ይሆዋ)፣ በ1941 ትርጉም ሁለት ጊዜ (ያህዌ) አንዲሁም በአዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅግ በርካታ ቦታ ላይ (ያህዌ) በሚል ተጽፈው ይገኛሉ።

ግዕዝ ፍልስፍና B-H-R (𐩧𐩢𐩨) የሚለው ሥር ብሔር ወይም ባሕር ከመስጠት በላይ ትርጉሙ ማናቸውም ባሕር ዓይነት፣ የዓለም፣ የሀሣብ፣ የድምጽ፣ የጠፈር፣ ወይም የመንፈስ ባሕር ቢሆን፤ ባሕሩ የባሕሩም ክፍሎች ሁሉ ወሰኖች እንዳሉባቸው በቀላል ሊገለጽ የሚችል ነው። እንግዲህ ወሰኖቹን የሚወስነው አወሳኝ ወይም ገዢው ኃይል «ብሔሩን የሚገዛ» ወይም በግዕዝ «እግዚአብሔር» በመባል ሊታወቅ ይቻላል። ይህ ላይኛ ፈቃድ ፈጣሪው ጸባይ የሰማዩ አባታችን ሲሆን ያለ እርሱ ረድኤት ምንም አለመቻሉን የሚል ግንዛቤ ነው። ስለዚህ የማናቸውም ተቃዋሚ ወይም ጋኔን ፈቃድ ቢኖር በእግዚአብሔር ፈቃድና ትግዕስት ብቻ ነው ስንኳ ለጊዜው ሊቃወሙት የሚቻለው (ኩፋሌ 10:5-7)።

ሚካኤል

ሚካኤል (በዕብራይስጥ: מִיכָאֵל‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል

መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

የቅዱስ ሚካኤልን ተአምራቶች ወይም ድርሳኑን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ

ሰውን ይረዳሉ

ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/

ስግደት ይገባቸዋል

ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15

ማርያም

ድንግል ማርያም በክርስትናና፣ በእስልምና እምነቶች መሠረት የከበረችው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነች።

በክርስትና እምነት የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማለትም የወልድ እናት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ኃይል በሥላሴ ምርጫ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደ ወለደችው ይታመናል ። በእግዚአብሔር ህልውናም ከፍጥረት በፊት እንደነበረች ኦዘ-ም፡፫ ቁ፡፲፭ ያስረዳል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ማርያምን በጣም ከመወደዷ የተነሳ ከ፻ በላይ በሰየመቻት ስሞቿ ትጠራታለች ። የቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች

ሙስሊሞች ደግሞ መሪማ የኢየሱስ (ኢሳ) እናት ይልዋታል።

በአለም ላይ ፫ ታላላቅ እምነቶች ዘንድ እስዋም ልጅዋም ትልቅ ክብርና ቅድስና በተለይ ለልጇ መመለክ ገንዘባቸው ነው።

ከድረገጾችዎ አንዱን ለማየት እዚህላይ ይጫኑ

ሣራ

ለፊልሙ፣ ሳራን ይዩ።

ሣራ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የአብርሃም ሚስትና የይስሐቅ እናት ነበረች። በዑር ከላውዴዎን ተወልዳ ስሟ በመጀመርያ ሦራ (ወይም በዕብራይስጡ ሣራይ፥ «ልዕልቴ») ሲሆን በኋላ እግዚአብሔር ወደ «ሣራ» (ዕብራይስጥ ሣራህ፥ «ልዕልት») ቀየረው።

በኦሪት ዘፍጥረት 20፡12 ዘንድ፥ አብርሃም ለጌራራ (ፍልስጥኤም) ንጉሥ ለአቢሜሌክ እንዳለው፣ ሣራ የአባቱ (ታራ) ልጅ ሆና በእውነት እህቱ ነበረች። በኩፋሌ 10፡47 ደግሞ አብራም የአባቱን ልጅ ሦራን እንዳገባት ይገልጻል። (ይህ አይነት ትዳር በእግዚአብሔር ሕገጋት የተከለከለው በሕገ ሙሴ ገና ወደፊት ነበር።)

