ሰሜን

ሰሜን የሚለው ቃል ስም፣ የስም ገላጭ ወይም የግሥ ገላጭ ሊሆን ይችላል፣ ከአራቱ ዋና ዋና የአቅጣጫ መጠሪያዎች አንዱ ነው። ይህ አቅጣጫ ለደቡብ ተቃራኒ ሲሆን ለምስራቅ እና ለምዕራብ ደግሞ ቀጤ ነክ ነው። እንደ ስምምነት ሁኖ የማንኛውም ካርታ የላይኛው ክፍል ሰሜን ተደርጎ ይወሰዳል።

ደግሞ ይዩ፦ ስሜን ዋልታ

Compass Rose English North
ኮምፓስ የተቀባው ሰሜንን ያመለክታል።
ሩሲያ

ሩሲያ (መስኮብኛ፦ Россия /ሮሲያ/) ወይም የሩሲያ ፌዴሬሽን (መስኮብኛ፦ Российская Федерация /ሮሲስካያ ፍየድየራትሲያ/) በአውሮፓ እና እስያ አህጉሮች ውስጥ የምትገኝ አገር ናት። በ17,075,200 ካሬ ኪ.ሜ. ከዓለም በመሬት ስፋት አንደኛ ስትሆን በሕዝብ ብዛትም ከዓለም ስምንተኛ ናት። ሩስያ ከኖርዌ፣ ፊንላንድ፣ ኤስቶኒያ፣ ሌትላንድ (ላቲቪያ)፣ ሊትዌኒያ፣ ፖላንድ፣ ቤላሩስ፣ ዩክሬን፣ ጆርጂያ፣ አዘርባይጃን፣ ካዛኪስታን፣ የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ፣ ሞንጎሊያ እና ሰሜን ኮሪያ ጋር ድንበር አላት።

ሩሲያ በጠፈር እና በጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ በጣም የተራቀቀች ናት፡፡

ሮማ

ሮማ ወይም ሮሜ (ጣልያንኛ፦ Roma) የጣሊያን ዋና ከተማ ነው።

በጥንታዊ አፈ ታሪክ መሠረት፣ ከተማው የተሠራው በመንታ ወንድማማች ሮሙሉስና ሬሙስ በ761 ዓክልበ. ነበረ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 4,013,057 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 2,705,603 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 41°48′ ሰሜን ኬክሮስ እና 12°36′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ደግሞ ይዩ፦ የሮሜ መንግሥት

ስሜን ቆጵሮስ

ስሜን ቆጵሮስ (በይፋ፦ «የቱርክ ስሜን ቆጵሮስ ሪፐብሊክ»፤ ቱርክኛ፦ Kuzey Kıbrıs /ኩዘይ ክብርስ/) በቆጵሮስ ደሴት ላይ የምትገኝ አገር ናት።

በሐምሌ 8 ቀን 1966 ዓም የቆጵሮስ ግሪኮች ወገን የቆጵሮስ መንፈቅለ መንግሥት ስላካሄዱ፣ ስለዚህ በ13 ሐምሌ የቱርክ ሥራዊት በስሜን ወረረ፣ ጦርነቱም ከጨረሰ በኋላ የቱርኮች ወገን አስተዳደር በስሜኑ፣ የግሪኮችም በደቡቡ ቀርተው ነበር። በ1967 ዓም ስሜኑ «የቱርክ ቆጵሮስ ፌዴራላዊ ግዛት» ሆነ፣ በ1976 ዓም «የቱርክ ስሜን ቆጵሮስ ሪፐብሊክ» ሆነ።

ሆኖም ከቱርክ አገር በስተቀር፣ ከአንዳችም ሌላ አገር ምንም ዲፕሎማቲክ ተቀባይነት የለውም። በተረፈ ሌሎቹ አገራት በይፋ በደቡብ የሚገኘውን የቆጵሮስ ሪፐብሊክን ይግባኝ ይቀበላሉ።

