ንግድ

ንግድ በመሰረቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ነው። ሰው ማንኛውንም የፈለገውን ቁሳቁስ ማሙዋላት የማይችል ስለሆነ የግድ በተሰማራበት ሙያ የሚያገኘውን የስራ ውጤት ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን እሱ ራሱ ማምረት የማይችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ሲል የሚያካሄደው የምርቶች ልውውጥ ሂደት ነው።

Wojciech Gerson - Gdańsk in the XVII century
Gdańsk
Accarias de Sérionne - Intérêts des nations de l'Europe, dévélopés relativement au commerce, 1766 - 5790093
Intérêts des nations de l'Europe, dévélopés relativement au commerce, 1766

ታሪክ

1965

መጋቢት 26 ቀን - የዓለም ንግድ ሕንጻ በኒው ዮርክ ከተማ ተከፈተ።ያልተወሰነ ቀን፦

የቻድ ዋና ከተማ ስም ከ'ፎርት-ላሚ' ወደ 'ንጃመና' ተለወጠ።

የኢኳቶሪያል ጊኔ ዋና ከተማ ስም ከ'ሳንታ ኢዛቤል' ወደ 'ማላቦ' ተለወጠ።

የጋምቢያ ዋና ከተማ ስም ከ'ባቱርስት' ወደ 'ባንጁል' ተለወጠ።

በልዩ ምርጫ መሠረት፣ የታንዛኒያ መንግሥት መቀመጫ ከዳር ኤስ ሳላም ወደ ዶዶማ እንዲዛወር ታቅዶ ነበር።

ዴንማርክ፣ አየርላንድና እንግሊዝ ወደ አውሮፓ ህብረት ተጨመሩ።

1985

1985 አመተ ምኅረት

መስከረም 2 ቀን - መይ ካሮል ጀሚሶን መጀመርያ ጥቁር አሜሪካዊት በጠፈር ሆነች።

መስከረም 20 ቀን - ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ የአንጎላ ፕሬዚዳንት ምርጫ ጆናስ ሳቪምቢን አሸነፈ።

ጥቅምት 24 ቀን - ቢል ክሊንተን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ ጆርጅ ቡሽን አሸነፈ።

ታኅሣሥ 23 ቀን - ቸኮስሎቫኪያ ተከፋፍሎ ቼክ ሪፑብሊክ እና ስሎቫኪያ ተለይተው 'ፍች' አደረጉ።

የካቲት 19 ቀን - ዓለም ንግድ ሕንጻ መጀመርያ ጥቃት ተቋቋመ።

ግንቦት 16 ቀን - ኤርትራ አገር ሆነች።1980ዎቹ: 1980 1981 1982 1983 1984 1985 1986 1987 1988 1989

1994

1994 አመተ ምኅረት

መስከረም 1 ቀን - አራት አውሮፕላኖች በአረብ ተዋጊዎች ተሰርቀው በአለም ንግድ ሕንጻና በፔንታጎን ተጋጭተው 3000 ያህል ሰዎች ተገደሉ።

ሐምሌ 2 ቀን - የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተፈትቶ በአፍሪካ ኅብረት ተተካ።

ነሐሴ 4 ቀን - የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ በቱርክመንኛ እንደ ቱርክመኒስታን መሪ አቶ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።

ነሐሴ 20 ቀን - የምድር ጉባኤ ስብሰባ በጆሃነስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ጀመረ።

ጳጉሜ 5 ቀን - ገለልተኛ አገር የሆነ ስዊስ በመጨረሻ የተባበሩት መንግስታት አባል ሆነ።

1 ሻምሺ-አዳድ

1 ሻምሺ-አዳድ የተርቃ ንጉሥ ኢላ-ካብካቡ ልጅ ነበረ። «የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» (MEC) የተባለው ሰነድ እንደሚለን፣ የሻምሺ-አዳድ ልደት ኢናያ (ወይም ዳዳያ) ሊሙ በሆነበት ዓመት፣ 1760 ዓክልበ. ሆነ ። በኋላ በሻሩም-አዳድ ሊሙነት (1745 ዓክልበ.) «ሻምሺ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ» ማለት እድሜው 15 ዓመት ሲሆን የተርቃን ዙፋን ወረሰ።