ዘፍጥረት 17:17፥ ኩፋሌ 12:32 እንደሚለን የአብርሃም ዕድሜ መቶ ሲሆን የሣራ ዕድሜ 90 ዓመት ስለ ተባለ ከአብርሃም በኋላ 10 ዓመታት እንደ ተወለደች ይመስላል። ዘፍጥረት 23:1 እስከ 127 ዓመት በሕይወት ኖረች ይለናል። በኩፋሌው ዜና መዋዕል መሠረት ግን ሣራ በ2024 ዓመተ ዓለም ዐረፈች (14:22)፣ ይህ ከአብርሃም ልደት 148 አመታት በኋላ ሊቆጠር ስለሚችል (10:30) እነዚህ ቁጥሮች ሁሉ አይስማሙም። የሣራ ዕድሜ በዘፍጥረት 23:1 እስከ 138 ዓመት ድረስ ከሆነ ግን ሁላቸው ይስማሙ ነበር። በዕብራይስጥ ኦሪት ዘፍጥረት የተሠጡት ዕድሜዎች እንዲህ አይነት ልዩነት ስለሚበዛ፣ ይህ የአይሁድ ረቢዎች ቅጂዎች ግድፋት አልነበረም ለማለት አንችልም።

ሦራ ከአብራም ጋራ ከዑር ወደ ካራን፣ ከካራንም ወደ ከነዓን ተጓዘች። አብርሃም የቤተሠቡ ባለቤት ሲሆን በከብትና በሎሌዎች ረገድ በጣም ሀብታም ሆነ። ረሃብ ወደ ከነዓን አገር በደረሰ ጊዜ ግን ወደ ግብጽ ሄዱ። የሣራህ ውበት ታዋቂ ነበረ፣ በዚያን ጊዜ የግብጽ ሰዎች ለራሳቸው እንዲይዟት ባሏንም አብርሃምን እንዲገድሉት የሚል ጭንቀት ለአብርሃም ነበረ። ስለዚህ እህቱ ብቻ እንደ ሆነች ለማለት አዘዛት። እንዲህ ሆነ፣ የግንጽም ፈርዖን ሣራን ወደ ቤተ መንግሥቱ ጨመራትና ለአብርሃም የብዙ ከብቶች ዋጋ ሰጠው። ሳይነካት ግን እግዚአብሔር ቤተ መንግሥቱን በመቅሠፍት መታ። ስለዚህ ፈርዖን በደሉን ስላወቀ አብርሃምን ሦራንና ከብቶቻቸውንም ከዚያ ሰደዳቸው። በኩፋሌ ዘንድ እነሱ በግብጽ ለ7 ዓመታት ቆዩ፣ ግብፃዊት ባሪያዋን ሀጋርን በዚህ ዘመን እንዳገኙ ይሆናል።

ሣራ እስካሁን ድረስ መካን ሆና ልጅ እንዲገኝ ባሪያዋን ሀጋርን ለአብራም እንደ ሁለተኛ ሚስት ሰጠቻት (ዘፍጥረት 16:3)። ሀጋር የአብርሃም ሚስት ምንም ብትሆን ግን ለሣራ በባርነት ቆየች፣ ስለዚህ ርጉዝ ከሆነች በኋላ በሀጋርና በእመቤቷ በሣራ መካከል መቀኝነት መጣ። ሀጋር ለአብራም እስማይልን ወለደች። ከጥቂት ዓመታት በኋላ የሥላሴ 3 መላዕክት አብርሃምን በከነዓን ሲጎበኙ ሣራ እራሷ ልጅ እንድትወልድ አሉ። ሣራም በዕድሜዋ ልጅ እንድትወልድ ሰምታ በልብዋ ሳቀች። ለምን ሳቅሽ ሲላት ደግሞ አልሳቅሁም ብላ ካደችው። እግዚአብሔር ለኔ ምንም የማይቻለኝ ሥራ የለም አላቸው። ልክ እንዳላቸውም ሣራ ለአብርሃም ልጁን ይስሐቅ ወለደ። ከዚህ በኋላ ከእመቤቷ ጋር ስለ ነበረው መቀያየም ሀጋርና እስማይል ሸሽተው የእስማይል ልጆች በፋራን ምድረ በዳ ሠፈሩ።

