ምዕራብ

ምዕራብ የሚለው ቃል ስም፣ የስም ገላጭ ወይም የግሥ ገላጭ ሊሆን ይችላል፣ ከአራቱ ዋና ዋና የአቅጣጫ መጠሪያዎች አንዱ ነው። ይህ አቅጣጫ ለምስራቅ ተቃራኒ ሲሆን ለሰሜን እና ለደቡብ ደግሞ ቀጤ ነክ ነው። እንደ ስምምነት ሁኖ የማንኛውም ካርታ ግራ ምዕራብ ተደርጎ ይወሰዳል።

Compass Rose English West
ኮምፓስ የተቀባው ምዕራብን ያመለክታል።
ላይቤሪያ

ላይቤሪያ (እንግሊዝኛ፦ Liberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒ፣ ኮት ዲቯር፣ ሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች።

መስከረም

መስከረም የወር ስም ሆኖ በጳጉሜ ወር እና በጥቅምት ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ መጀመርያው የወር ስም ነው።

«መስከረም» ከግዕዙ «ከረመ» ከሚለው ግስ የተባዛ ነው። ሌላ ከቀረቡት ግመቶች መካከል መነሻው «መሰስ-ከረም» (ክረምቱ መሰስ ብሎ ማለፉን)፣ ወይም «መዘክረ-ዓም» (የዓመት መታወሻ) ይባላል።

በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ጦውት ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከጣኦት ስም «ጀሑቲ» መጣ።

በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የሰፕቴምበር መጨረሻና የኦክቶበር መጀመርያ ነው።

ምዕራባዊ አውሮፓ

ምዕራብ አውሮፓ በጠቅላላ የአውሮፓ ምዕራባዊ ክፍሎች ሲሆን፣ አንድ የተወሰነ ትርጒም የለውም።

ብዙ ጊዜ በተግባር «ምዕራብ አውሮፓ» ከሚባሉት አገራት መሃል፦ ኦስትሪያ፣ ቤልጅግ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አይስላንድ፣ አይርላንድ፣ ጣልያን፣ ሉክሳምቡርግ፣ ሆላንድ፣ ኖርዌ፣ ፖርቱጋል፣ እስፓንያ፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድና ዩናይትድ ኪንግደም ይጠቀሳሉ።

ሞሪታኒያ

ሞሪታኒያ (አረብኛ፡ موريتانيا‎) በይፋ የሞሪታኒያ እስላማዊ ሪፐብሊክ፣ በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ ከአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ በደቡብ-ምዕራብ ከሴኔጋል፣ በምሥራቅና ደቡብ-ምሥራቅ ከማሊ፣ በሰሜን-ምሥራቅ ከአልጄሪያ፣ እና በሰሜን-ምዕራብ ከምዕራባዊ ሣህራ ጋር ትዋሰናለች። የአገሩዋ ስም የመጣው ከጥንቱ የሞሪታኒያ መንግሥት ነው። ዋና እና ትልቁዋ ከተማዋ ኑዋክሾት ናት።

ሞሮኮ

ሞሮኮ (አረበኛ፡ المغرب) በሰሜን-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝና በሕገ-መንግሥታዊ የዘውድ ሥርዓት የምትተዳደር የ፴፪ ሚሊዮን ሕዝብ አገር ናት። መግሪብ በምዕራብ ድንበሯ የአትላንቲክ ውቅያኖስ፤ በሰሜን የሜድትራኒያን ባሕር፤በምሥራቅ አልጄሪያ እና በደቡብ ምዕራባዊ ሣህራ ታዋስናለች። የመግሪብ ርዕሰ ከተማ በአገሪቱ በስተ ምዕራብ የምትገኘውና በሕዝብ ብዛት ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ራባት (አማርኛ፡ ርባጥ]] ስትሆን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የአገሪቷ ታላቅ የባሕር ወደብ የሚገኝባት የካዛብላንካ ከተማ እና ጥንታዊቷ ማራኬሽ (አማርኛ፡ ምራክሽ) ሌሎቹ ትላልቅ ከተሞች ናቸው።