የሻምሺ-አዳድ ስም በዚህ ዜና መዋዕል ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። በ1734 ዓክልበ. ኡኒናን አሸነፈ፤ ለሚከተሉት ዓመታት ግን ከስሙ በቀር ቃላቱ ጠፍቷል። ወደ አሦር ንጉሥ ናራም-ሲን ዘመን መጨረሻ በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ወደ «ካርዱንያሽ» (ባቢሎን) ወረደ። ይህ ማለት በዘመቻ ባቢሎንን ያዘ አይመስልም፤ ምናልባት ወደ ባቢሎን የሄደው በስደት ይሆናል። ሆኖም በ1723 ዓክልበ. ከባቢሎን ወጥቶ ኤካላቱምን እንደ ያዘ ይዘገባል። እዚያ ለ፫ ዓመታት ቆይቶ አሹርን ይዞ ንጉሡን 2 ኤሪሹምን አስወጥቶ የአሦርን መንግሥት ለራሱ ቃመው።

ከሻምሺ-አዳድ ዘመን በአሦር ጀምሮ የካሩም ንግድ በትንሹ እስያ ተመለሰ፤ በልጁም ዘመን እስከ 1678 ዓክልበ. ድረስ ተቀጠለ።

ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል

ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል የአማርኛ ምሳሌ ነው።

ሥነ ንዋይ

ሥነ ንዋይ የምጣኔ ሀብት ጥናት ነው።

ሱዳን

ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ: السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው።

ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች።ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።

ባርነት

ባርነት በጠባብ ትርጉሙ «ሰዎችን እንደ ሌላ ሰው ንብረት የሚገዙበት፣ የሚሸጡበት፣ የሚለዋወጡበት ወይም የሚያዙበት ሁናቴ» ማለት ነው። ይህም ደግሞ «የንብረት ባርነት» ሲባል፣ ዛሬ በአሁኑ ሰዓት ሰዎች እንደ ንብረት መቆጠሩ በማናቸውም አገር ሁሉ ሕገወጥ ሆኖአል። በሰፊው ትርጉም ሰው ያለፈቃዱ ወይም ያለደመወዝ ሥራ ወይም አገልግሎት ለመፈጽም ቢገደድ፣ ይህ በተግባር ባርነት ሊባል ይችላል።

ከዝርዮቹ ሁሉ የሰው ልጅ ብቻ የሌሎቹን ዝርዮች (እንስሳ ወይም አትክልት) ለመግዛትና ለማስለምድ እንደ ተዘጋጀ ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስም ይህን ነጥብ በቀዳሚው ምዕራፍ ያውጣል። ሆኖም በሰው ልጅ ውስጥ የአለመተባበር ጸባይ ችግር ስላለ፣ በታሪክ ላይ ብዙ ጊዜ እርስ በርስ መገዛዛት የመረጡ ብዙ ሆነዋል። ስለዚህ በየአህጉሩ ከቅድመ-ታሪክ ጀምሮ ባርነት ይስፋፋ ነበር። በጥንታዊው ዘመን በጥንታዊ ግብጽ (3000 ዓክልበ. ግድም) ባርዮች እንደ ነበሩ ታውቋል። ከዚያም በኋላ ኤላምና ኪሽ የተባሉት ጥንታዊ አገራት እርስ በርስ ጦርነት ሲጀምሩ (2384 ዓክልበ.)፣ ከተማረኩት ሰዎች ቁጥር የባርነት መሠረት በዓለም ላይ ዳግመኛ ቆመ።

