ብራዚል


ብራዚልደቡብ አሜሪካ በመሬት ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት አንደኛዋ ትልቅ አገር ነች። በአለም አንደኛ ቡድን በእግር ኳስ አላት።

República Federativa do Brasil
የብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ

የብራዚል ሰንደቅ ዓላማ የብራዚል አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር የብራዚል ብሔራዊ መዝሙር
Hino Nacional Brasileiro

የብራዚልመገኛ
ዋና ከተማ ብራዚሊያ
ብሔራዊ ቋንቋዎች ፖርቱጊዝ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
 
ሚሸል ቴሜር
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
8,547,403 (5ኛ)
.65
የሕዝብ ብዛት
የ2017 እ.ኤ.አ. ግምት
 
207,350,000 (6ኛ)
ገንዘብ ሬያል
ሰዓት ክልል UTC -3
የስልክ መግቢያ +55
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ .br

ቋንቋዎች

ይፋዊ ቋንቋ ፖርቱጊዝ ሲሆን መነጋገሪያው ግን በፖርቱጋል ከሚነገረው መደበኛ ፖርቱጊዝ እንደ ቀበሌኛ ትንሽ ይለያል። ከዚያ በቀር ብዙ የጥንታዊ ኗሪዎች ልሳናት የሚችሉ ጎሣዎች ይገኛሉ። አንዳንድ ማህበረሠብ ደግሞ ጀርመንኛን ወይንም ጣልኛን ይናገራል።

ባሕል

የብራዚል ብሔራዊ ጭፈራ ሳምባ ይባላል። ሳምባ እግሮቹ በፍጥነት የሚፈራረቁበት ጭፈራ ነው። የብራዚል ዘመናዊ ሙዚቃ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፤ አንዱ አይነት ቦሦ ኖቫ የሚባለው ነው። ቦሦ ኖቫ በ1950ዎቹሪዮ ደ ጃኔይሮ ከተማ የተለማ እንደ ጃዝ ሙዚቃ የመሰለ ሙዚቃ ዘውግ ነው።

ኗሪዎቹ ለእግር ኳስ ያላቸው ፍቅር አይበለጠም። ብዙ ሚሊዮን አድናቂዎች አሉት።

ሜላሊን

ሜንተሊን (በእስፓንኛ: Medellín) የአንቲቶቢሊያ ክፍል ዋና ከተማ ኮሎምቢያ ማዘጋጃ ቤት ነው. ይህ በመምሪያው ውስጥ በጣም የተጨናነቀች ከተማ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ነው.

ሪዮ ዴ ጃኔይሮ

ሪዮ ዴ ጃኔይሮ (በፖርቱጋልኛ: Rio de Janeiro፣ ሲተረጎም፦ የጃንዋሪ ወንዝ) የብራዚል ሪዮ ዴ ጃኔይሮ ክፍላገር ዋና ከተማ ነው። ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉት። ከ1755 እስከ 1952 ዓ.ም. ድረስ የብራዚል ዋና ከተማ ሲሆን በ1952 ዓ.ም. የብራዚል መንግሥት ወደ ብራዚሊያ ተዛወረ።

ሳው ፓውሉ

ሳው ፓውሉ (ፖርቱጊዝ፦ São Paulo) በህዝብ ብዛት የብራዚል ትልቁ ከተማ ነው። ስያሜው በፖርቱጊዝ «ቅዱስ ጳውሎስ» ማለት ነው። ከተማው የሳው ፓውሉ ክፍላገር ርዕሰ ከተማ ነው።

የፖርቱጋል ሰዎች የመሠረቱት በ1546 ዓ.ም. ነበር።

ሳው ፓውሉ (ክፍላገር)

ሳው ፓውሉ ከብራዚል ክፍላገራት አንዱ ሲሆን የአገሩ ዋና ኢንዱስትሪያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማዕከል ነው። ክፍላገሩ ለቅዱስ ጳውሎስ የተሰየመ ሲሆን በሕዝብ ቁጥር ከአገሩ ትልቁ ነው። የሳው ፓውሉ ርዕሰ ከተማ ሳው ፓውሉ በደቡብ አሜሪካ ትልቁ ከተማ ነው።

በሎሪዞንቺ

በሎሪዞንቺ (በፖርቱጋልኛ: Belo Horizonte፣ ሲተረጎም፦ መልካም አድማስ) የብራዚል ከተማ ነው። ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉት።

ብሔራዊ ማህደሮች (ብራዚል)

