መዳብ


መዳብ ወይም ኮፐር (Cu) የንጥረ ነገር ብረታብረት ነው።

ደግሞ ይዩ፦

Cu-Scheibe
Cu-TableImage
መዳብ
1 ነቢሪራው

ሰዋጀንሬ ነቢሪራው በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1635-1614 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ስሙ «ሰዋጀንሬ ነቢሪራው» የሚታወቀው ከአንዳንድ ቅርስ ነው።

በአንድ ጽላት ላይ («የካይሮ ፍትሓዊ ጽላት») ከፈርዖን ነቢሪራው 1ኛ ዓመት (1635 ዓክልበ.) ሲሆን አያመሩ የተባለ መኮንን የኤል-ካብ አገረ ገዥ በመርሆተፕሬ ኢኒ 1ኛ አመት (1661 ዓክልበ.) እንደ ተሾመ ይጠቅሳል።

አንዳንድ ማህተም ወይም ጥንዚዛ ምልክት፣

«ሰዋጀንሬ» በሚል መዳብ ጩቤ።

በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ላይ «ነቢሪ-አውትሬ» ወይም ነቢሪራው ለሃያ-(?) አመት እንደ ገዛ ይላል። በአንዳንድ መምህር ዘንድ 29፣ 27, ወይም 26 አመት ነበር፣ ሁለተኛው ቁጥር በደንብ አይነበብም። ከርሱ ቀጥሎ ሁለተኛው ነቢሪራው ወይም «ነቢታውሬ» ይጠቀሳል።በተጨማሪ ከዚያ 1500 ዓመት በኋላ በ150 ዓክልበ. ያህል የተሠራ አንድ ጣኦት ምስል ይታወቃል፤ በመሠረቱ በየጎኑ «ያለፉት ፈርዖን ሰዋጀንሬ»፣ «ያለፉት ፈርዖን ነፈርካሬ»፣ «አህሞስ»ና «ቢንፑ» ይጠቀሳል። በአንድ መላ ምት፣ ከጥንታዊ ምስል ተቀድቶ ፈርዖን ነቢሪራው ሰዋጀንሬ፣ ልጁም 2 ነቢሪራው ነፈርካሬ፣ እና በዘመኑ የኖሩት ልዑላን መስፍኖች አህሞስና ቢንፑ ይጠቀሳሉ። ሆኖም የ2 ነቢሪራው ስም በቶሪኖ ቀኖና ብቻ ስለሚገኝ ሌላ ስሙ አይታወቅለትም።

ሱቁጥራ

ሱቁጥራ ወይም ሶኮትራ (አረብኛ፦ سُقُطْرَى) በሕንድ ውቅያኖስ የሚገኝ የየመን ደሴት ነው። ባካባቢው ሦስት ሌሎች ትንንሽ ደሴቶችም አሉ።

የሱቁጥራ ስም መነሻ ከሳንስክሪት /ድቪፐ ሱቀደረ/ «ሀሤት ደሴት» እንደ መጣ ይባላል። በ1ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈው ግሪክኛ የቀይ ባሕር ፔሪፕሉስ (ጉዞ መግለጫ)፣ ደሴቱ /ዲዮስኮሪዶ/ ወይም «የዲዮስኮሪ» (መንታ ጣኦታት) ተባለ። ሦስተኛው መነሻ አረብኛው /ሱቅ አል-ቃትራ/፣ «የጠብታ ሱቅ» እንደ ሆነ ይባላል። ጠብታ ማለት በሱቁጥራ ብቻ የሚገኘው የሱቁጥራ ሜርቆ ቀይ ፈሳሽ ሲሆን፣ ይህ ፈሳሽ ስለቀይ ቀለሙ ለማጌጥ ተፈላጊ ነበር።

በጥንት የብዙ አገራት መርከበኞች እንደ ደረሱ ከጽሑፎቻቸው ብዛት ታውቋል። የደሴቱ ኗሪዎች በ44 ዓም በቅዱስ ቶማስ ተጠምቀው ወደ ክርስትና እንደ ገቡ ይነገራል። የኔስቶራዊ ቤተ ክርስቲያን ክፍልፋይ ምዕመናን ሆኑ። ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ፣ በአሁኑ የመን የተገኘው ማህራ ሱልጣናት ሱቁጥራን ይገዙ ነበር። በ1499 ዓም የፖርቱጋል ጦር መርከቦች ሱቁጥራን ያዙት፣ ስላልተስማማቸው ግን በ1503 ዓም እንደገና ተዉት። ጥቂት ኔስቶራዊ ክርስቲያን ሕዝብ በሱቁጥራ እስከ 1792 ዓም ድረስ ቀሩ።

የዛሬው ኗሪዎች አረብኛ እንደ መደበኛ ቋንቋ ከመናገራቸው በላይ፣ ኗሪ ቋንቋቸው ሱቁጥርኛ እንደ ደቡብ አረብኛ አይነት የሆነ ሴማዊ ቋንቋ ነው። ዋና ምርቶቻቸው ተምር፣ ንጥር ቅቤ፣ ትምባሆና አሣ ናቸው። የበሬና የፍየልም እረኞች አሉ።

ደሴቱ ከአሕጉር በመገለሉ፣ በርካታ በሱቁጥራ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ አትክልትና እንስሳት ዝርዮች አሉበት። በተለይም