ከዚያውም ዘመን ወዲህ፣ በብዙ አገራት ባርነት ሕጋዊ ቢሆንም፣ በሌሎች አገራት ተከለክሏል። በድሮ ዘመን በብዙ አገራት ሕገ መንግሥት ዘንድ የባርነት ልማድ በሕጋዊነት ይጠበቅ ነበር። በ600 ዓክልበ. ግን በግሪክ አገር የአቴና አለቃ ሶሎን ባወጣው ሕገ መንግሥት መሠረት፣ የእዳ ባርነት ተከለከለና ባርዮች የነበሩት የአቴና ዜጎች ነጻነታቸውን አገኙ። የባርዮች ሁኔታን የሚቀምሩት ሕግጋት ወይም ልማዶች በጊዜ ላይና ከአገር ወደ አገር ይለያዩ ነበር።

በተለይ እስልምና ከተነሣ በኋላ ብዙ ባርዮች እንደ ተማረኩ ተብሏል። የአውሮፓም መንግሥታት በአሜሪካዎች ውስጥ ቅኝ አገራት ከተከሉ በኋላ፣ እነርሱም በተለይ ከአፍሪካ የተማረኩትን ጥቁር ባርዮች ይግዙ ነበር። በ1764 ዓም ግን ባርያ መያዝ በኢንግላንድ ሕገወጥ እንደሚሆን ተበየነ። ከዚህም በኋላ በብዙ አውሮፓዊ አገራት እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ ስሜን ክፍላገራት ባርነት ሕገ ወጥ ይደረግ ጀመር። ወደ ደቡብ የተረፉት ባርዮች ግን ነፃነታቸውን ያገኙ ከአሜሪካዊ ብሔራዊ ጦርነት ቀጥሎ ብቻ ሆነ። በ1858 ዓም የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ፲፫ኛው ለውጥ ባርነትን በአሜሪካ ለዘለቄታ ከለከለ።

በአፍሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ የባርነት ልማድ ከዚህ በኋላ ተቀጠለ። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በጻፉት ታሪክ ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ውስጥ ባርነትን ለመከልከል ስለተደረጉ ጥረቶች በሰፊው ገልጸዋል። አንድ ምዕራፍ በሙሉ፣ ምዕራፍ ፲፬ «ባሮች ነጻ እንዲወጡ ስለማድረጋችንና የነፃነታቸውም ነገር በያመቱ እየተሻሸለ ስለ መሔዱ» አቅርበዋል። እሳቸው እንደ ገለጹት፣ የጣልያን መንግስት ወኪሎች ስለ ኢትዮጵያ መክሰሻ ለማድረግ የባርነት ሁናቴ በማጋነን እያወሩ ነበር። ይሁንና «በፍጥረት ጌታና ባርያ ተብሎ የተለየ ነገር አለመኖሩ በሰው ልብ የታወቀ ስለ ሆነ»፣ ከ1845 ዓም ጀምሮ የነገሡት ነገስታት ዓፄ ቴዎድሮስ፣ ዓፄ ዮሐንስ ፬ኛና ዓፄ ዳግማዊ ምኒልክ ሁላቸው የባርነት ንግድ ሕገ ወጥ የሚያድርጉ አዋጆች ቢሰጡም፣ እነዚህ አዋጆች ባብዛኛው በባላባቶች ዘንድ ቸል ተብለው ነበርና ተግባራዊ አልሆኑም። አጼ ኃይለ ሥላሴ በበኩላቸው ባርዮች ነጻ እንዲወጡ ብዙ አዋጆች ሲያውጡ፣ ለማራኪዎቹም የሙት ቅጣት እስኪያገኙ ድረስ አወጁ። ፋሺስቶች ግን እንዳሉ የባርነት መኖሩን ዋና መክሰሻ አደረጉት። እስካሁንም ድረስ የእንግሊዝኛ ውክፔድያ በፕሮፓጋንዳ እንደሚተርክ፣ የኢትዮጵያ ባርዮች ነጻ የወጡ በጣልያኖች ትዕዛዝና ሥልጣኔ ብቻ ነበረ፣ ከዚህም በላይ ሰብአዊ ንግድ (ባርነት) ዛሬ በኢትዮጵያ እንዳለ ይላል እንግሊዝኛው ውክፔድያ። ባርነትና ሰብአዊ ንግድ በውነት ግን በኢትዮጵያ ወይም የትም አገር በዘመናችን በሕግ ክልክል ነው።