ምጣኔ ሀብቱ በተለይ በቱሪስም ይመሰረታል፤ ቱሪስቶቹ ወይም በአየር ከቱርክ አገር፣ ወይም በመርከብ ይገባሉ። በግል ጀልባ (ያሕት) የሚገቡም አሉ። ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ምርቶች የወተት ውጤቶች፣ ሎሚ፣ አረቄ፣ ዶሮ፣ ድንች ናቸው። ሕዝቡ ቱርክኛ ይናገራልና የእስልምና ተከታዮች ናቸው። ዋንኛው እስፖርት እግር ኳስ ነው። ባሕላቸው በጭፈራና በሙዚቃ፣ በሥነ ጥበብ፣ በአበሳሰል ወዘተ. እንደ ቱርክ አገር ባሕል ይመስላል።

ስሜን አሜሪካ

ሰሜን አሜሪካ በአለም ካርታ ላይ ወደ ምእራብ በኩል የሚገኝ አህጉር ነው።

ስሜን ኮርያ

ሰሜን ኮርያ በሙሉ መጠሪያ የኮርያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኮርይኛ፡ 조선민주주의인민공화국) በምስራቅ እስያ የምትገኝ ሀገር ስትሆን የኮርያን መሬት የሰሜን ክፍል ትይዛለች። የዚች ሀገር ዋና ከተማ መጠሪያ ፒዩንግያንግ ነው። በሁለቱ ኮርያዎች ማለትም በደቡብ ኮርያ እና ሰሜን ኮርያ መካከል እንደ ድንበር ሁኖ የሚያገለግል የጦር ቀጠና አለ። የአምኖክ ወንዝ እና የቱመን ወንዝ በሰሜን ኮርያ እና በቻይና መካከል እንደ ድንበር ሁነው ያገለግላሉ። ወደሰሜን ርቆ የሚገኘው የቱመን ወንዝ ክፍል ደግሞ ከሩስያ ጋር ለሚኖራት ድንበር ሆኖ ያገለግላል።

ስሜን ኮርያ የተባባሪ መንግሥታት አባል ቢሆንም፣ ከሁለት ሌሎች አባላት እነርሱም ደቡብ ኮርያና ጃፓን ዲፕሎማቲክ ተቀባይነት የለውም።

ቦትስዋና

ቦትስዋና ወይም በይፋ የቦትስዋና ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ: Republic of Botswana ሰጿና፡ Lefatshe la Botswana) በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ አገር ናት። ቦትስዋና የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛት ስትሆን ነፃነቷን በመስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፱ ዓ.ም. ከተቀዳጀች በኋላ መሪዎቿ በነፃ ዴሞክራሲያዊ ምርጫዎች ተመርጠዋል።

ቦትስዋና ሜዳማ ስትሆን ከሰባ ከመቶ በላይ በካለሃሪ በርሃ የተሸፈነች ናት። በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ አፍሪካ፣ በምዕራብና ሰሜን ከናሚቢያ እና በሰሜን ምሥራቅ ከዚምባብዌ ጋር ትዋሰናለች። ከዛምቢያም ጋር በደንብ ያልተወሰነ ቢበዛ በመቶ ሜትር የሚቆጠር ወሰን አላት።

አማራ (ክልል)