ከአትክልት፦

የሱቁጥራ ሩማን Punica protopunica

የሱቁጥራ ሜርቆ Dracaena cinnabari

የሱቁጥራ ወርቅ-በሜዳ Dorstenia gigas

የኪያር ዛፍ Dendrosicyos socotranus - በመላው ዱባ አስተኔ ብቸኛው ዛፍ ይሄ ነው።

የሱቁጥራ እጣን ዛፍ Boswellia socotrana

ብዙ የሬት ዝርዮችከእንስሳት፦

የሱቁጥራ ወማይ ወፍ Onychognathus frater

የሱቁጥራ መዳብ-ጥምጣም ማር-መጣጭ ወፍ Chalcomitra balfouri

የሱቁጥራ ድምቢጥ Passer insularis

የሱቁጥራ እስስት Chamaeleo monachus

ሦስት የሠርጣን ዝርዮች

በርካታ የሸረሪት ዝርዮች

ቀንድ አውጣ

ቀንድ አውጣ የዛጎል ለበስ እንስሳ መደብ ነው። የየብስ ቀንድ አውጣ ብቻ ሳይሆኑ ብዙ የባሕር ቀንድ አውጣ ወይም የሐይቅ ቀንድ አውጣ ዝርዮች ደግሞ አሉ። በዚህ መደብ ያሉት አንዳንድ ዛጎልን አይለብሱም፣ ዛጎል-የለሽ ዝርዮችም ስለግ (ከእንግሊዝኛው) ተብለዋል።

የቀንዳውጣ «ቀንድ» በውነት ቀንድ ሳይሆን ዓይኖቹ ያሉበት መዳህሰስ ነው።

ቀንድ አውጣ ሰብልን ስለሚበላ አስቸጋሪ ነው።

ብዙ ቀንድ አውጣ የበሽታ ተሽካሚዎች ሲሆኑ ለጤንነት አስቸጋሪ ነው።

በአንዳንድ አገራት አበሳሰል ውስጥ፣ ቀንድ አውጣ እንደ ምግብ ይበላል።

የቀንድ አውጣ ዛጎል ለጌጣጌጥና እንደ እንቁ ክብርን አገኝቷል።በግብርና ቀንዳውጣ ለመከልከል፣ መዳብ ይሠራል፤ ቀንዳውጣዎች መዳብን አይወዱምና። የመዳብ ቀለበት በዛፍ ግንድ ዙሪያ ቢቀመጥ ቀንዳውጣ እስከ ፍሬው ድረስ አይደርስም። ቡና ለአጸድ ቀንድ አውጣ በጣም መርዛም ሲሆን የተፈጨ ቡና ዱቄት ቢሆንም በማዳበሪያው መጨምሩ ይከለክላቸዋል።

በኢትዮጵያ የተገኙት ተክሎች እንዶድ እና ጓሳ በተለይ በሽታ-አዘልን ቀንዳውጣዎች ለመግደል አገልግለዋል፣ ይህም በምዕራብ ሳይንስ ታውቋል።

ቀንዳውጣ በነዚህ አገራት አበሳሰል ውስጥ እንደ ምግብ ይበላል፦ ፖርቱጋል፣ እስፓንያ፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጅግ፣ ጣልያን፣ ቡልጋሪያ፣ ግሪክ፤ ማልታ፣ ቆጵሮስ፤ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፤ ላዎስ፣ ካምቦዲያ፣ ቬትናም፣ ፊልፒንስ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኔፓል፣ ቻይና።

የአጸድ ቀንድ አውጣ (Cornu aspersum) የሚመንጨው ንፋጭ እዠት ለሰዎች ቆዳ ቁስልን ለማሳደስ እንዳቀለለ ይታወቃል፤ ስለዚህ ይህ እዠት በአንዳንድ የቆዳ ክሬም ውስጥ ተጨምሯል።

በቀንድ አውጣ መደብ፣ አንዳንድ ዝርዮች እንደ ሌሎች እንስሳት ሁሉ በወንድና በሴት ጾታዎች ይከፈላሉ። አብዛኞቹ የቀንድ አውጣ ዝርዮች ግን አንድ ጾታ ብቻ አላቸው እሱም ፍናፍንት ነው። እያንዳንዱ ፍናፍንት ቀንዳውጣ ዘሩንም እንቁላሉንም ይፈጥራል ማለት ነው። በወሲብ ጊዜ ሁለቱ ፍናፍንት ቀንዳውጦች መጀመርያ እርስ በርስ «የፍቅር ጦር» ይጥላሉ፤ ይህ እንደ ስለታም አጥንት የሚጣል ፍላጻ የሌላውን ቀንዳውጣ ይወጋል። ከዚህ በኋላ ዘርን በመለዋወጥ እርስ በርስ እርጉዝ ያደርጋሉ። አንዳንዴም አንድያ ፍናፍንት ቀንዳውጣ ለብቻው እራሱን እርጉዝ ለማድረግ ይቻላል። እርጉዝ ከሆኑ ብዙ መቶ ትንንሽ እንቁላሎች ይጥላሉ።

የቀንዳውጣ እግር በንፋጭ ምንጨት ስለሚሸፈን ቀስ ብሎ ሲሄድ ሲሄድ የንፋጭ ጎዳና ይተዋል። ከትንሽ በኋላም ሲደርቅ ይጠፋል። ይህ በመዝሙረ ዳዊት 58:8 (በእብራይስጥ) ይጠቀሳል፤ «(ኀጥኣን) እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ያልቃሉ»፣ በዘመናዊው አማርኛ ትርጉም ግን «ቀንድ አውጣ» ሳይጠቅስ «እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ» አለ።

