አርጀንቲና

አርጀንቲና ወይም በይፋ አርጀንቲናዊ ሬፑብሊክ (እስፓንኛ፦ República Argentina /ሬፑብሊካ አርሔንቲና/) በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማ ብዌኖስ አይሬስ ነው።

መደበኛው ቋንቋ እስፓንኛ ሲሆን ቀበሌኛው በእስፓንያ ከሚሰማው ትንሽ ይለያል። ሌሎችም ቋንቋዎች የሚናግሩ ሕዝቦች አሉ፣ ወይም ኗሪ ቋንቋዎች እንደ ቀቿ፣ ወይም አውሮፓዊ ቋንቋዎች (በተለይ ጣልኛጀርመንኛ)

አርጀንቲና ሪፐብሊክ
República Argentina

የአርጀንቲና ሰንደቅ ዓላማ የአርጀንቲና አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Himno Nacional Argentino

የአርጀንቲናመገኛ
ዋና ከተማ ብዌኖስ አይሬስ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እስፓንኛ
መንግሥት

ፕሬዝዳንት
ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል
ማውሪስዮ ማክሪ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
2,780,400 (8ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
43,417,000
ሰዓት ክልል UTC −3
የስልክ መግቢያ 54
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .ar
ሖርሔ ልዊስ ቦርሔስ

ሖርሔ ልዊስ ቦርሔስ (እስፓንኛ፦ Jorge Luis Borges) 1891-1978 ዓም) የአርጀንቲና ጸሓፊ ነበር።

ቀቿ

ቀቿ (Qhichwa Simi / Runa Shimi / Runa Simi) በደቡብ አሜሪካ በ10 ሚሊዮን ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በጥንታዊ ኢንካ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበረ። ዛሬም በቦሊቪያ ፔሩና አንዳንድ አውራጃ በኤክዋዶር መደበኛ ሁኔታ አለው። አይማራ የሚባለው ሌላ ደቡብ-አሜሪካዊ ቋንቋ ዘመድ ነው።

እስፓንያውያን ከወረሩ አስቀድሞ በሰፊ ይሰማ ሲሆን በዚያን ጊዜ ምንም ጽሕፈት አልነበረውም። ይሁንና መቆጣጠር ሲባጎዎች በማሰር ዘዴ ነበር የተፈጸመ። ዛሬ የሚጻፈው በላቲን ፊደል ነው።

ብዌኖስ አይሬስ

ብዌኖስ አይሬስ የአርጀንቲና ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 13,349,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,768,772 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 34°40′ ደቡብ ኬክሮስ እና 58°30′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

መጀመርያው ጊዜ ስፓኒሾች የመሠረቱት በ1528 ዓ.ም. ሲሆን በ1533 ዓ.ም. ስለ ኗሪዎች መቃወም እንደገና ተዉት።

ሁለተኛ ጊዜ በ1572 ዓ.ም. መሠረቱት። በ1872 ዓ.ም. የአርጀንቲና መንግሥት መቀመጫ ሆነ።

ቼ ጌቫራ

ኤርኔስቶ ጌቫራ ዴ ላ ሴርና (በስፓንኛ: Ernesto Guevara De La Serna) ወይም ቼ ጌቫራ (በስፓንኛ: Che Guevara) (1920-1960 ዓ.ም.) የአርጀንቲና ተወላጅ ሲሆን በኩባ ኰሙኒስት አብዮት የገነነ አብዮታዊ ሆነ። ከዚያ በኋላ በሌሎች አገራት እንደ ኮንጎ እና ቦሊቪያ ማርክሲስት አብዮታዊ ሆነ። በ1960 ዓ.ም. በቦሊቪያ ተገደለ።

አንዴስ ተራሮች

አንዴስ ተራሮች በምሥራቁ ደቡብ አሜሪካ ከቬኔዝዌላ እስከ አርጀንቲና ድረስ የሚዘረጋ የተራሮች ሰንሰለት ነው።

አኮንካጓ

አኮንካጓ በሜንዶዛ ክፍለ ሃገር አርጀንቲና የሚገኝ በከፍታ ከአለም 2ኛ ደረጃውን የያዘ ተራራ ነው።

የ1978 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

የ1978 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፩ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከግንቦት ፳፬ እስከ ሰኔ ፲፰ ቀን ፲፱፻፸ ዓ.ም. በአርጀንቲና ተካሄዷል። አርጀንቲና ኔዘርላንድን ፫ ለ ፩ በተጨማሪ ሰዓት በመርታት ዋንጫውን አሸንፋለች። የውድድሩ ይፋዊ ኳስ አዲዳስ ታንጎ ነበር።

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፱ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ከሰኔ ፬ እስከ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በደቡብ አፍሪካ ተካሄዷል። ውድድሩን ለማቅረብ የተካሄደው ዕጣ ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ብቻ እንዲሳተፉ ነበር የተፈቀደው። ደቡብ አፍሪካ ግብፅና ሞሮኮን በማሸነፍ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫን ያቀረበች አፍሪካዊ ሀገር ሆናለች።