አማራ (ክልል 3) ከዘጠኙ የኢትዮጵያ ክልሎች አንዱ ሲሆን ከ 1994 በፊት አራት የሀገሪቱን ዋና ወና ክፍለ ሀገራት የ ካትት ነበር እነሱም በጌምድር ጐጃም ወሎና ሸዋ ነበሩ ።የአማራ ብሔራዊ ክልል ጅኦግራፊያዊ አቀማመጥ በ8° 45 እስከ 13° 45 ሰሜን የኬንትሮስ እና በ35° 46 እስከ 40° 25 ምስራቅ የኬንትሮስ መስመር ውስጥ ይገኛል። በምስራቅ የአፋርና የኦሮሚያ ክልሎች፣ በምዕራብ ሱዳን እና ቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል፣ በሰሜን የትግራይ ክልልና በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል። የቆዳ ስፋቱ ፻፶፯ሺ፸፮ ካሬ ሜትር ሲሆን ከአገሪቱ አሥራ አምስት በመቶ ድርሻ ይይዛል። የክልሉ ሕዝብ ብዛት ደግሞ በ፳፻፪ ዓ/ም 20,875,456 እንደነበር የተገመተ ሲሆን ከአገሪቱ ጠቅላላ ሕዝብ 33.9% አካባቢ ድርሻ ይይዛል ተብሎ ይገመታል። ክልሉ በ፲ ዞኖችና በ፻፷፮ የገጠርና የከተማ ወረዳ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ፴፰ የሚሆኑት የከተማ አስተዳደሮች ናቸው።የአማራ፣የአገው፣የኦሮሞና የሌሎች ብሔረሰቦች በጋራ የሚኖሩበት ክልል ነው።

አርባ ምንጭ

አርባ ምንጭ በኢትዮጵያ የደቡብ ብሄር ብሄረስቦችና ሕዝቦች ክልል ከተማ ሲሆን በጋሞጎፋ ዞን (ቀድሞ ሰሜን ኦሞ ዞን)ና በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ይገኛል።

በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ72,507 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 36,296 ወንዶችና 36,211 ሴቶች ይገኙበታል።በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ68,816 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ6°2′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°33′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

አክሱም

አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት በፊት ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች

የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ።

ሰባ አምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ነው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስጥ የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይመዋል ።

አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል።

በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ47,320 ሰው መኖሪያ ሲሆን እነሱም 23,542 ወንዶችና 23,778 ሴቶች ይገኙበታል።በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ41,197 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ14°07′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ወይም በይፋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝ የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በአፍሪካ ነፃነታቸውን ጠብቀው ለመኖር ከቻሉ ሁለት አገሮች አንዷ ነች። በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ስትሆን ፣ በቆዳ ስፋት ደግሞ አስረኛ ናት። ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ናት።

አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ዕድሜያቸው ከአንድ ምዕተ-ዓመት የሚያንስ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያ ግን ከጥንት ጊዜ ጀምሮ በንጉሠ-ነገሥታት እና ንግሥተ-ነግሥታት የተመራች ሀገር ናት። የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት የአመጣጡን ዘር እስከ አስረኛው ዓመተ-ዓለም ድረስ ይቆጥራል። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃ ተግኝቷል። በበርሊን ጉባኤ በኩል የአውሮፓ ሀያላት ሀገሮች አፍሪካን ሲከፋፍሏት፣ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ጠብቃለች። የሊግ ኦፍ ኔሽንስ (League of Nations) አባል ከነበሩት ሶስት የአፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነበረች። ከአጭር የኢጣልያ ወረራ ጊዜ በኋላም ከየተባበሩት መንግሥታት መሥራቾች አንዷ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ብዙ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን ሲያገኙ፣ ሰንደቅ-አላማቸውን በኢትዮጵያ ቀለሞች ማለትም በአረንጓዴ ፣ ቢጫ እና ቀይ ላይ ነው የመሠረቱት። አዲስ አበባ ደግሞ ለየተለያዩ በአፍሪካ ላይ ላተኮሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ ሆነች።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ የትልቅ የግዛት ለውጥ ውጤት ናት። ከሰሜን ግዛቱዋ በጣም የተቀነሰ ሲሆን በደቡብ በኩል ደግሞ ተስፋፍቷል። በ ፲፱፻፷፯ (1967) ዓ.ም.፣ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ሲወርዱ፣ የእርስ በርስ ጦርነት በሀገሩ ተባባሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢትዮጵያ በተለያዩ የመንግሥት አይነቶች ተዳድራለች። ዛሬ አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት (African Union) እና የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ለአፍሪካ መቀመጫ ናት። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከአፍሪካ ኃያል ሠራዊቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ በአፍሪቃ የእራሷ ጥንታዊ ፊደል ያላት ሀገርም ናት።

ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። ሶፍ ዑመር ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ ዳሎል ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም ኦሮሞና አማራ በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የቡና ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና ማር አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።

ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። ክርስትናን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሁለተኛው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ነው። የመጀመሪያው የእስላም ሂጅራ ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። ነጋሽ በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ ቤተ-እስራኤሎች በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የናይል(ኣባይ) ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው።

እስያ

እስያ የአለም ትልቁ አህጉር ነው።

ስሙ «እስያ» የወጣ ከግሪክ Ασία (/አሲያ/) ሲሆን መጀመርያ በጽሕፈት የተገኘው በሄሮዶቶስ ታሪክ መጻሕፍት ውስጥ ነበር። በሄሮዶቶስ ዘንድ እስያ ማለት አናቶሊያ (ትንሹ እስያ) ወይም ፋርስ መንግሥት ግዛት ነበረ። ሄሮዶቶስ ስለ ስሙ መነሻ ግን እርግጥኛ አይደለም፤ ግሪኮች እስያ ከፕሮሜጤዎስ ሚስት (ሄሲዮኔ) እንደ ተሰየመ ሲያስቡ፣ ልድያውያን ግን ከኮቱስ ልጅ አሲያስ እንደ ሆነ አሰቡ ይለናል።

ኮርያ

ኮርያ በምሥራቅ እስያ የተገኘ ታሪካዊ አገር ነው። ከ1937 ዓም እስካሁን የኮርያ ልሳነ ምድር በሁለት መንግሥታት ይለያያል፦

ደቡብ ኮርያ

ሰሜን ኮርያ

ዩናይትድ ኪንግደም

ዩናይትድ ኪንግደም (ማለት «የተባበረው ግዛት») በተለመደው እንግሊዝ አገር ሲባል፣ እንዲያውም «እንግሊዝ አገር» (ወይም ደግሞ «ኢንግላንድ» ወይም «አንግልጣር») ከዩናይትድ ኪንግደም ዋና ክፍላገሮች አንዱ ብቻ ነው። ሌሎቹም፦

ስኮትላንድ

ዌልስ

ሰሜን አይርላንድናቸው። ከነዚህም እንግሊዝ፣ ስኮትላንድና ዌልስ አብረው «ታላቋ ብሪታንያ» የምትባል ደሴት ናቸው። ከ1699 ዓ.ም. (1707 እ.ኤ.አ.) አስቀድሞ፣ እንግሊዝና ስኮትላንድ የተለያዩ ንጉዛት ነበሩ። ከ1595 ዓ.ም. ጀምሮ ግን 2ቱ አገራት አንድ ንጉሥ ነበራቸውና በ1699 በመዋሐዳቸው አንድ ላይ «ዩናይትድ ኪንግደም» ሆነዋል።

ከዚህም በላይ እስካሁን አንዳንድ ባዶ ማዶ ግዛቶች አሏት።

ደብረ ማርቆስ

ደብረ ማርቆስ በኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልል የምትገኝ ሲሆን የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ናት። እንዲሁም ከተማዋ የ ጉዛምን ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት።

በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ85,597 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 43,229 ወንዶችና 42,368 ሴቶች ይገኙበታል።

መገኛ

የደብረማርቆስ ከተማ የምትገኘው በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ከአዲስ አበባ በ 300 ኪ.ሜ ከባህር ዳር ደግሞ 253 ኪ.ሜ ፣ በ 37021’ ሰሜን ላቲቲውድ እና 37º 43’ ምስራቅ ሎንግቲውድ ነው፡፡