ቆጵሮስ

ቆጵሮስ (ግሪክኛ፦ Κύπρος /ኪፕሮስ/) በሜድትራኒያን ባሕር የምትገኝ ደሴት አገር ናት። ዋና ከተማው ሌፍኮዚያ ነው።

ቆጵሮስ የተባባሪ መንግሥታት አባል ቢሆንም፣ ከአንዱ ሌላ አባል እርሱም ቱርክ (ስለ ስሜን ቆጵሮስ ጉዳይ) ዲፕሎማቲክ ተቀባይነት የለውም።

ከ1966 ዓም የቱርክ ሥራዊት ወረራ ጀምሮ የስሜኑ ክፍሎች በቱርኮች አስተዳደር ሆነዋል። ከክፍሎቹ መካከል ቀጭን የተባባሪ መንግሥታት መሃልገብ ዞን ይገኛል።

በእጅ ያለ መዳብ እንደወርቅ ይቆጠራል

በእጅ ያለ መዳብ እንደወርቅ ይቆጠራል የአማርኛ ምሳሌ ነው።

በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነው

በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነው የአማርኛ ምሳሌ ነው።

ታኅሣሥ ፳፫

ታኅሣሥ ፳፫ ቀን

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፲፫ተኛው እና የመፀው ወቅት ፹፰ተኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፶፫ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፶፪ ቀናት ይቀራሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየወሩ ፳፫ኛ ቀን የሰማዕታትን ዓለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስንን ታስታውሳለች።

ነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ

ንፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የንፋስን አቅም ወደ ኤሌክትሪክ አቅም የሚቀይር መሳሪያ ነው። ኤሌክትሪክ ማመንጫው አብዛኛውን ጊዜ ከ4 አበይት ክፍሎች ይዋቀራል። እኒህም #ዘዋሪ ላባ፣ #ጄኔሬተር ቆጥ፣ #መቆጣጠሪያ ስርዓት እና #የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት ናቸው ።

ዘዋሪው ላባ በንፋስ ጉልበት ሲሽከረክረ፣ እርሱ በተራው ዳይናሞውን (የመግነጢስ እና ጥቅልል መዳብ ሽቦ ስርዓት) በመዘወር ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የመቆጣጠሪያ ስርዓቱ፣ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ እንዳፈለገ እንዳይለዋወጥ፣ በተወሰነ መጠን እንዲረጋ የሚያደርግ የኮምፒዩተር ስርዓት ነው።

ንግድ

ንግድ በመሰረቱ እጅግ በጣም ጥንታዊ የሰው ልጆች እንቅስቃሴ ነው። ሰው ማንኛውንም የፈለገውን ቁሳቁስ ማሙዋላት የማይችል ስለሆነ የግድ በተሰማራበት ሙያ የሚያገኘውን የስራ ውጤት ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን እሱ ራሱ ማምረት የማይችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ሲል የሚያካሄደው የምርቶች ልውውጥ ሂደት ነው።

ደግሞ ይዩ፦ ምጣኔ ሀብት

ኢድሪሚ

ኢድሪሚ ከ1473 እስከ 1443 ዓም ያህል ድረስ የሙኪሽ አገር (አላላኽ ከተማ) ንጉሥ ነበረ።

የኢድሪሚ ታሪክ በተለይ ከሐውልቱ አካድኛ ጽሑፍ የሚታወቀው ነው። የሐለብ መጨረሻ ንጉሥ የ1 ኢሊም-ኢሊማ ልጅ ነበር፣ ይህም ሥርወ መንግሥት ቀድሞ የያምኻድ መንግሥት ተብሎ ነበር። በ1480 ዓክልበ. ገደማ የሑራውያን ንጉሥ ባራታርና ሐለብን ወደ ሚታኒ መንግሥት እንደ ጨመረው ይታመናል። ኢድሪሚና ቤትሠቡ ከሐለብ ወደ ኤማር ሸሹ። ኢድሪሚ ከዚያ ወደ ከነዓን ምድር አሚያ ከተማ ሂዶ ከሐቢሩ ወገን ጋር ለሰባት ዓመት ቆየ ይላል። በዚያ በስደት ሆኖ ከሐቢሩና ሐገሩ ስደተኞች መካከል ሥራዊት ያሕል ሰበሰበ። በ1473 ዓክልበ እነርሱ በመርከብ በሶርያ ተመልሰው ደረሱ፣ አላላኽን ለመያዝ ቻሉና የአላላኽ፣ የኑሓሼና የኒያ ኗሪዎች ተደሰቱ፤ ሙኪሽ ከተባለው አገር ጋር ተባበሩ ይላል። ባራታርና ግን ለሰባት ዓመት ጠላቱ ሆነ። በመጨረሻ በ1465 ዓም አካባቢ ኢድሪሚ መልክተኛውን ወደ ባራታርና ልኮ «እኛ ዱሮ የሑራውያን ጓደኞች ነበርን» በሚል መልዕክት አሳሰበው። ባራታርና ይህን ተቀበለና ኢድሪሚ ለሚታኒ ጥገኛ ንጉሥ ሆኖ በሙኪሽ እንዲቆይ ፈቀደ። ኪዙዋትና የተባለው አገር ደግሞ የሚታኒ ጥገኛ እንደ ተደረገ ይመስላል። በኢድሪሚም ሆነ በባራታርና ቅርሶች እስካሁን በተገኙት መረጃዎች ምንም ስለ ግብጽ ባይጠቀስም፣ ፈርዖን 3 ቱትሞስ ደግሞ በዚህ ዘመን በሙኪሽና በሚታኒ ላይ ይዘምት ነበር።