ሣራ ገና እርጉዝ በነበረችበት ወቅት በጌራራ ሲቆዩ፣ አብርሃም እንደገና እህቴ ብቻ ናት ብሎ አስመሰለ። እንደ ዘመኑ ልማድ የአገሩ ንጉሥ አቢሜሌክ ለራሱ እንድትሆን ወሰዳት። እንደገና ንጉሡ ሳይነካት እግዚአብሔር ማለደ፣ በሕልሙ ውስጥ ዛተው። የእግዜር ፈቃድ ከአቢሜሌክ ይልቅ አሸነፈና ያንጊዜ ሣራ በነጻ ወጣች፣ አቢሚሌክ ደግሞ ለአብርሃም ብዙ ከብትና ብር ጨመረ (ዘፍጥረት ምዕራፍ 20) ።

ሣራ ቢያንስ 127 ዓመታት ሆና ባረፈችበት ዘመን አብርሃም ለመቃብር አንድ ዋሻ በኬብሮን ከኬጥያዊው ሰው ኤፍሮን ገዛ።

ሣራ የታማኝነት አራያ ሆና በአዲስ ኪዳን ብዙ ጊዜ ትከበራለች -- ሮማውያን 4፡19፣ 9፡9፤ ዕብራውያን 11፡11፣ ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡22-26፤ 1 ጴጥሮስ 3፡6።

በቁርአን ደግሞ ሣራ በስሟ ባትጠቀስም በዘፍጥረት ከተገኘው ታሪክ ብዙ አይለይም።

በኋላ የአይሁድ ረቢዎች (ከፈሪሳውያን ወገን የወጡ) እንደ ልማዳቸው ስለ ሣራ የጻፉት ተጨማሪ መረጃዎችና ትችቶች ብዙ አሉ።

ሥላሴ

ሥላሴ ማለት ሠለሰ ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፣ ቃሉም የግእዝ ነው። ይህ ቃል የአምላክን አንድነትና ሦስትነትን ያመለክታል።

የሥላሴ እምነት የክርስትና ሃይማኖቶች ተከታይ አንዷ ከሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዋነኛ መሰረተ ትምህርት ነው።

ትምህርቱ በዐቢይ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ (ተዋሕዶ፣ ምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት) ዘንድ ተቀባይ ሲሆን ማለትም በእንግሊዘኛ ሞኖቴዪዝም (Monotheism= በአንድ አምላክ ማመን) ይባላል፣ የሥላሴን አንድነት ያልተረዱ ወይም መረዳት የማይፈልጉ ፖሊቴዪዝም (በብዙ አምላክ ማመን= Polytheism) ብለው ይሰይሙታል ፣ ደግሞ ከማያስተምሩት ክፍልፋዮች መካከል አሪያኒስም፣ የይሖዋ ምስክሮች፣ እና ሞርሞኒስም ተገኝተዋል።

ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር

ስብሐት (ስብሐት ለአብ) ገብረ እግዚአብሔር (ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም. - ሰኞ፣ የካቲት 12 ቀን 2004) በትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደ ፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው።

ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መጽሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን (Das Capital) ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል።

ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል።

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው። ደራሲው የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው። ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው።

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ

ቀዳማዊ ፡ ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ (ቀ.ኃ.ሥ.) ከጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፳፫ እስከ መስከረም ፪ ቀን ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ የኢትዮጵያ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ነበሩ። ተፈሪ ፡ መኰንን ፡ ሐምሌ ፲፮ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፹፬ ዓ.ም. ፡ ከአባታቸው ፡ ከልዑል ፡ ራስ መኰንን ፡ እና ፡ ከእናታቸው ፡ ከወይዘሮ ፡ የሺ ፡ እመቤት ፡ ኤጀርሳ ፡ ጎሮ ፡ በተባለ ፡ የገጠር ፡ ቀበሌ ፡ ሐረርጌ ፡ ውስጥ ፡ ተወለዱ።