አመሰራረት

ደብረማረቆስ ከተማ የጎጃም ገዥ በነበሩት ደጃዝማቸ ተድላ ጓሉ በ1845 ዓም የተቆረቆረች ሲሆን የከተማዋም መጠሪያ መንቆረር ይባል ነበር፡፡ በ 1872 ዓም ወደ ሥልጣን የመጡት ንጉስ ተክለሃይማኖት ካሁኑ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መመስረት ጋር ተያይዞ የከተማዋ ስያሜ መንቆረር መባሉ ቀርቶ ደብረ ማረቆስ እንዲሆን አዋጅ በማስነገራቸው የከተማዋ መጠሪያ ሊሆን በቃ፡፡ ደብረማርቆሰ በክልሉ ከሚገኙ የሪፎርም ከተሞች አንዷ ስትሆን ከተማዋ በስሯ 6 ቀበሌዎችና ማዘጋጃ ቤት ያሉት የከተማ አስተዳደር አላት፡፡ በ2002 ዓ.ም የተዘጋጀ የተቀናጀ ልማት ፕላን አላት፡፡

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ60,796 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል:: የከተማው አቀማመጥ በ10°20′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°43′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። ደብረ ማርቆስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመሰረተ ልማት እየተሟላላት ነው። ከተማዋ አዲስ ድረገጽ ከፍታለች።

ስዩም ይዘንጋው ድንቁ (talk) 14:14, 23 ጁላይ 2019 (UTC)

ደብረ ዘይት

ቢሾፍቱ ወይም ደብረ ዘይት በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በምስራቅ ሸዋ ዞንና በአድአ ጨዘላ ወረዳ ይገኛል።

በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ131,159 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 64,642 ወንዶችና 66,517 ሴቶች ይገኙበታል።በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ104,537 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ8°45′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°59′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

ደገሃቡር

ደገሃቡር በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ከተማ ሲሆን በደገሃቡር ዞንና በደገሃቡር ወረዳ ይገኛል።

በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ42,815 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 22,670 ወንዶችና 20,145 ሴቶች ይገኙበታል።የከተማው አቀማመጥ በ8°13′ ሰሜን ኬክሮስ እና 43°33′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።

ግዕዝ

ግዕዝ ፡ በአፍሪካ ቀንድ ፡ በኢትዮጵያና ፡ በኤርትራ ፡ በጥንት ፡ የተመሠረተና ፡ ሲያገለግል ፡ የቆየ ፡ ቋንቋ ነው። የግዕዝ ፡ አመጣጥ ፡ በግምት ፡ የዛሬ ፡ ፫ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ከየመን ፡ እና ፡ ደቡብ ፡ አረቢያ ፡ በመነሣትና ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ በመሻገር ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከሰፈሩ ፡ የተለያዩ ፡ የሳባውያን ፡ ነገዶች ፡ ቋንቋና ፡ በጊዜው ፡ ሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይነገሩ ፡ በነበሩ ፡ ቋንቋዎች ፡ ዘገምተኛ ፡ ውኅደት ፡ ነው። በአክሱም ፡ መንግሥትና ፡ በኢትዮጵያ ፡ መንግሥት ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነበር።

ግዕዝ ፡ ከአማርኛና ፡ ሌሎች ፡ ኢትዮ-ሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ጋር ፡ ሲወዳደር ፡ «ንጹሕ» ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ እስከ ፡ ፲ኛው ፡ ክፍለ-ዘመን ፡ መጀመሪያ ፡ ድረስ ፡ ዋነኛ ፡ የመግባቢያ ፡ ቋንቋና ፡ ልሳነ ፡ ንጉሥ ፡ ነበር። ከ ፲፫ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ ፡ ግን ፡ ሙሉ ፡ በሙሉ ፡ መነገር ፡ አቁሞ ፡ በሰሜን ፡ ኢትዮጵያ ፡ በትግርኛ ፡ እንዲሁም ፡ በማዕከላዊው ፡ ክፍል ፡ ደግሞ ፡ በአማርኛ ፡ ተተካ። ዛሬ ፡ በኢትዮጵያ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሥነ-ስርዓት ፡ እንዲሁም ፡ በኤርትራ ፡ ኦርቶዶክስ ፡ ተዋሕዶ ፡ ቤተክርስቲያን ፣ በኢትዮጵያ ፡ ካቶሊክ ፡ ቤተክርስቲያን እና ፡ በቤተ-እስራኤል ፡ ሥነ-ስርዓቶች ፡ ይሰማል።