ሱዳን

ሱዳን በይፋ የሱዳን ሪፑብሊክ (አረብኛ: السودان) ከአፍሪካ በስፋት ሦስተኛ ስትሆን በአህጉሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ክልል ትገኛለች። ዋና ከተማዋ ካርቱም ነው። ከግብፅ ፣ ከቀይ ባሕር ፣ ከኤርትራ ፣ ከኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከመካከለኛው የአፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ከቻድ ፣ እና ከሊቢያ ጋር ድንበር ትካለላለች። የአባይ ወንዝ (ናይል) ሀገሪቱዋን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ይከፍላል። የአረብ ባህል ደንበኛ ሲሆን አብዛኛው ሕብዝ የእስልምና ዕምነት ተከታይ ነው።

ሱዳን ከግብፅ የተጣመረ ረዥም ታሪክ አላት። የመጀመሪያው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1955 እስከ 1972 እ.ኤ.አ. ከዚያም ሁለተኛው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት ከ1983 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ተከስቷል። በ1989 እ.ኤ.አ. በሰላማዊ መፈንቅለ መንግሥት ኦማር ሀሳን አህመድ አል-በሽር ሥልጣን ላይ የወጡ ሲሆን እራሳቸውን የሱዳን ፕሬዝዳንት ብለው ሾመዋል። የእርስ በርስ ጦርነቱ በሰላም ውል የቆመ ሲሆን ይህ ውል ያኔ የሀገሪቱዋ ደቡባዊ ክፍል ለነበረው ቦታ ራስን የመምራት መብት ሰጥቷል። በጃኑዋሪ 2011 እ.ኤ.አ. በተካሄደው ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት በሱዳን ፈቃድ ደቡብ ሱዳን ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ሉዓላዊ ሀገር ሆነች።ዋና ከተማዋ ካርቱም የሱዳን የፖለቲካ፣ ባህል እና ንግድ ማዕከል ናት። የሀገሪቱዋ መንግሥት በይፋ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንታዊ ሪፐብሊክ ቢሆንም ስልጣን ላይ ያለው ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (National Congress Party) በሁሉም የመንግሥት አካላት ላይ ባለው ጥብቅ ቁጥጥር ምክንያት በብዙ የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ዘንድ መንግሥቱ አምባገነናዊ ተብሎ ይቆጠራል።

ሴኔጋል

ሴኔጋል ወይም የሴኔጋል ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ ሀገር ነው። ሴኔጋል ከምዕራብ በሴኔጋል ወንዝ፣ ከሰሜን በሞሪታንያ፣ ክምሥራቅ በማሊ እና ክደቡብ በጊኒና ጊኒ-ቢሳው ይዋሰናል። የጋምቢያ ግዛት እንዳለ በሴኔጋል ውስጥ ነው የሚገኘው። የሴኔጋል የቆዳ ስፋት 197,000 ካሬ ኪ.ሜ. የሚጠጋ ሲሆን የሕዝብ ብዛቱ ደግሞ ወደ 14 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል። የሴኔጋል የአየር ሁኔታ የየምድር ወገብ ሲሆን ደረቅና ዝናባማ ወራት ተብሎ ወደ ሁለት ይከፈላል።

የሴኔጋል ርዕሰ ከተማ ዳካር በሀገሩ የምዕራብ ጫፍ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። ከባህር ጠረፍ ወደ ፭፻ ኪ.ሜ. ገደማ በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የኬፕ ቨርድ ደሴቶች ይገኛሉ። በ፲፯ኛው ና ፲፰ኛው ክፍለ ዘመናት በቅኝ ገዢ መንግሥታት የተሠሩ የንግድ ተቋማት ከባህር ዳር ይገኛሉ።