በ፲፰፻፺፱ ፡ የሲዳሞ ፡ አውራጃ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። በ፲፱፻፫ ዓ.ም. ፡ የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሆኑ። የሐረርጌ ፡ አገረ ፡ ገዥ ፡ ሲሆኑ ፣ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሺህ ፡ ተከታዮች ፡ ነበሩዋቸውና ፡ ልጅ ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ በኅይል ፡ እንዳያስወጡ ፤ እያሱም ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ አገረ ፡ ገዥነት ፡ እንዳይሽሯቸው ፡ የሚል ፡ ስምምነት ፡ ተዋዋሉ። ዳሩ ፡ ግን ፡ እያሱ ፡ ሃይማኖታቸውን ፡ ከክርስትና ፡ ወደ ፡ እስልምና ፡ እንደቀየሩ ፡ የሚል ፡ ማስረጃ ፡ ቀረበና ፡ ብዙ ፡ መኳንንትና ፡ ቀሳውስት ፡ ስለዚህ ፡ ኢያሱን ፡ አልወደዱዋቸውም ፡ ነበር። ከዚህም ፡ በላይ ፡ እያሱ ፡ ተፈሪን ፡ ከሐረር ፡ ከአገረ ፡ ገዥነታቸው ፡ ለመሻር ፡ በሞከሩበት ፡ ወቅት ፡ ስምምነታቸው ፡ እንግዲህ ፡ ተሠርዞ ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ ለወገናቸው ፡ ከስምምነቱ ፡ ተለቅቀው ፡ በዚያን ፡ ጊዜ ፡ እሳቸው ፡ እያሱን ፡ ከእንደራሴነት ፡ አስወጡ። እንግዲህ ፡ በ፲፱፻፱ ፡ ዓ.ም. ፡ መኳንንቱ ፡ ዘውዲቱን ፡ ንግሥተ ፡ ነገሥት ፡ ሆነው ፡ አድርገዋቸው ፡ ተፈሪ ፡ ደግሞ ፡ እንደራሴ ፡ ሆኑ። ከዚህ ፡ ወቅት ፡ ጀምሮ ፡ ተፈሪ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ባለሙሉ ፡ ሥልጣን ፡ ነበሩ። በመስከረም ፳፯ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፩ ፡ ዓ.ም. ፡ የንጉሥነት ፡ ማዕረግ ፡ ተጨመረላችው። በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም ፡ ንግሥት ፡ ዘውዲቱ ፡ አርፈው ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ሆኑና ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. ፡ ብዙ ፡ የውጭ ፡ ልዑካን ፡ በተገኙበት ፡ ታላቅ ፡ ሥነ-ሥርዓት ፡ ቅብዓ ፡ ቅዱስ ፡ ተቀብተው ፡ እሳቸውና ፡ ሚስታቸው ፡ እቴጌ ፡ መነን ፡ ዘውድ ፡ ጫኑ።

በንግሥ ፡ በዓሉ ፡ ዋዜማ ፡ ጥቅምት ፳፪ ፡ ቀን ፡ የትልቁ ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ የዳግማዊ ፡ ዓፄ ፡ ምኒልክ ፡ ሐውልት ፡ በመናገሻ ፡ ቅዱስ ፡ ጊዮርጊስ ፡ ቤተ-ክርስቲያን ፡ አጠገብ ፤ ለዘውድ ፡ በዓል ፡ የመጡት ፡ እንግዶች ፡ በተገኙበት ፡ ሥርዐት ፣ የሐውልቱን ፡ መጋረጃ ፡ የመግለጥ ፡ ክብር ለብሪታንያ ፡ ንጉሥ ፡ ወኪል ፡ ለ(ዱክ ፡ ኦፍ ፡ ግሎስተር) ፡ ተሰጥቶ ፡ ሐውልቱ ፡ ተመረቀ።