^ en:Timeline_of_abolition_of_slavery_and_serfdom

^ en:Slavery in contemporary Africa፣ en:Human trafficking in Ethiopia

ቤኒን

ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶና ኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንና ዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነት፣ ዓሳ፣ እንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምና ወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦ በኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬ፣ ፍየልና የጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆ፣ ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።

አሦር

አሦር (አሹር) ማለት በጥንታዊ ዘመን በላይኛ ጤግሮስ ወንዝ አጠገብ የተገኘ ከተማና አካባቢው ነበረ። በኋለኛ ጊዜ የአሦር መንግሥት ሃይለኛ ሆኖ መላ መሬት እስከ ግብጽ ድረስ ገዛ። በጥንታዊ አሦር ከተማና በጤግሮስ አጠገብ ያሉትም ተራሮች እስከ ዛሬው አርሜንያ ድረስ 'የአሦር ተራሮች' ይሰየሙ ነበር።

በኦሪት ዘፍጥረት መሠረት አሦር (አሹር) ከኖኅ ልጅ ሴም ልጆች አንዱ ሲሆን፥ ከሰናዖር ወጥቶ አንዳንድ ከተማ ሠራ። በአሦራውያንም እምነት ዘንድ 'አሹር' ከተማውን የመሠረተው አምላክ ስም ነበረ።

ከቅድመኛው ዘመን አውራጃው ሹቡር ተብሎ ከሰናዖር (ሹመር)፣ ማሪ ወይም ከአካድ ይገዛ ነበር። ሹቡር በታላቁ ሳርጎን መንግሥት ውስጥ ክፍል ሆኖ ጉታውያን እስከ አጠፉት ድረስ ቆየ። በኋላ እስከ 1879 ዓክልበ. ግ. ከኡር 3ኛ ሥርወ መንግሥት ይቆጣጠር ነበር። የዑር መንግሥት ሲወድቅ የአሦር ከተማ ነገሥታት ሊሙ ስሞች ይመዘገባሉ።

በዚህ ወቅት አሦር ከተማ-አገር ብቻ ነበረ። ሆኖም አሦራውያን የብረታብረት ንግዳቸውን ለማስፋፋት በማሰብ አንዳንድ ቅኝ-ከተማ (ካሩም) በሐቲ (ዛሬው ቱርክ) ውስጥ መሠረቱ። ከነዚህም ዋነኛው ካነሽ የተባለው ከተማ ነበር።

በ1720 ዓክልበ. ግ. አሞራዊው ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ አገሩን ከነአሦር ከተማ አቀና። ልጁን 1 እሽመ-ዳጋን (1688-1678 ዓክልበ.) በአሦር ላይ ሾመው። ነገር ግን የባቢሎን ንጉስ ሃሙራቢ ድል አድርጎት ዙሪያው ወደ ባቢሎን መንግሥት ተሳለፈ። ከትንሹ እስያ ይካሄድ የነበረው የብረታብረት ንግድ በዚያን ጊዜ ተቋረጠ። ለሚከተለው መቶ አመት አሦር ለባቢሎን ተገዥ ነበር።

በ1507 ዓክልበ. ግ. ባቢሎን ለካሣውያን ከወደቀ በኋላ፥ አሦር በሚታኒ መንግሥት (ሑራውያን) በ1441 ዓክልበ.ግ. ይሸነፍ ነበር። ሚታኒ በኬጢያውያን ግፊት ሲወድቅ ግን የአሦር ንጉስ አሹር-ኡባሊት ነጻነቱን አዋጀ (1366 ዓክልበ. ያህል)። ከዚህ በላይ ይህ አሹር-ኡባሊት የራሱን ልጅ ኩሪጋልዙን በባቢሎን ዙፋን ላይ አሾመው።