ከዚህ በኋላ ኢድሪሚ በሐቲ (የኬጥያውያን መንግሥት) ላይ ዘምቶ ሰባት አምባዎች እንደያዘባቸው ይላል። ከዚያ ሕዝቡን በጸጥታ አስተዳደረው ይላል። ጸሓፊውም ሻሩዋ ኢድሪሚ ለ30 አመት እንደ ገዛ በማለት ጨመረ።

ለኢድሪሚ ሁለት ሌሎች ጽላቶች ይታወቃሉ። ከነዚህ አንዱ ከኢድሪሚና ከኪዙዋትና ንጉሥ ፒሊያ መካከል የተደረገው ውል ነው። በዚህ ውል መሠረት ከአንዱ አገር ወደ ሌላው የሸሹት ባርዮች እንዲመለሱ አስቻለ። ባርያውን የያዘው ሰው 500 ሰቀል መዳብ ለወንድ፣ 1000 ለሴት ባርያ እንዲከፈል አዘዘ። ወይም የባርያው ጌታ እራሱ ባርያውን ለመያዝ እርስ በርስ ወደ ኪዙዋትናም ሆነ ሙኪሽ መግባቱን በነጻ ፈቀደው።

ኢድሪሚ ብዙ ጣኦታት እንዳገለገለ ስለ ጻፈ በእርግጥ አረመኔ ንጉሥ ነበር። በከነዓን ውስጥ ቢቆይ ብሉይ ኪዳን ከእስራኤል ውጭ በዚህ ዘመን ለነገሡት አረመኔ ነገሥታት ብዙ ትኩረት አይሰጥም፤ ግን ጎቶንያል ፈራጃቸው የሆነበት ወቅት ያሕል ይመስላል።

የኢድሪሚ ልጅ ኒፕመቃ በሙኪሽ ዙፋን ላይ ተከተለው።

ካሩም

ካሩም በጥንት (2150-1628 ዓክልበ. ያሕል) የአሦር ሰዎች በውጭ አገራት በተለይ በሐቲ (አናቶሊያ) ያቋቋሙት የንግድ ሠፈሮች ነበሩ።

በኤብላ ጽላቶች መካከል አንዱ ሰነድ ከኤብላ (በሶርያ) እና ከአሹር (ወይም ከአባርሳል?) መካከል የተዋወለ ውል ሲሆን በዚህ ውል አሹር በኤብላ ግዛት ውስጥ ካሩም ለማስተዳደር ፈቃድ አገኘ።

ከዚህ ጥቂት ዓመታት በኋላ የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ኤብላን አጠፋ። ከኋለኛ ዘመን በኬጥኛ በተጻፈ ታሪክ ዘንድ፣ የቡሩሻንዳ ንጉሥ ኑርዳጋል በካሩሞች የነበሩትን አካዳዊና አሦራዊ ነጋዴዎች መደብ ስለ በደለ፣ ሳርጎን ደግሞ አናቶሊያን ወረረ። ይህም ድርሰት በአማርና ደብዳቤዎች መካከል በአካድኛ ተገኘ፤ ቅጂዎቹ ግን በሳርጎን ዘመን ስላልተጻፉ እንደ ታማኝ ታሪክ አይቆጠሩም።

በሐቲ እነዚህ የአሦራውያን ነጋዴ ሠፈሮች ከሐቲ ከተሞች አጠገብ ይመሠረቱ ነበር፤ ቀረጥም ለከተማው ገዢ ያስረክቡ ነበር። አነስተኛ «መባርቱም» የተባሉት ጣቢያዎች ደግሞ ነበሯቸው። በተለይ 1880-1745 እና 1662-1628 ዓክልበ. በጠቅላላ የካሩምና የመባርቱም ቁጥር ምናልባት ፳ ያሕል ነበር። ከነዚህም ውስጥ ካነሽ፣ አንኩቫ፣ ሐቱሳሽ በዋናነት ይጠቀሳሉ።

በዚሁ ዘመን መደበኛ ገንዘብ (መሀልቅ) ገና አልተፈጠረም ነበር። የአሦር ነጋዴዎች ወርቅ በጅምላ፣ ብር ለችርቻሮ ይጠቅማቸው ነበር። የወርቅ ዋጋ ከብር ፰ እጥፍ መሆኑ ተወሰነ። ሆኖም ሌላ የብረታብረት አይነት በአሦርኛ «አሙቱም» ሲባል ይህ ከወርቅም በላይ ውድ ነበር፤ ከብር ፵ ጊዜ ተላቀ። «አሙቱም» ምናልባት ያንጊዜ ትኩስ ግኝት የነበረ ብረት ሊሆን ይቻላል። እነዚህ የአሦር ነጋዴዎች በተለይም ቆርቆሮና ልብስ ለሐቲ ሰዎች ይሸጡ ነበር። ከሐቲ አገር ካስወጡአቸው ውጤቶች መካከል ከሁሉ አይነተኛ የሆነው መዳብ ነበረ።በሐቲ ዙሪያ ያሉት ከተማ-አገራት ሲወዳደሩ ሲታገሉ አንዳንዴ ለንግድ አስጊ ሁኔታ ይፈጥር ነበር። በ1745 ዓክልበ. ግድም ዋናው የካነሽ ካሩም ተቃጠለ፤ ይህን ያደረገው የዛልፓ (በጥቁር ባሕር ዳር) ንጉሥ ኡሕና ይታስባል። የኩሻራ ንጉሥ ፒጣና በ1662 ዓክልበ. አካባቢ ካነሽን ይዞ በልጁ አኒታ መንግሥት የአሦራውያን ነጋዴዎች ሊመለሱ ቻሉ። የአኒታም መንግሥት የኬጥያውያን መንግሥት መንስኤ ሆነ። በኋላ «የአላሕዚና ሰው ዙዙ» ተከተለው። ከዙዙ በኋላ በአሦርም ብሔራዊ ጦርነት በደረሰው ወቅት ካሩሞቹ ከአናቶሊያ ጠፉ። ትልቁም ካሩም ካነሽ በ1628 ዓክልበ. ግብድ. በሻላቲዋራ ከተማ ንጉሥ እጅ ጠፋ።