ባሕር-ዳር

ባሕር-ዳር በድሮ ስሙ ባሕር ዳር ጊዮርጊስ በሰሜን-ምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የአማራ ክልል ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ በቀድሞው ጎጃም ክፍለ ሓገር ውስጥ ከጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ተቀምጣ ስትገኝ ባህር ዳር እንደ መቀሌና ደሴ የወረዳ ደረጃ ያላት ስፔሻል(ልዩ) ዞን ናት። በማዕከላዊ ስታትስቲክ ትመና የ167,261 ህዝብ ከነሱም መሃከል የ86,355 ወንዶችና የ80,906 ሴቶች መኖሪያ ከተማ ናት። 1700 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ትገኛለች።

ቤኒን

ቤኒን ወይም በይፋ የቤኒን ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከምዕራብ ቶጎን፣ ከምሥራቅ ናይጄሪያን እና ከሰሜን ቡርኪና ፋሶና ኒጄርን ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ ፖርቶ ኖቮ ሲሆን የመንግሥቷ መቀመጫ ግን ኮቶኑ ከተማ ናት። የቤኒን የቆዳ ስፋት ወደ 110,000 ካሬ ኪ.ሜ. ሲሆን የሕዝቧ ብዛት ደግሞ ወደ 9.05 ሚሊዮን ይገመታል።

የቤኒን ይፋ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን እንደ ፎንና ዮሩባ የመሳሰሉት የሀገሪቷ ባህላዊ ቋንቋዎች ሰፊ ተናጋሪ አላቸው። የሮማ ካቶሊክ ክርስትና ብዙ ተከታዮች ሲኖሩት እስላሞች፣ ፕሮቴስታኖችና የቩዱ ተከታዮችም ይገኛሉ። ቤኒን የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እናም ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ናት።

ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. የሀገሪቱ መሬት በዳሆሚ መንግሥት ነበር የሚመራው። በ17ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአትላንቲክ የባሪያ ንግድ በአካባቢው ሰፍቶ ስለነበር ቦታው የባሪያ ጠረፍ ይባል ነበር። በ1892 እ.ኤ.አ. ፈረንሳይ አካባቢውን በመቆጣጠር የፈረንሳይ ዳሆሚ ብላ ሰየመችው። በ1960 እ.ኤ.አ. ዳሆሚ ነፃነቷን በማግኘት ለ፲፪ ዓመታት በዴሞክራሲያዊ መንግሥት ተመርታለች።

ከ1972 እስከ 1990 እ.ኤ.አ. ሀገሪቷ በማርክሲስት ሌኒኒስት አቋም የቤኒን ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ተብላ ተሰመች። በዚህ ጊዜ በሀገሪቷ የኢኮኖሚ ውድቀት ተከስቶ ነበር። በ1991 እ.ኤ.አ. የቤኒን ሪፐብሊክ ተመሠረተ።

ቤኒን ወደ ውጭ የሚልከው ዋንኛ ምርት ጥጥ ሲሆን ከዚህ በላይ ካሸው ለውዝ (Anacardium occidentale)፣ ኮኮነት፣ ዓሳ፣ እንጨት ወደ ውጭ ይላካሉ። ፔትሮሊየምና ወርቅም ይላካሉ። ባለፉት ዓመታት ውስጥ ቤኒን ለተግባራዊ ሳይንስ ምርመራ ጥናት አንጋፋ ማዕከል ሆናለች።

በደቡብ ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ የበቆሎ ዳቦ በኦቾሎኒ ወጥ ወይም በቲማቲም ወጥ ይጠቀማል። አሳ እና ዶሮ ከሁሉ ተራ ሥጋዎች ናቸው፣ በሬ፣ ፍየልና የጫካ አይጥ ደግሞ ይበላሉ። በስሜን ቤኒን ባሕላዊ አበሳሰል፣ በተለይ ኮቴሃሬ በበቆሎው ፈንታ ይጠቀማል። ቤሬ ወይም አሳማ በጥብስ ወይም በወጣወጥ፣ ፎርማጆ፣ ኩስኩስ፣ ሩዝ፣ ባቄላ፣ ፍራፍሬ በሰፊው ይጠቀማሉ።