በ1290 ዓክልበ. የአሦር ንጉስ 1 አዳድ-ኒራሪ የሚታኒን መንግሥት አሸነፈ። የአዳድ-ኒራሪ ተከታይ 1 ስልምናሶር መንግሥቱን በከጢያውያን አግጣጫ እስከ ከርከሚሽ ድረስ አስፋፋ። የስልምናሶርም ልጅ 1 ቱኩልቲ-ኒኑርታ እንኳን በባቢሎን ላይ ገዛ። ሆኖም በቅርብ ጊዜ ባቢሎን በአሦር ላይ አመጽ ታደርግ ነበር።

በ1200 ዓክልበ.. አካባቢ የኬጢያውያን መንግሥት በሙሽኪ (ፍሩጋውያን) ግፊት ስለ ወደቀ፥ ባቢሎንና አሦር ለአሞራውያን መሬት ተወዳዳሪዎች ሆኑ። የአሦር ንጉስ 1 አሹር-ረሽ-ኢሺ በዚህ አቅራቢያ በ1140 ዓክልበ. በባቢሎንን ንጉሥ 1 ናቡከደነጾር ላይ አሸነፈ።

የአሹር-ረሽ-ኢሺ ልጅ 1 ቴልጌልቴልፌልሶር የመንግሥቱን ጠረፍ በጣም አስፋፋ። ከርከሚሽን ከመማረኩ በላይ በሙሽኪ ላይ እስከ ጥቁር ባሕር ድረስ ዘመቻ አደረገ። ደግሞ እስከ ሜድትራኒያን ባሕር ድረስ ሲዘረጋ ፊንቄን (ሊባኖስ) ያዘ።

ከ1 ቴልጌልቴልፌልሶር በኋላ ከጎረቤቶቹ ከአራማውያንና ከኡራርቱ የተነሣ የአሦር ኅይል ደክሞ ነበር። በ920 ዓክልበ. ግን 2 አዳድ ኒራሪ ንጉሥ ሆሞ የአሦር ሃይል ታደሰ። ደግሞ ወደ ስሜን የኖሩትን ሕዝቦች በሙሉ በሰፈራ አፈለሳቸው። ይሁንና መንግሥቱ ከአቦር ወንዝ ወደ ምዕራብ አልዘረጋም።

ንጉስ አሹር-ናሲር-ፓል ከ890 ዓክልበ. ጀምሮ ነግሦ ያለ ምኅረት ጠረፎቹም አስፋፋ። ከአቦርና ከኤፍራጥስ መካከል ያሉትን አራማውያን ድል አድርጎ በሜድትራኒያን ሲደርስ ፊንቄን ቀረጠ። ካልሁንም ዋና ከተማው እንዲሆን አደረገው።

በልጁ 3 ስልምናሶር 34 አመት ዘመን (865-831 ዓክልበ.) አሦር በየአመቱ ለጦርነት ሠለፈ። ባቢሎን ተወርሮ ተቀረጠ። የሶርያ (አራም-ደማስቆ) ንጉስ ወልደ አዴር (አድርአዛር) ከእስራኤል ንጉስ አክዓብ ጋራ በቃርቃር ፍልሚያ ስልምናሶርን አጋጠመው። ስልምናሶርም ፊንቄንና የእስራኤል ንጉስ ኢዩን አስቀረጠ። በዋና ከተማው በካልሁ የተገኘው ጥቁር ሐውልት ስለ 3 ስልምናሶር ዘመን ድርጊቶች ይመሰክራል [1]። ከዚህ ቀጥሎ የአሦር አቅም ለመቶ አመት እንደገና ይደክም ጀመር። ሆኖም ንጉሱ 3 አዳድ-ኒራሪ (818-790 ዓክልበ.) ስርያን ማረከ ሜዶንንም ወረረ።