ክሪስታል ራዲዮ

የክሪስታል ራዲዮ የሚሰኘው ከሁሉ በላይ በጣም ቀላል ራዲዮ ተቀባይ ሲሆን፣ በድሮው የራድዮ ዘመን ታዋቂነት ያገኘ ነበር። ክሪስታል ራዲዮ ባትሪም ሆነ ሌላ የኤሌክትሪክ ኃይል አይፈልግም። ይልቁኑ ከሚተላለፍ የራዲዮ ሞገድ አቅም በመውሰድ በራሱ ይሰራል። ለዚህ ተግባር ሲባል ክሪስታል ራዲዮ ረጅም የሽቦ አንቴና ይፈልጋል። ክሪስታል መባሉ ድሮ ይሰራበት ከነበርው ወሳኝ ክሪስታል ጋሌና የተባለ ክፍል የመጣ ስም ነው። በአሁኑ ዘመን ይህ ክፍል በዳዮድ ተተክቷል። ክሪስታል ራዲዮ በጣም ቀላል ከመሆኑ የተነሳ ማንም ሰው ሊሰራው ይችላል። የሚያስፈልጉትም እቃወች አንቴና ሽቦ (ረጅም መሆነ አለበት)፣ ጣቢያ መቀየሪያ ጥቅል ሽቦ (መዳብ) ፣ ክሪስታል ጠቋሚ ወይንም ዳዮድ እና የጆሮ ስልክ (ማለቱ ማናቸውም በጆሮ ላይ ተደርጎ ሙዚቃ ለመስማት የሚያገለግል ኢር ፎን) ናቸው። በርግጥ የክሪስታል ራዲዮ የተወሰነ ጣቢያወችና በዚያው ልክ ድምፁም ከፍተኛ ስላልሆነ ኢር ፎን መጠቀም ግድ ይላል።

ዚምባብዌ

የዚምባብዌ ሪፐብሊክ ከዚህ በፊት የሮዴዢያ ሪፐብሊክ በመባል የምትታወቅ ስትሆን፣ በደቡብ አፍሪካ የምትገኝ ወደብ-የለሽ ሀገር ናት።

ዚምባብዌ ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦትስዋና ፣ ዛምቢያ እና ሞዛምቢክን ትዋሰናለች። የዚምባብዌ ስም የመጣው ከ«ድዚምባ ድዜማብዌ» ሲሆን በሾና ቋንቋ «የድንጋይ ቤቶች» ማለት ነው።

የንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ

የንጥረ ነገሮች ሠንጠረዥ ወይም የሜንደሊቭ ሠንጠረዥ (periodic table of the chemical elements) የሚባለው ሠንጠረዥ ሲሆን ንጥረ ነገሮችን በሙሉ ከተለያዩ መረጃዎች ጋር ጠቅልሎ የያዘ ዘመናዊ ሠንጠረዥ ነው። የተለያዩ ማሻሻያዎች ቢደረጉበትም በዋናነት የሩሲያዊው ሳይንቲስት ዲሜትሪ ሜንደሊቭ (1869) ግኝት ነው። የሠንጠረዡ ይዘት እና ቅርፅ በየጊዜው ሲቀያየር ኑሯል። ለዚህም ምክንያቱ አዳዲስ ንጥረ ነገሮች እና የኬሚስትሪ ሀሳቦች መፍለቃቸው ነው።

የኤሽኑና ሕግጋት

የኤሽኑና ሕግጋት በሁለት ጽላቶች በ1937 እና 1939 ዓ.ም. በኢራቅ ተገኙ። ምናልባት 1775 ዓክልበ. አካባቢ እንደ ኤሽኑና ሕግ ፍትሕ ሆነው ወጡ፤ የትኛው ንጉሥ እንዳወጣቸው ግን እርግጥኛ አይደለም።

ከነዚህ ሕገጋት ብዙዎቹ የሐሙራቢ ሕግጋት (1704 ዓክልበ. ግድም) ይመስላሉ፤ እንዲሁም ብዙዎቹ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 በሕገ ሙሴ (1661 ዓክልበ. ግድም) መልስ አገኙ። ሆኖም ከነዚህ ሕጎች መካከል ያላቸው ልዩነቶች ደግሞ ጥቂት አይደሉም።

ሌሎችም ሕግጋት ነበሩ፤ ነገር ግን ጽሑፊ በፍርስራሽ ሆኖ በሙሉ ሊነበብ አይቻልም። ከተረፉት ሕግጋት መሃል፦

§1) ለአንድ ሰቀል (፱ ግራም ያህል) ብር መግዣው፦

1 ጉር (300 ሊተር ያህል) ገብስ

3 ሊተር የሩስቱም (?) ዘይት

12 ሊተር የሰሊጥ ዘይት

15 ሊተር ጮማ

40 ሊተር «የወንዝ ዘይት» (?)