ለንግሥ ፡ ስርዐቱ ፡ ጥሪ ፡ የተደረገላቸው ፡ የውጭ ፡ አገር ፡ ልኡካን ፡ ከየአገራቸው ፡ ጋዜጠኞች ፡ ጋር ፡ ከጥቅምት ፰ ፡ ቀን ፡ ጀምሮ ፡ በየተራ ፡ ወደ ፡ አዲስ ፡ አበባ ፡ ገብተው ፡ ስለነበር ፡ ሥርዓቱ ፡ በዓለም ፡ ዜና ፡ ማሰራጫ ፡ በየአገሩ ፡ ታይቶ ፡ ነበር። በተለይም ፡ በብሪታንያ ፡ ቅኝ ፡ ግዛት ፡ በጃማይካ ፡ አንዳንድ ፡ ድሀ ፡ ጥቁር ፡ ሕዝቦች ፡ ስለ ፡ ማዕረጋቸው ፡ ተረድተው ፡ የተመለሰ ፡ መሢህ ፡ ነው ፡ ብለው ፡ ይሰብኩ ፡ ጀመር። እንደዚህ ፡ የሚሉት ፡ ሰዎች ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ድረስ ፡ ስለ ፡ ፊተኛው ፡ ስማቸው ፡ «ራስ ፡ ተፈሪ» ፡ ትዝታ ፡ ራሳቸውን ፡ «ራስታፋራይ» ፡ (ራሰተፈሪያውያን) ፡ ብለዋል።

ዓጼ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዘውድ ፡ እንደጫኑ ፡ የአገሪቱን ፡ የመጀመሪያ ፡ ሕገ-መንግሥት ፡ እንዲዘጋጅ ፡ አዝዘው ፡ በዘውዱ ፡ አንደኛ ፡ ዓመት ፡ በዓል ፡ ጥቅምት ፳፫ ፡ ቀን ፡ ፲፱፻፳፬ ፡ ዓ.ም. ፡ በአዲሱ ፡ ምክር ፡ ቤት ፡ (ፓርላማ) ፡ ለሕዝብ ፡ ቀረበ። ከዚህም ፡ በላይ ፡ ብዙ ፡ የቴክኖዎሎጂ ፡ ስራዎችና ፡ መሻሻያዎች ፡ ወደ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ከውጭ ፡ አገር ፡ አስገቡ።

በ፲፱፻፳፰ ዓ.ም. ፡ የሙሶሊኒ ፡ ፋሺስት ፡ ሠራዊት ፡ ኢትዮጵያን ፡ በወረረ ፡ ጊዜ ፡ ጃንሆይ ፡ ሕዝባቸውን ወራሪውን በሙሉ ለመቃወም እንዳስነሡና የከተት ዐዋጆቻቸው በታሪክ ገጾች ይዘገባሉ። በዐዋጅ መሠረት የዘመቻው ጊዜ እስቲያልቅ ድረስ ለሚታግሉ ነጋዶች ከቀረጥ አስተስርየት ሰጣቸው። እራሳቸው በቆራጥነት ፡ ከታገሉ ፡ በኋላ ፡ የጠላቱ ፡ ጦር ፡ ኅይል ፡ ግን ፡ በመጨረሻ ፡ ወደ ፡ እንግሊዝ ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ አሰደዳቸው። ወደ ፡ ጄኔቭ ፡ ስዊስ ፡ ወደ ፡ ዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ማኅበር ፡ ሄደው ፡ ስለ ፡ ጣልያኖች ፡ የዓለምን ፡ እርዳታ ፡ በመጠየቅ ፡ ተናገሩ። የዓለም ፡ መንግሥታት ፡ ግን ፡ ብዙ ፡ አላደረጉም። በ፲፱፻፴፪ ዓ.ም. ፡ ግን ፡ አውሮፓ ፡ ሁሉ ፡ በሁለተኛው ፡ የዓለም ፡ ጦርነት ፡ ተያዘ። የእንግሊዝ ፡ ሠራዊቶች ፡ ለኢትዮጵያ ፡ አርበኞች ፡ እርዳታ ፡ በመስጠት ፡ ጣልያኖች ፡ ተሸንፈው ፡ በ፲፱፻፴፫ ዓ.ም. ፡ ኢትዮጵያን ፡ ተዉ። ዓፄ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ አዲስ ፡ አበባን ፡ እንደገና ፡ የገቡበት ፡ ቀን ፡ ከወጡበት ፡ ቀን ፡ በልኩ ፡ ዕለት ፡ አምስት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ ነበረ።

ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በ1948 ዓ.ም. ተሻሽሎ የወጣ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ፡ የሕዝቦችን ፡ መብቶችና ፡ ተከፋይነት ፡ በመንግሥት ፡ አስፋፍቶ ፡ ሁለቱ ፡ ምክር ፡ ቤቶች ፡ እንደመረጡ ፡ አደረገ። በ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፡ ግርማዊነታቸው ፡ የአፍሪካ ፡ አንድነት ፡ ድርጅት ፡ በአዲስ ፡ አበባ ፡ እንዲመሠረት ፡ ብዙ ፡ ድጋፍ ፡ ሰጡ። በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. ፡ ወደ ፡ ካሪቢያን ፡ ጉብኝት ፡ አድርገው ፡ የጃማይካ ፡ ራስታዎች ፡ ተገኛኙ። በ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ፡ በማርክሲስት ፡ አብዮት ፡ ደርግ ፡ ሥልጣን ፡ ያዙና ፡ እሳቸው ፡ በእሥር ፡ ቤት ፡ ታሰሩ። በሚከተለው ፡ ዓመት ፡ ከተፈጥሮ ፡ ጠንቅ ፡ እንደ ፡ አረፉ ፡ አሉ ፤ ሆኖም ፡ ለምን ፡ እንደ ፡ ሞቱ ፡ ስለሚለው ፡ ጥያቄ ፡ ትንሽ ፡ ክርክር ፡ አለ። ብዙ ፡ ራስታዎች ፡ ደግሞ ፡ አሁን ፡ እንደሚኖሩ ፡ ይላሉ።

ቅዱስ ሩፋኤል

ቅዱስ ሩፋኤል (በዕብራይስጥ: רָפָאֵל) ሲነበብ ሩፋኤል ፣ ከ፯ቱ ሊቀመላእክት መዐረጉ ሦሥተኛ ነው ።

ሩፋኤል መላእከ ኃይል

በግዕዝ :

ፈታሔ መኀፀን ወሰፋድል ።

መወለድ መንፈሳዊ ።

ወሐኪም ሰማያዊ ይባላል ።የወላድ ማኀፀን እንዲፈታ ስለተሾመ ከጌታ አዋላጅ ብትኖርም ባትኖርም ሩፋኤል አይታጣም ፣ በምጥ ጊዜ ሴቶች ሁሉ በባላገር ያሉ መልኩን ያነግታሉ ማየ ጸሎቱንም ይጠጣሉ ቶሎም በፍጥነት ይወልዳሉ ።

አስርቱ ቃላት

አስርቱ ቃላት ወይም አስርቱ ትዕዛዛት በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔር ለሙሴ በደብረ ሲና የገለጣቸው 10 ትዕዛዛት ወይም ሕግጋት ናቸው። የሚገኘው በኦሪት ዘጸአት 20፡2-17 ሲሆን፣ ዳግመኛ በኦሪት ዘዳግም 5፡6-21 በጥቃቅን ተለውጦ ሊታዩ ይችላሉ። እስከምናውቀው ድረስ፣ መጀመርያ የተጻፉበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ነበረ።

አዳም

አዳም እግዚአብሔር የፈጠረው የመጀመሪያው ሰው ነው።

ኢየሱስ

ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישוע ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት በግሪክ ቋንቋ Χριστός ነው፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም አማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው ።

እየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለትም ከሥላሴ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ

እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።

እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።

ከነዓን (ጥንታዊ አገር)

ከነዓን ጥንታዊ አገር ሲሆን ዛሬ በእስራኤልና በሊባኖስ አካባቢ ያሉትን አካባቢዎች ያጠቃልል ነበር። በመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን አገር ለአብርሃም ልጆች በቃል ኪዳን ሰጠ።

ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ

አጼ ዘርአ ያዕቆብ በዘውድ ስማቸው ቆስጠንጥንዮስ ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግስትክብረ እግዚ በ1399 እ.ኤ.አ. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር የድሮውፈተገር ክፍለ ሐገር ተወለዱ(ከቀኝ ያለውን ካርታ ይመልከቱ) ። የነገሡበትም ዘመን 1434 - 1468 እ.ኤ.አ. ነበር። ያረፉትም በደጋ ደሴት፣ ጣና ሃይቅ ነው።

በ ኢሲራክ ዘሽሌ ገብረኪዳን ተጻፈ።

ከኢልዮን የኢትዮጵያ ኅብረት

የባቢሎን ግንብ

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ኃይማኖት ተከታዮች በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ፴ ዓ/ም በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውሰው፣ ኤጲፋንያ በመባልም የሚታወቀው ደማቅ በዓል ነው። መገለጥ፣ መታየት ማለት ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ታሪክ የሚገኘው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ቁ ፲፫–፲፯ ውስጥ ነው። ጌታ