አካድኛ

አካድኛ ወይም አሦርኛ ወይም ባቢሎንኛ በጥንት በመስጴጦምያ የተነገረ ሴማዊ ቋንቋ ነበረ።

በሥነ ቅርስ መጀመርያው የታወቀው አካድኛ ጽሑፍ ከመስኪአጝ-ኑና ዘመን (2314 ዓክልበ. ግድም) ነው። ከአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ጀምሮ የአካድ መንግሥት (2077-2010 ዓክልበ.) በመላው መስጴጦምያ፣ ኤላምና ሶርያ አስገደዱት። ከዚያ በኋላ ኤላም ወደ ኤላምኛ መለሰ፣ የሶርያም ቋንቋ ኤብላኛ ሆነ። በአሦርና በባቢሎን የአካድኛ አይነቶች ተነገሩ። አሦራውያን በአናቶሊያ (ሐቲ) የካሩም ንግድ እስከ 1628 ዓክልበ. ድርስ ያሕል ያካሄዱ ነበር፤ የአሦርኛ አካድኛ ጥቅም እንደ መደበኛ ወይም ይፋዊ ጽሑፍ ቋንቋ አስፋፉ።

በሚከተለው ዘመን በግብጽ የተገኙ የአማርና ደብዳቤዎች (1369-1339 ዓክልበ.) እንዳሳዩ፣ ጽሕፈት የነበራቸው አገራት ሁሉ አካድኛ እንደ መደበኛ ቋንቋ ይጠቀሙ ነበር። የጥንታዊ ግብጽ፣ የከነዓን፣ የሚታኒ፣ የኬጥያውያን መንግሥት፣ የባቢሎን (ካራንዱኒያሽ)፣ የአላሺያ ወይም የአርዛዋ ባለሥልጣናት ሁላቸው በአካድኛ ተነጋገሩ። እነዚህ አገራት ግን ለየራሳቸው ልሳናት ግብጽኛ፣ ከነዓንኛ፣ ሑርኛ፣ ኬጥኛ፣ ካሥኛ፣ ሚኖአንኛ እና ሉዊኛ ነበሩዋቸው።

በ740 ዓክልበ. የአሦር ንጉሥ 3 ቴልጌልቴልፌልሶር አረማይስጥ ከአሦርኛ ጋር ይፋዊና መደበኛ ቋንቋ አደረገው። ከዚያ ጀምሮ የአረማይስጥ ጥቅም እየተስፋፋ የአካድኛ ጥቅም በየጊዜ ይቀነስ ነበር። ከአዲስ ባቢሎን መንግሥት ውድቀት በኋላ አካድኛ ባይነገርም አካድኛን መጻፍ የቻሉ ጥቂት ሊቃውንት እስከ 75 ዓም ያህል ቀሩ።

የአካድኛ ጽሕፈት ከሱመርኛ የተበደረው ኩኔይፎርም (ውሻል ቅርጽ) ጽሕፈት ነበረ። የቻይና ጽሕፈትን በመምሰል እያንዳንዱን ቃል ለማንበብ ብዙ ሺህ ምልክቶች መማር አስፈለገ። ከ200 እስከ 1850 ዓም ድረስ የኩኔይፎርም ማንበብ ችሎታ አልኖረም፤ ከ1850 ዓም በኋላ ብቻ ሊፈታ የቻለ ነው።