6 ምና (=3.24 ኪሎግራም) ሱፍ

2 ጉር ጨው

1 ጉር የድስት አመድ

3 ምና (1.62 ኪሎግራም) መዳብ

2 ምና (1.08 ኪሎግራም) የተሠራ መዳብ

§2) 1 ሊተር የሰሊጥ ዘይት ለ30 ሊተር ገብስ መደበኛ ነው፤ 1 ሊተር ጮማ ለ25 ሊተር ገብስ፤ 1 ሊተር «የወንዝ ዘይት» ለ8 ሊተር ገብስ

§3) የጋሪ ኪራይ ከነነጂው፣ ከነበሬው፦ 100 ሊተር ገብስ፣ ወይም 1/3 ሰቀል ብር፣ ለአንድ ቀን ይሆናል።

§4) የመርከብ መጓጓዣ ኪራይ ለ1 ጉር ይዘት 2 ሊተር ገብስ ነው፤ <...> ሊተር የመርከበኛው ኪራይ ለአንድ ቀን ነው።

§5) መርከበኛ ቸልተኛ ሆኖ መርከቡ ከሰመጠበት፣ የይዘቱን ዋጋ በሙሉ ይከፍላል።

§6) ሰው አለግባብ የሌላውን ሰው መርከብ ከወሰደ፣ 10 ሰቀል ብር ይክፈል።

§7) ምርቱን ያመረተው ዋጋ 20 ሊተር ገብስ፣ ወይም 12 ቅንጣት ብር (0.6 ግራም) ይሆናል።

§8) ያመነሸው ዋጋ 10 ሊተር ገብስ ነው።

§9) ሰው ለሠራተኛ ምርቱን ለማምረት ፩ ሰቀል ብር ከሰጠው፣ ሠራተኛው ግን ሥራውን ካልጨረሰው፣ በሠራተኛው ላይ የ10 ሰቀል ብር ቅጣት አለ።

§9 ሀ) የማጭድ ኪራይ 15 ሊተር ገብስ ነው፣ ለባለቤቱም ይመልስ።

§10) የአህያ ኪራይ 10 ሊተር ገብስ፣ የነጂውም ኪራይ 10 ሊተር ገብስ፣ ለአንድ ቀን ይሆናል።

§11) የሠራተኛው ኪራይ (ደሞዝ) 1 ሰቀል ብር እና ለሥንቁ 60 ሊተር ገብስ ለአንድ ወር ይሆናል።

§12) ማንኛውም ሰው በዜጋ እርሻ፣ በሰብሉ ከተያዘ፦ በመዓልት ከሆነ 10 ሰቀል ብር ይክፈል። በሌሊት በሰብሉ የተያዘው፣ ይሙት በቃ።

§13) ማንኛውም ሰው በዜጋ ቤት ውስጥ ከተያዝ፦ በመዓልት ከሆነ 10 ሰቀል ብር ይክፈል። በሌሊት በቤቱ የተያዘው፣ ይሙት በቃ።

§15) ነጋዴው ብር፣ ገብስ፣ ሱፍ ወይም የሰሊጥ ዘይት ከባርያ እጅ አይቀበለም።

§17/18) የሰው ልጅ የሙሽሪት ማጫ ብር ለአማቱ ካመጣ፦

(ሀ) ከዚያ ከሁለቱ አንዱ ካረፈ፣ አማቱ ማጫዋን ይመልስ፤

(ለ) ሙሽሪት ወደ ቤተሠቡ ከገባች፣ ከዚያም (ልጅ ሳይወለድ) ከሁለቱ አንዱ ካረፈ፣ ያመጣው ጥሎሽ አይወጣም፤ ትርፉን ብቻ ይወስዳል።

§18 ሀ) ጥሎሹም ለ፩ ሰቀል ብር የ36 ቅንጣት (1.8 ግራም) ወለድ አገድ አለው፤ ለ፩ ጉር ገብስ የ40 ሊተር ወለድ አገድ አለ።.

§19) የሚከፍለው ሰው በአውድማ ይቀበል።

§22) ሰው በሌላ ሰው ላይ ምንም የእዳ ነገር ሳይኖረው፣ ሆኖም የሌላውን ገረድ ከያዘ፣ የገረድ ጌታ በአምላክ ይማል፣ «አንተ በኔ ላይ ምንም ነገር የለህም»፤ ገረዱን የያዘው ሰው እንደ ገረዲቱ ዋጋ ይክፈል።

§23/24) ሰው በሌላ ሰው ላይ ምንም የእዳ ነገር ሳይኖረው፣ ሆኖም የሌላውን ገረድ ከያዘ፣ በቤቱም እንድትሞት ካደረገ፣ እርሱ ለገረዲቱ ጌታ ፪ ገረዶች ይተካ።