ቋንቋው ፡ የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ አባል ፡ እየሆነ ፡ በደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ ቅርንጫፍ ፡ ውስጥ ፡ ይካተታል። ደቡብ ፡ ሴማዊ ፡ በመባሉ ፡ ግዕዝ ፡ የሣባ ፡ ቋንቋ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ግዕዝ ፡ የተጻፈው ፡ በግዕዝ ፡ ፊደል ፡ አቡጊዳ ፡ ነው። ይህም ፡ ፊደል ፡ ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ለአማርኛ ፣ ለትግርኛ ፡ እና ፡ ለሌሎችም ፡ ቋንቋዎች ፡ ይጠቀማል። በመላውም ፡ የአፍሪቃ ፡ አህጉር ፡ ውስጥ ፡ የመጀመሪያውና ፡ ብቸኛ ፡ አፍሪቃዊ ፡ የራሱን ፡ ፊደላት ፡ የያዘ ፡ ቋንቋ ፡ ሲሆን ፣ በዓለምም ፡ ላይ ፡ ዋናና ፡ የስልጣኔ ፡ አራማጅ ፡ ከሚባሉት ፡ ቋንቋዎች ፡ አንዱ ፡ ነው።

በግዕዝ ፡ ጽሕፈት ፡ ፳፮ ፡ ፊደላት ፡ ብቻ ፡ ይጠቀሙ ፡ ነበር ፤ እነርሱም፦

ሀ ፣ ለ ፣ ሐ ፣ መ ፣ ሠ ፣ ረ ፣ ሰ ፣ ቀ ፣ በ ፣ ተ ፣ ኀ ፣ ነ ፣ አ ፣ ከ ፣ ወ ፣ ዐ ፣ ዘ ፣ የ ፣ ደ ፣ ገ ፣ ጠ ፣ ጰ ፣ ጸ ፣ ፀ ፣ ፈ ፣ ፐ

ናቸው።

ሊቁ ፡ ሪቻርድ ፓንኩርስት ፡ እንደሚጽፍ ፣ አንድ ፡ ተማሪ ፡ በመጀመርያው ፡ አመት ፡ ፊደሉን ፡ ከተማረ ፡ በኋለ ፣ በሚከተለው ፡ አመት ፡ መጀመሪያይቱ ፡ የሐዋርያው ፡ የዮሐንስ ፡ መልእክትን ፡ ከአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግዕዝ ፡ ከትዝታ ፡ ለመጻፍ ፡ መማር ፡ ነበረበት። በሦስተኛው ፡ ደረጃ ፡ የሐዋርያት ፡ ሥራ ፡ በአራተኛውም ፡ መዝሙረ ፡ ዳዊት ፡ በግዕዝ ፡ ማስታወስ ፡ ነበረበት። ይህንን ፡ ከጨረሰ ፡ ታላቅ ፡ ግብዣ ፡ ይደረግና ፡ ልጁ ፡ ጸሐፊ ፡ ይሆን ፡ ነበር።

በብሪቲሽ ፡ ቤተ-መጻሕፍት ፡ (የእንግሊዝ ፡ አገር ፡ ብሔራዊ ፡ ቤተ-መጻሕፍት) ፡ ውስጥ ፡ ፰፻ ፡ የሚያሕሉ ፡ የድሮ ፡ ግዕዝ ፡ ብራናዎች ፡ አሉ።

በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ፡ ትምህርቶች ፡ ዘንድ ፣ ግዕዝ ፡ የአዳምና ፡ የሕይዋን ፡ ቋንቋ ፡ ነበር። ፊደሉን ፡ የፈጠረው ፡ ከማየ አይኅ ፡ አስቀድሞ ፡ የሴት ፡ ልጅ ፡ ሄኖስ ፡ ነበረ። ከባቢሎን ፡ ግንብ ፡ ውድቀት ፡ በኳላ ፣ ከአርፋክስድ ፡ ወገን ፡ የዮቅጣን ፡ ልጆች ፡ ቋንቋውን ፡ እንደ ፡ ጠበቁት ፡ ይባላል። የዮቅጣን ፡ ልጅ ፡ ሣባ ፡ ነገዶች ፡ ከዚያ ፡ ቀይ ፡ ባሕርን ፡ አሻግረው ፡ ወደ ፡ ዛሬው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ያስገቡት ፡ ይታመናል። እንዲሁም ፡ ካዕብ ፡ እስከ ፡ ሳብዕ ፡ (አናባቢዎችን ፡ ለመለየት) ፡ ወደ ፡ ፊደል ፡ የተጨመረበት ፡ ወቅት ፡ በንጉሥ ፡ ኤዛና ፡ ዘመን ፡ እንደ ፡ ነበር ፡ ይባላል።

ጎንደር ከተማ

ጎንደር ቀደም ሲል የጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዛሬ የጎንደር ክፍለ ሐገር እና የጥንትዋ ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበር። ጎንደር ክፍለህገር በሰባት አውራጅዎች ይከፈላል። እነዚህም አውራጃዎች ከነዋና ከተማቸው የሚከተሉት ናቸው፤ ወገራ አውራጃ ዋና ከተማው ዳባት፣ ሰሜን አውራጃ ዋና ከተማው ደባርቅ፣ ደብረታቦር አውራጃ ዋና ከተማው ደብረታቦር፣ ሊቦ አውራጃ ዋና ከተማው አዲስ ዘመን፣ ጋይት አውራጃ ዋና ከተማው ንፋስ መውጫ፣ ጭልጋ አውራጃ ዋና ከተማው አይክል፣ ጎንደር ዙሪያ አውራጅ ዋና ከተማው ጎንደር ናቸው።ዛሬ በስሜን ጎንደር ዞን በአማራ ክልል ሲገኝ ከጣና ሃይቅ ሰሜን አንገረብ ወንዝ ላይ ከሰሜን ተራራ ወደ ደቡብ ምእራብ ሰፍሮ ይገኛል። በ12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°28′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው። አጼ ፋሲለደስ ጎንደርን እንደ ዋና ከተማነት ለመጀመሪያ ጊዜ ይጠቀሙ እንጂ ከዚያ በፊት በአካባቢው ሰወች ይኖሩበት እንደነበር ታሪክ አለ። ሆኖም ግን ከተማው በታሪክ የገነነው አጼ ፋሲለደስ በአሁኑ ፋሲል ግቢ ወይም የነገሥታት ግቢ ውስጥ የፋሲል ግንብን በ1636 ሲያንጽ ነበር።

የማእከላዊ እስታቲስቲክ ባለስልጣን በ1998 ቁጥሩ ጎንደር 194,773 የህዝብ ብዛት ስትይዝ ከነሱም 97,625 ወንዶች ሲሆኑ 97,148 ሴቶች ናችው።

ጥቅምት

ጥቅምት የወር ስም ሆኖ በመስከረም ወር እና በኅዳር ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ሁለተኛው የወር ስም ነው።

«ጥቅምት» ከግዕዙ «ጠቀመ» ከሚለው ግስ የተባዛ ነው።በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ፓውፔ ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከበዓሉ ስም «ኦፐት» መጣ («ፓን-ኦፐት» = የኦፐት ወር)።

በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የኦክቶበር መጨረሻና የኖቬምበር መጀመርያ ነው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.