አዲስ አበባ

አዲስ ፡ አበባ (ወይም ባጭሩ «አዲስ») ፡ ተብላ ፡ የተሠየመችው ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ ኅዳር ፲፬ ፡ ቀን ፡ ፲፰፻፸፱ (1879) ፡ ዓ.ም. ፡ ፍልውሃ ፡ ፊን-ፊን ፡ ወደሚልበት ፡ መስክ ፡ ወርደው ፡ ሳሉ ፡ ከዚህ ፡ በፊት ፡ አይተዋት ፡ የማያውቋት ፡ አንዲት ፡ ልዩ ፡ አበባ ፡ አይተ ፡ ስለማረከቻቸው ፡ ቦታውን ፡ ‹‹አዲስ ፡ አበባ!›› ፡ አሉ ፡ ይባላል። አዲስ ፡ አበባ ፡ (ኣዲስ ኣበባ) ኢትዮጵያ ፡ ዋና ፡ ከተማ ፡ ስትሆን ፡ በተጨማሪ ፡ የአፍሪካ ፡ ሕብረት ፡ መቀመጫ ፡ እንዲሁም ፡ የብዙ ፡ የተባበሩት ፡ መንግሥታት ፡ ድርጅት ፡ ቅርንጫፎችና ፡ ሌሎችም ፡ የዓለም ፡ የዲፕሎማቲክ (የሰላማዊ ግንኙነት) ፡ ልዑካን ፡ መሰብሰቢያ ፡ ከተማ ፡ ናት። ራስ-ገዝ ፡ አስተዳደር ፡ ስላላት ፡ የከተማና ፡ የክልል ፡ ማዕረግ ፡ ይዛ ፡ ትገኛለች። አብዛኞቹን ፡ የሀገሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ የሚናገሩ ፡ ክርስቲያኖች ፡ እና ፡ ሙስሊሞች ፡ የሚኖሩባት ፡ ከተማ ፡ ናት። ከባሕር ፡ ጠለል ፡ በ2500 ፡ ሜትር ፡ ከፍታ ፡ ላይ ፡ የምትገኘው ፡ ከተማ ፡ በግምት ፡ 2,757,729 ፡ በላይ ፡ ሕዝብ ፡ የሚኖርባት ፡ በመሆኗ ፡ የሀገሪቱ ፡ አንደኛ ፡ ትልቅ ፡ ከተማ ፡ ናት።

ከተማዋ ፡ እቴጌ ፡ ጣይቱ ፡ በመረጡት ፡ ቦታ ፡ ማለትም ፡ በፍል ፡ ውሐ ፡ አካባቢ ፡ ላይ ፡ በባላቸው ፡ በዳግማዊ ፡ ምኒልክ ፡ በ፲፰፻፸፰ (1878) ዓ.ም. ፡ ተቆረቆረች። የሕዝቧ ፡ ብዛት ፡ በያመቱ ፡ 8% (ስምንት ፡ በመቶ) ፡ እየጨመረ ፡ አሁን ፡ አራት ፡ ሚሊዮን ፡ እንደሚደርስ ፡ ይገመታል።

ከእንጦጦ ፡ ጋራ ፡ ግርጌ ፡ ያለችው ፡ መዲና ፡ የአዲስ ፡ አበባ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ መገኛ ፡ ሆናለች። ይህም ፡ በመስራቹ ፡ የቀድሞው ፡ ንጉሠ-ነገሥት ፡ ስም ቀዳማዊ ፡ ኃይለ ፡ ሥላሴ ፡ ዩኒቨርሲቲ ፡ ይባል ፡ ነበር።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኝ የመጀመሪያውና ትልቁ የመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ስምነት የኢትዮጵያን የትምህርት ፋናንና ዕርምጃን እንዲያሳይ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ከመመረቁ በፊት፣ መሠረቱ በንጉሠ ነገሥቱ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. ተጣለ። ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ አዲስ አበባ በመባል ይታወቅ ነበር፤ በኋላም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የዘውዳዊው መንግሥት ሥርዓት ካከተመ በኋላ የተመሠረተው ወታደራዊ መንግሥት አሁን በሚጠራበት ስሙ ሰይሞታል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና አስተዳደሩን ሰድስት ኪሎ በሚገኘው በዋናው ግቢ ያደረገ ሲሆን በአምስት ኪሎ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ሰሜን)፣ በአራት ኪሎ የሳይንስ ፋኩልቲ፣ በስድስት ኪሎ (የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ እንዲሁም የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ)፣ በጥቁር አንበሳ (የህክምና ፋኩልቲ ) በልደታ (የቴክኖሎጂ ፋኩለቲ-ደቡብ)፣ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ፣ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት፣ የጥርስ ህክምና ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም በደብረዘይት ከተማ የእንሰሳት ህክምና ፋኩልቲን ያስተዳድራል።

