አመንቺ ጅረት

አመንቺ ጅረት የኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሄድበትን አቅጣጫ እየቀየረ ሲጓዝ የሚፈጠር ጅረት ነው። ቀጥተኛ ጅረት የኤሌክትሪክ ቻርጅ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ሲጓዝ የሚፈጠር ጅረት ነው።

ኒኮላ ተስላ

ኒኮላ ተስላ (1848-1935 ዓም) ሰርባዊ-አሜሪካዊ ፊዚሲስትና የፈጠራዎች ፈጣሪ ነበር። በተለይ በ AC አመንቺ ጅረት ስለ ሠራው ማሻሻል ዝነኛ ነው። በኦስትሪያ-ሀንጋሪ መንግሥት ተወልዶ በኋለ ወደ አሜሪካ ፈለሰ።

ኤሌክትሪክ ዑደት

የኤሌክትሪክ ዑደት ማለቱ የኤሌክትሪክ አባላት እርስ በርስ ግንኙነት ነው። የኤሌክትሪክ አባላት (የኤሌክትሪክ መሰረታዊ ክፍሎች) ኤሌክትሪክ ተቃዋሚን፣ ኤሌክትሪክ ቃቤን፣ ኤሌክትሪክ አቃቤን፣ ቮልቴጅ ምንጭን፣ ኤሌክትሪክ ጅረት ምንጭን ማብሪያ ማጥፊያንና ሽቦን ይጠቀልላል። በኤሌክትሪክ መረብና በኤሌክትሪክ ዑደት ያለው ልዩነት የኤሌክትሪክ ዑደት ሽቦወች የተዘጋ መንገድ ሲሰሩ የኤሌክትሪክ መረብ ግን ክፍት ሊሆን ይችላል። በሌላ አነጋገር በኤሌክትሪክ ዑደት ውስጥ የሚፈጠር የኤሌክትሪክ ጅረት ክብ ሰርቶ ይመላለሳል እንጂ ወጥቶ የሚጠፋበት ክፍተት አያገኝም።

ከቮልቴጅ ወይንም ጅረት ምንጮች፣ ከጉልት የኤሌክትሪክ አባላት (ፓሲቭ ኤለመንትስ - ምሳሌ ተቃዋሚ፣ አቃቤና ቃቤ)፣ ከቀጥተኛ የተበተኑ አባላት (የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦ) የተሰሩ ማናቸውም የኤሌክትሪክ መረቦች በአልጀብራና ሽግግር (ላፕላስ ሽግግር፣ ፎሪየር ሽግግር ወዘት...) መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተተንትነው በቀጥተኛ ጅረት (ዲሬክት ከረንት)፣ በአመንቺ ጅረት (ኦልተርኔቲንግ ከረንት)ናቅጽበታዊ ባህርይ የሚያሳዩትን ጸባይ ማስላት ይቻላል።

ተነሳሽ የኤሌክትሪክ አባላትን (አክቲቭ ኢለመንትስ) ያቀፉ የኤሌክትሪክ ዑደቶች ባንጻሩ ኤሌክትሮኒክ ዑደት ሲሰኙ፣ ትንታኔያቸው ጉልት የኤሌክትሪክ አባላት (ፓሲቭ ኮምፖኔንትስ)ን ብቻ ከያዘ መረብ ይወሳሰባል። ለዚህ ምክንያቱ ቀጥተኛ (ሊኒያር) ስላልሆኑና በቀላሉ የአልጀብራና የሽግግር መንገዶችን በኒህ ላይ መተግብር ስለማይቻል ነው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.