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ

የ2010 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ ከሰኔ ፭ እስከ ሰኔ ፲፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ተካሄዷል። በዚህ ምድብ ውስጥ የአርጀንቲና፣ ግሪክ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ናይጄሪያ ቡድኖች ነበሩ።

የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን

የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከክርስትና ዋና አብያተ ክርስቲያናት ቅርንጫፎች አንዱ ነው። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በመባልም ይታወቃል። በአለማችን እጅግ ጥንታዊ ከሆኑት ሃይማኖታዊ ተቋማት አንዷ በመሆን፣ በምዕራቡ ዓለም ታሪክና እድገት ውስጥ ትልቅ ሚና ተጫውታለች። የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በምዕራቡ ዓለም ፍልስፍና፣ ባህል፣ ሳይንስ እና ሥነ ጥበብ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ፓፓ ወይም ጳጳሱ በመባል የሚታወቀው የሮማው ጳጳስ፣ የቤተክርስቲያን መሠረተ እምነቶች በኒቂያው የሃይማኖት መግለጫ ውስጥ ተጠቃለው ቀርበዋል። ዋናው ማዕከላዊው ቅዱስ ቅድስተ ቅዱሳን በቫቲካን ከተማ በሮማ ኢጣሊያ ውስጥ ይገኛል።

በዓለም ላይ ከ1.29 ቢሊዮን በላይ አባላት ያሉት ዓለም አቀፍ የክርስትያን ቤተ ክርስቲያን ናት። ካቶሊኮች በመላው ዓለም የሚኖሩት በተልእኮዎች፣ በዲያስፖራዎች፣ እና በተለዋወጦች ነው። ከ20ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ አብዛኛዎቹ በደቡባዊ ሄመዝፊው (ክፍለ አለም) ውስጥ አውሮፓ ውስጥ ዓለማዊነት ስለማይታወቁ እና በመካከለኛው ምስራቅ ላይ ስደትን ያሻብባሉ። ከቫቲካን ከተማ በላይ በአሁኑ ወቅት የመንግሥት ሃይማኖት በኮስታ ሪካ፣ ሊክተንስታይን፣ ማልታ፣ እና ሞናኮ ነው። በተጨማሪ በአንዶራ፣ አርጀንቲና፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኤል ሳልቫዶር፣ ፓናማ፣ ፓራጓይ፣ ፔሩና ፖላንድ፣ እንዲሁም በፈረንሳይና በስዊስ ክፍላገራት ውስጥ የመንግሥት ድጋፍ ወይም ዕውቅና በይፋ ተስጥቷል።

የስልክ መግቢያ

የስልክ መግቢያ ቁጥር በየሃገሩ ይለያል።

የአርጀንቲና እግር ኳስ ማህበር

የአርጀንቲና እግር ኳስ ማህበር (እስፓንኛ፦ Asociación del Fútbol Argentino, AFA) የአርጀንቲና እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። ማህበሩ የአርጀንቲና ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንንና የተለያዩ ብሔራዊ ውድድሮችን ያዘጋጃል።

የዓለም ሀገራት ባንዲራዎች

የአለም ሀገራት ባንዲራዎች ከዚህ እንደሚከተለው ናቸው።

የዓለም ዋንጫ

የዓለም ዋንጫ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር አባል አገሮች የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ነው። ከ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት የ፲፱፻፴፬ ዓ/ም እና የ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ውድድሮች ሲሰረዙ እስካሁን አሥራ ዘጠኝ ውድድሮች ተካሂደዋል። የዋንጫና ደረጃ ጨዋታዎቹ በዓለም በብዙ ተመልካቾች ከሚታዩ የስፖርት ዝግጅቶች አንደኛ ነው። በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የ ፳፻፪ቱ ፲፱ ኛው የዋንጫ ውድድር በ ፩ ነጥብ ፩ ቢሊዮን ሰዎች እንደታየ ይገመታል።

ደቡብ አሜሪካ

ደቡብ አሜሪካ በአለም ካርታ ላይ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ምእራብ የሚገኝ አህጉር ነው።

ፋልክላንድ ደሴቶች

ፋልክላንድ ደሴቶች በአትላንቲክ ውቅያኖስ በደቡብ አሜሪካ አጠገብ የሚገኝ የዩናይትድ ኪንግደም ባሕር ማዶ ግዛት ነው። አርጀንቲና ግን በደሴቶቹ ላይ ይግባኝ ትላለች።

ፓፓ ፍራንሲስኮስ

ፓፓ ፍራንሲስኮስ ወይም ፖፕ ፍራንሲስ፣ ልደት ስም ሖርጌ ማሪዮ ቤርጎልዮ (1929 ዓም አርጀንቲና ተወለዱ) ከ2005 ዓም ጀምሮ የሮሜ ፓፓ ወይም የሮማን ካቶሊክ መሪ ናቸው።

ደቡብ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
South America (orthographic projection)

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.