በአገራችን፣ ጥር ፲ ቀን፣ በከተራ፣ በገጠር ወራጅ ውሃ የሚከተርበት፣ ታቦታት ከየአቢያተ ክርስቲያናቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በምዕመናን ታጅበው በዘፈንና በሆታ ይሄዳሉ። እዚያም በየተዘጋጀአቡነ ባስልዮስ ከእስክንድርያ ፓትርያርክ አቡነ ዮሳብ 2ኛ የጵጵስና ማዕረግ ተቀበሉ። ኢትዮጵያም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እራሷን የቻለች ሆነች። ወደ ፶፭-፷ ሚሊዮን የሚቀርቡ ምእመናን ሲኖሩት ከምሥራቃዊ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ትልቁ ነው።

ዳግማዊ ምኒልክ

ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ (ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፮ እስከ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም.) ከ፲፰፻፶፯ እስከ ፲፰፻፹፪ ዓ/ም የሸዋ ንጉሥ ከዚያም ከ፲፰፻፹፪ እስከ ፲፱፻፮ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ።

ግንቦት

ግንቦት የወር ስም ሆኖ በሚያዝያ ወር እና በሰኔ ወር መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ዘጠነኛው የወር ስም ነው።

«ግንቦት» ከግዕዙ «ግንባት» ከሚለው ቃል የተባዛ ነው። የግንቦት ወር የክረምት ጎረቤት ቢሆንም ሙቀታማ፣ ደረቃማ እና ዝንብ የሚበዛበት ወር ነው። በዚህም ጸባዩ ብዙ ምሳሌያዊ አነጋገሮችን አፍርቷል።

አባቶች "በግንቦት አንድ ዋንጫ ወተት" ይላሉ። ”ኅብረ ብዕር” በተባለው መጽሐፋቸው፣ አቶ ካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር፣ ብሂሉ ሰውነታችን ኃይለኛውን የግንቦት ሙቀት መቋቋም ይችል ዘንድ አንጀት የሚያርስ፣ ቆዳን የሚያለሰልስ፣ የጠፋ አቅምን የሚመልስ ወተት ማግኘት አለበት ለማለት ነው። ይላሉ

ሌላም ብሂል አለ። "በነሐሴ ባቄላ፣ በግንቦት አተላ" የሚለውም ሰው ብቻ ሳይሆን ከብቶችም በደረቃማው ገጽታ ምክንያት በግንቦት ወር ምን ያህል እንደሚጐዱ ያሳያል። በመሆኑም በወሩ አተላ እንደሚወደድ አመልካች ነው።

ግንቦት ጎልታ የምትታወቀው በተለይ ዓመት ካመት ከልደታ ጋር ነው። ልዩ ክብር አላት፤ ድግስም አላት። ከንፍሮ እስከ ቂጣ ብሎም እስከ እርድ ድረስ ይፈጸምባታል።

በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ ሥርዓት ደግሞ "ቦረንተቻ" የሚከበርበት ወር ነው። ጐጆ የወጣ ሁሉ ከሠላሳ ቀናት በአንዱ (ራሱ በመረጠው) ድግስ መደገስ አለበት፤ በድግሱ መቅረብ ያለባቸው የድግስ ዓይነቶችም ቂጣ፣ ቆሎ፣ ጉሽ ጠላና በግ ናቸው፤ ለድግሱ የሚታረደው በግ፣ ሙሉ ጥቁር ሆኖ ግንባሩ ላይ ነጭ ምልክት ያለበት መሆንም ይኖርበታል። የድግሱ ሥነ ሥርዓት የሚከናወነው ከመሸ በኋላ ማለትም ከብት በረት ከገባ በኋላ ሲሆን፣ ለዝግጅቱ ተብሎ የሚታረደው የበግ ሥጋ መበላት ያለበት ተጠብሶ ነው። ከዚህ ውጭ ሥጋው በወጥ መልክ ተሠርቶ ወይም በጥሬው መብላት አይፈቀድም።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.