ብራዚል ብሔራዊ ቤተ መዛግብት የፋይል አስተዳደር ስርዓት ብራዚል ውስጥ (SIGA) ማዕከላዊ አካል ነው. ይህም ጥር 2, 1838 የተቋቋመው እና ሪዮ ዴ ጄኔሮ ላይ የተመሠረተ ነው. 8 Archives ሕግ (ሕግ 8159) ጥር 1991 መሠረት, ይህ ግዛት እና ዜጎች ማገልገል, ሱቅ, ለማደራጀት ለማቆየት; መዳረሻ ይስጡ እና የፌዴራል መንግስት የ ጥናታዊ ቅርስ ለማስተላለፍ ግዴታ አለው. ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ስብስብ የጽሑፍ ሰነዶችን 55 ኪሜ ይዟል; 2,240,000 ፎቶግራፎች እና አሉታዎች; 27,000 ስዕሎች, ካርቶኖች, 75,000 ካርታዎች እና ፕላኖች; 7000 መዛግብት እና 2000 መግነጢሳዊ ቴፕ ድምፅ; ፊልም መካከል 90,000 ማንከባለል እና 12,000 የቪዲዮ ካሴቶች. በተጨማሪም በታሪክ, በመዝገብ, በመረጃ ሳይንስ, በአስተዳደር ሕግ እና በሕዝብ አስተዳደሩ ላይ የተሰማሩ ቤተ-መጻህፍት አለው, ከ 43,000 መጽሐፎች እና መጻሕፍት, 900 ጋዜጦች እና 6,300 አልፎ አልፎ.

ብራዚሊያ

ብራዚሊያ የብራዚል ዋና ከተማ ነው። በ2013 እ.ኤ.አ. የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 2,789,761 ሆኖ ይገመታል። ይህም በብራዚል ውስጥ በሕዝብ ብዛት አራተኛው ትልቅ ከተማ ያረገዋል። ከተማው 15°45′ ደቡብ ኬክሮስ እና 47°57′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

አራራ፣ ብራዚል

አራራ፣ (ፖርቱጊዝ፦ Arara) የብራዚል ከተማ ነው።

አናናስ

ኣናናስ Ananas comosus ኢትዮጵያ ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኝ ተክል ነው።

መጀመርያ በቅድመ-ታሪክ የታረሰበት ቦታ በደቡብ ብራዚል-ፓራጓይ ጠረፍ ዙሪያ እንደ ነበር ይታመናል። ከ1500 ዓም በኋላ የፖርቱጋል እና እስፓንያ መርከበኞች አለም ዙሪያ አስፋፉት።

ኩሪቺባ

ኩሪቺባ (ፖርቱጊዝ፦ Curitiba) የብራዚል ከተማ ነው።

ካሪቢያን ባሕር

ካሪቢያን ባሕር የአትላንቲክ ውቅያኖስ ባህር ነው። ከስሜን አሜሪካና ደቡብ አሜሪካ መካከል ይገኛል፤ በበሕሩ ውስጥ አያሌው ደሴቶችና አገራት አሉ። መላው ባሕርና በውስጡ ያሉት ደሴቶች የካሪቢያን ዙሪያ ይባላል።

የስልክ መግቢያ

የስልክ መግቢያ ቁጥር በየሃገሩ ይለያል።

የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን

የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ፖርቱጊዝ፦ Confederação Brasileira de Futebol, CBF) የብራዚል እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። ማህበሩ የብራዚል ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንንና የተለያዩ ብሔራዊ ውድድሮችን ያዘጋጃል።

የዓለም ዋንጫ

የዓለም ዋንጫ በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር አባል አገሮች የወንድ እግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚከናወን ውድድር ነው። ከ፲፱፻፳፪ ዓ/ም ጀምሮ በየአራት ዓመቱ ይካሄዳል። ነገር ግን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ምክንያት የ፲፱፻፴፬ ዓ/ም እና የ፲፱፻፴፰ ዓ/ም ውድድሮች ሲሰረዙ እስካሁን አሥራ ዘጠኝ ውድድሮች ተካሂደዋል። የዋንጫና ደረጃ ጨዋታዎቹ በዓለም በብዙ ተመልካቾች ከሚታዩ የስፖርት ዝግጅቶች አንደኛ ነው። በደቡብ አፍሪቃ የተካሄደው የ ፳፻፪ቱ ፲፱ ኛው የዋንጫ ውድድር በ ፩ ነጥብ ፩ ቢሊዮን ሰዎች እንደታየ ይገመታል።

ደቡብ አሜሪካ

ደቡብ አሜሪካ በአለም ካርታ ላይ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ወደ ምእራብ የሚገኝ አህጉር ነው።

ፓውሎ ኮሄሎ

ፓውሎ ኮሄሎ (ፖርቱጊዝ፦ Paulo Coelho) የብራዚል ጸሓፊና ባለቅኔ ናቸው።

ደቡብ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች
South America (orthographic projection)

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.