እግር ኳስ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ቤስቦል ወደ ቤኒን ገብቷል።

ቶጎ

ቶጎ የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ነው። ይፋዊ ብሔራዊ ቋንቋ ፈረንሳይኛ ሲሆን ከ39 ኗሪ ቋንቋዎች በላይ ይገኛሉ። ከነዚህም ሁለቱ ኤዌኛ እና ካቢዬኛ እንደ አገራዊ ልሳናት ዕውቅና ተቀብለዋል።

ከኗሪዎቹ 51% ያህል የባህላዊ አረመኔነት ተከታዮች ናቸው፤ 29% ያህል የክርስትና፣ 20% ያሕል የእስልምና አማኞች ናቸው። የባህላዊ ተከታዮቹ ብዙ የእጅ ሥራዎች፣ የጣኦት ምስል፣ ስጋጃ፣ የወገብ ጨርቅ፣ ሌላ ሥነ ጥበብ ይፈጥራሉ። ብሔራዊ መጠጡ ሶዳቢ ወይም የኮኮነት ዘምባባ አረቄ ይባላል። ከሁሉ የተወደደ እስፖርት እግር ኳስ ሲሆን ብሔራዊ የቅርንጫት ኳስ ቡድን ደግሞ አለ።

ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ ካካው፣ ቡና፣ ጥጥ፣ ፎስፌት፣ ኦቾሎኒ፣ ሲሚንቶ ናቸው።

ኒው ዚላንድ

ኒው ዚላንድ በደቡብ ምዕራብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።

ናሚቢያ

ናሚቢያ በደቡብ-ምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ ሀገር ናት። በምዕራብ በአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በስሜን በአንጎላና በዛምቢያ፣ በምስራቅ በቦትስዋና፣ በደቡብም በደቡብ አፍሪቃ ትካለላለች። በ1982 አመተ ምኅረት ነጻነትዋን ከደቡብ አፍሪቃ ስላገኘች በጣም አዲስ አገር ነች። ዋና ከተማዋ ዊንድሁክ ነው።

አልጄሪያ

አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر‎ አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት።

አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራ፣ ሞሪታኒያና ማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል።

አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ ኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት።

የመን (አገር)

የየመን ሪፑብሊክ በዓረቢያ ምድር ወይንም ፔኒሱላ በደቡብ ምዕራብ እስያ የምትገኝ ሀገር ስትሆን 530,000 ስኩኤር (ካሬ) ኪሎ ሜትር ስፋት እና ከ23 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ነዋሪ አላት። ዋና ከተማዋ ሰንዓ በመባል ይጠራል።እንዲሁም የመን ቸ

ጊኔ-ቢሳው

ጊኔ-ቢሣው የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ነው። የጊኔ-ቢሣው ብሄራዊ ቋንቋ ፖርቱጊዝኛ ሲሆን ፉላኒኛ፣ ባላንታኛ እና ማንዲንግኛ በብሔሮቻቸው ይነገራሉ። የጊኔ ቢሣው ፖርቱጊዝኛ ክሬዮል መደበኛ ነው።

ከሀገሩ ኗሪዎች 45% ያህል የእስልምና ተከታዮች (በተለይ ሱኒ)፣ 22% ያህል የክርስትና አማኞች (በተለይ ካቶሊክ)፣ 31 % አካባቢ ኗሪ አረመኔ እምነቶችን ይከተላሉ። በጊኔ-ቢሳው ባሕል በርካታ የሙዚቃ ስልቶች በተለይም ጉምቤ የሚባለው ስልት አሉ። የሀገሩ ባሕላዊ አበሳሰል ሩዝ፣ ጥቁር-ዓይን አተር፣ ኮቴሃሬ፣ ስኳር ድንች፣ ካሳቫ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ሙዝ ጥብስ፣ ኮረሪማ ይመርጣል። እግር ኳስ ከሁሉ የተወደደው እስፖርት ነው።

ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ሸቀጦች በተለይ ዓሣ፣ ኦቾሎኒና ሌላ ለውዝ አይነቶች፣ እንጨት ናቸው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.