አዲስ አበባ በስሩ የሚከተሉትን ፋኩልቲዎች እና ኢንስቲቲዩቶች ይዟል፦

ኤሽኑና

ኤሽኑና የሱመር ጥንታዊ ከተማ ነበር። ዛሬው ሥፍራው ተል አስማር ተብሎ በዘመናዊው አገር ኢራቅ ውስጥ በዲያላ ወንዝ ሸለቆ ይገኛል። ኤሽኑና ከስሜኑ ተራሮች ወደ መስጴጦምያ በደረሰው መንገድ ላይ ስለተቀመጠ የብርቅ ሸቀጦች (ፈረስ፣ ሰንፔር፣ ዕንቁዎች ወዘተ.) ንግድ ማዕከል ሆነና በለጸገ።

የአካድ መንግሥት እየደከመ (በሹዱሩል ዘመን 2001-1986 ዓክልበ. ግ.) ኤሽኑና በአካድ ቅሬታ ግዛት ውስጥ እንደ ቀረ ይታወቃል። ከዚያ የኤላም ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ያዘው። ከዚህ በኋላ ለዑር መንግሥት ተገዥ ሆነ፤ ከዚያ በተራው ለኢሲንና ለላርሳ ተገዛ። አንዳንድ የኤሽኑና ገዢ ግን እንደ ነጻ ንጉሥ ይገዛ ነበር። 2 ኢፒቅ-አዳድ 1771-1729 ዓክልበ. በተለይ ለኤሽኑና ሰፊ ግዛት አሸነፈ። በመጨረሻ በ1674 ዓክልበ. ኤሽኑና ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ወደቀ።

የኤሽኑና ሕግጋት ደግሞ ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል፤ የትኛው ንጉሥ እንዳወጣቸው ግን እርግጥኛ አይደለም።

ዋሺንግተን ዲሲ

ዋሺንግተን ዲሲ (እንግሊዝኛ፦ Washington D.C.) የአሜሪካ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 570,898 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 38°55′ ሰሜን ኬክሮስ እና 77°00′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የእንግሊዝ ሰዎች መጀመርያ በአካባቢው በደረሱ ወቅት (1600-1660 ዓ.ም.) በአሁኑ ዲሲ ሥፍራ ናኮችታንክ የተባለ የኗሪዎች ታላቅ መንደርና ንግድ ማዕከል ተገኘ። የአሁኑ ዋሺንግተን ከተማ የአሜሪካ አዲስ ልዩ ዋና ከተማ እንዲሆን በ1783 ዓ.ም. ተመሠረተ። በ1792 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ በይፋ ከፊላዴልፊያ ወደ ዋሺንግተን ተዛወረ።

የከተማው ስም «ዋሺንተን» የአገሩን መጀመርያውን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሺንግተንን ያከብራል። «ዲሲ» (D.C.) ማለት በእንግሊዝኛ ለ«ዲስትሪክት ኦቭ ኮሎምቢያ» (District of Columbia ወይም የኮሎምቢያ ክልል) አጭር ነው።

ዓለም ንግድ ሕንጻ

የዓለም ንግድ ሕንጻ (World Trade Center) በኒው ዮርክ ከተማ የነበሩ ሰባት ሕንጻዎች ነው። ሕንጻዎቹን የነደፈው ጃፓናዊ-አሜሪካዊው ሚኖሩ ያማሳኪ ነው።

110 ፎቅ ላላቸው መንታ ሕንጻዎቹ ይታወቃል። የየካቲት 19 ቀን 1985 ዓ.ም. ጥቃት ቢቋቋምም በመስከረም 1 ቀን (ሴፕቴምበር 11) 1994 በደረሰበት ጥቃት ፈርሷል።

ዚምባብዌ

የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት።

ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማብዌ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው።

የአለም ንግድ ድርጅት

የአለም ንግድ ድርጅት (እንግሊዝኛ፦ WTO ወይም World Trade Organization) በዠኔቭ ስዊስ የተመሠረተ ድርጅት ሲሆን 164 አባላት አገራትና 23 ተመልካች መንግሥታት አሉት። ኢትዮጵያም ከተመልካች መንግሥታት መካከል ነች።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.