§25) ሰው በአማቱ ቤት ከታጨ፣ አማቱ ግን በድሎት ልጂቱን ለሌላ ከሰጠ፣ የልጅቱ አባት ፪ እጥፍ የማጫዋን ብር ይመልሳል።

§26) ሰው ለሴት ልጅ የማጫዋን ብር ካመጣ፣ ሌላ ግን ያለ ወላጆች ፈቃድ በግድ ከያዛት፣ የሕይወት ጉዳይ ነው፤ ይሙት በቃ።

§27) ሰው ወላጆቿን ሳይጠይቅ ሴት ልጃቸውን ከያዘ፦

(ሀ) ከዚያም የሠርግ ሥነ ሥርዓትና ውል ካልፈጸመ፣ ለአንድ አመት ሙሉ እቤቱ ውስጥ ብትኖርም፣ «ሚስት» አትሆንም።

(ለ) ከዚያም የሠርግ ሥነ ሥርዓትና ውል ከፈጸመ፣ «ሚስት» ነች። በሌላ ሰው ጭን ከተያዘች፣ ይሙት በቃ ጉዳይ ነው።

§29) ሰው በጦርነት ጊዜ ከተማረከ፣ በሌላ አገር ለረጅም ጊዜ ከኖረ፣ ሌላ ሰው ደግሞ ሚስቱን አግብቶ ልጅ ከወለደችለት፣ ቢሆንም ሰውዬው በተመለሰበት ጊዜ ወደ ሚስቱ ሊመለስ ይችላል።

§30) ሰው ከተማውን ከጠላ፣ ከሸሸ፣ ሌላ ሰው ደግሞ ሚስቱን ከወሰደ፣ ሰውዬው በተመለሰበት ጊዜ ምንም ይግባኝ ማለት የለውም።

§31) ሰው የሌላውን ሰው ገረድ በወሲብ ከያዘ፣ 1/3 ምና (20 ሰቀል ወይም 180 ግራም) ብር ይክፈል፤ ገረዲቱም የጌታዋ ሆና ትቅር።

§32) ሰው ልጁን ለአሳዳጊነት ከሰጠ፣ ለሦስት ዓመት ስንቅ በቂ ምግብ፣ ዘይትና ልብስ ካላቀረበለት፣ 10 ምና ለልጁ አሳዳጊነት ይክፈል፣ ልጁም ለርሱ ይመልሳል።

§33) ገረድ ያለ ሕግ ልጇን ለሌላ ሴት ልጅ አሳዳጊነት ከሰጠችው፣ እሱም አድጎ ጌታው ካወቀው፣ ጌታው ይዞት ሊውሰደው ይችላል።

§36/37) ሰው ንብረቱ እንዲጠበቅ አደራ ቢያኖር፣ አደራ ያለው ባልንጀራ ማንም ሌባ እቤቱ ሳይገባ ንብረቱ እንዲጠፋ ካደረገ፣ ባልንጀራው ንብረቱን ለሰውዬው ይተካል። ከቤቱም ቢሰረቅ፣ የባለቤት ማጣት ነው፣ ባለቤቱ በቤተ መቅደስ ለሰውዬው በአምላክ ይማል፦ «የኔና ያንተ ንብረት አንድላይ ጠፍተዋል፣ እኔ አልከፋሁም አልበደልኩም።» ይማልና ምንም ዕዳ አይሆንበትም።

§39) ሰው ድሃ ሆኖ ቤቱን ከሸጠ፤ ገዢው በፈቃዱ በሚሸጥበት ቀን ባለቤቱ ሊገዛው ይችላል።

§40) ማንም ሰው ባርያ፣ ገረድ፣ በሬ፣ ወይም ሸቀጥ ከገዛ፣ ለማናቸውም ዋጋ፣ ማን እንደ ሸጠው ሊያስረዳ ካልቻለ እርሱ እራሱ ሌባው ነው።

§42) ሰው የሌላውን አፍንጫ ከቈረጠ፣ ፩ ምናን ይክፈል፤ ለዓይን፦ ፩ ምና፤ ለጥርስ፦ 1/2 ምና (፴ ሰቀል)፤ ለዦሮ - 1/2 ምና። ለጥፊ፦ 10 ሰቀል ብር ይክፈል።

§43) ሰው የሌላውን ጣት ከቈረጠ፣ 2/3 ምና ይክፈል።

§44/45) ሰው ሌላውን በጠብ ወደ ምድር ጥሎት እጁን ከሰበረ፣ 1/2 ምና ብር ይክፈል። እግሩን ከሰበረ፣ 1/2 ምና ይክፈል።

§46) ሰው ሌላውን ከመታ ክሳዱን አጥንት ከሰበረ፣ 2/3 ምና ብር ይክፈል።

§47) ሰው ሌላውን በጠብ ከጎዳው፣ 10 ሰቀል ብር ይክፈል።

§47A) ሰው በጠብ የሌላ ሰው ልጅ መሞት ካደረገበት፣ 2/3 ምና ብር ይክፈል።

§49) ሰው ከተሰረቀ ባርያ ጋር፣ ከተሰረቀች ገረድ ጋር ከተገኘ፣ ባርያ ለባርያ፣ ገረድ ለገረድ መተካት አለበት።:

§50) ማንም ሹም ከዜጋ የሸሸውን ባርያ፣ የሸሸችውን ገረድ፣ የባዘነውን በሬ ወይም አህያ ወደ ኤሽኑና ካላመጣው ወይም ካላመጣት፣ በቤቱም ውስጥ ከጠበቀው፣ ከአንድ ወር በላይ ካለፈ፣ ቤተ መንግሥት በስርቆት ይከሰዋል።

§51) የባርነት ምልክት ያለበት የኤሽኑና ባርያ ወይም ገረድ ከኤሽኑና በር ያለ ጌታቸው አይወጡም።

§52) የመንገደኛ ባርያ ወይም ገረድ ወደ ኤሽኑና በር ገብቶ የባርነት ምልክት ይቀበላል፣ በጌታውም አደራ ይቆያል።

§53) በሬ ወግቶ በሬን ከገደለ፣ ሁለቱ ባለቤቶች የደኅናውን በሬ ዋጋና የሞተውን በሬ ሬሳ በትክክል ይካፈሉ።

§54/55) በሬ ተዋጊ ከሆነ፣ ኃላፊውም ለባለቤቱ ቢመሰክርለት፣ እሱ ግን በሬውን ባይጠብቀው፣ ሰውንም ቢገድል፣ የበሬው ባለቤት 2/3 ምና ብር ይክፈል። ባርያን ወግቶ ቢገድል፦ 15 ሰቀል ብር ይክፈል።

§56/57) ውሻ ተዋጊ ከሆነ፣ ኃላፊውም ለባለቤቱ ቢመሰክርለት፣ እሱ ግን ውሻውን ባይጠብቀው፣ ሰውንም ቢገድል፣ የውሻው ባለቤት 2/3 ምና ብር ይክፈል። ባርያን ወግቶ ቢገድል፦ 15 ሰቀል ብር ይክፈል።

§58) ግድግዳ ሊወድቅ ቢል፣ ኃላፊው ለባለቤቱ ቢመሰክለት፣ እሱ ግን ግድግዳውን ካልጠነከረ፣ ግድግዳውም ወድቆ የሰውን ልጅ ከገደለ፦ የሕይወት ጉዳይ ነው፤ በንጉሥ ድንጋጌ ነው።

የጥንተ ንጥር ጥናት

ኬሚስትሪ ወይም የጥንተ-ንጥር ጥናት የቁሶችን አሰራር እና ጸባይ ያጠናል።

የ«ኬሚስትሪ» ስም የሚመጣ ከእንግሊዝኛ ሲሆን እሱ የተወለደ ከ1700 ዓ.ም. አካባቢ በፊት «አልኬሚ» ከተባለ ሌላ ጥናት ነበር። ይህም አልኬሚ ዋና ዒላማ ብረት ወደ ወርቅ ለመቀየር ነበር። የማይቻል ምኞት እንደ ነበር የዛኔ ተገነዘበ። አልኬሚ የሠራ ሰው 'አልኬሚስት' ተባለ ወይም በአጭሩ 'ኬሚስት'። በኋላ ትውልድ የኬሚስት ሥራ 'ኬሚስትሪ' ተባለ።

የ«አልኬሚ» ስም ደግሞ የወጣ ከዓረብኛ «አል-ኪሚያ» (الكيمياء ወይም الخيمياء) ማለት «የመቀየር ጥበብ» ሲሆን የዚህ ቃል መነሻ በእርግጠኝነት አይታወቅም። ወይም ከግሪክ «ቄሜያ» (χημεία, ቀላጭ ብረታብረት) ወይም ከግብጽ ዱሮ ስም «ከመት» («የከመት ጥበብ» ለማለት) ሊሆን ይችላል።

እንዲሁም በእንግሊዝኛ chemical ኬሚካል የሚለው ቃል ድምጽ ኃይል ከ«ኬሚስትሪ» ሲሆን፣ በዐማርኛ «ጥንተ ንጥር» መባሉ ከግዕዝ ነው። «ንጥር» ማለት የተነጠረ ወይም የተጠራ እንደ ንጥር ቅቤ ቢሆን ፅንሰ ሀሣቡ ከነጥሮን (ሶዲየም ከሰላ ወይም አምቦ አመድ) ጋር፣ በግሪክም /ኒትሮን/፣ ዓረብኛ /ናጥሩን/፣ ዕብራይስጥ /ኔቴር/፣ ግብጽኛ /ነቸሪት/ («የአምላክ») እንደ ተዛመደ ይታሥባል።

ድንጋይ ዘመን

ድንጋይ ዘመን በ«ሦስቱ ዘመናት» አስተሳሰብ ከናስ ዘመን አስቀድሞ የነበረው ዘመን ነው። በአጠቃላይ እንደ ተለመደ ከ3125 ዓክልበ. ያህል በፊት ያመልክታል። በዚህ ዘመን አብዛኞቹ መሣርያዎችና እቃዎች የተሠሩ ከድንጋይ ነበር።

የናስ ጥቅም በጥንታዊ ግብጽ ከ3125 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ይታወቅ ነበር። ይህም ደግሞ በአለም ላይ የጽሑፍ መጀመርያ ወቅት ስለነበር፣ የታሪክ መጀመርያ ደግሞ ይባላል። እንግዲህ የ«ድንጋይ ዘመን» እና የ«ቅድመ-ታሪክ» ትርጉም አንድላይ ሊሆን ይችላል።

የዚህ አከፋፈል ዋጋ አጠያያቂ ነው። በብዙ ቦታዎች የናስና የብረት ዕውቀት የገቡት በአንድ ጊዜ ነበረ። ለምሳሌ በስሜን አሜሪካ በኩል፣ አውሮፓውያን 1500 ዓም ያህል ሳይገቡ ኗሪዎቹ የብረታብረት ቀለጣ እንደነበራቸው አይታስብም፤ ከተደቀደቀ መዳብ፣ ወርቅና ብር በቀር ብዙ የብረታብረት እቃዎች አላወቁም ነበር። የመዳብና የነሐስ ቀለጣ ግን በደቡብ አሜሪካ ይታወቅ ነበር፣ ከ800 ዓም ግድም ጀምሮ በመካከለኛ አሜሪካ ደግሞ ይታወቅ ነበር።

ገንዘብ

በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።

የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።

ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.