መዝገበ ዕውቀት

መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ማለት ወይም የዕውቀት ዘርፎች ሁሉ ወይም የአንድ ዕውቀት ዘርፍ የመረጃ ክምችት ነው። ከመዝገበ ቃላት የሚለይበት ጥቅሙ እያንዳንዱ መጣጥፍ ስለ አንድ ቃል ወይም ዘይቤ ብቻ ሳይሆን ጥልቀት ያለው መረጃ እሚሰጥ መሆኑ ነው። ስለዚህ የመዝገበ ዕውቀት መጣጥፍ ከመዝገበ ቃላት መጣጥፍ ይልቅ ረጅምና ዝርዝሩን የሚገልጽ ነው። ከሁሉ ጥንታዊው እስካሁንም የሚገኘው መዝገበ ዕውቀት የፕሊኒ መጽሐፍ ናቱራሊስ ሂስቶሪያ ወይም «የተፈጥሮ ታሪክ» (69 ዓ.ም. በሮማይስጥ ተጽፎ) ይባላል። በአሁኑ ዘመን በኢንተርኔት የሚነቡ ብዙ መዛግብተ ዕውቀት (ለምሳሌ ውክፔዲያ) ሊገኙ ይቻላል።

ዕውቀት የተሳተ መረጃ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ መዝገበ ዕውቀት «መዝገበ ዕውነት» ከቶ አይሆንም። ለመሆኑ ግን በዞራስተር ጽሑፍ መሠረት «መዝገበ ዕውነት» (ሃታ-ማራኒሽ) የእግዚአብሔር 16ኛው ስያሜ ነው።

ማይክሮሶፍት

ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን ዓለም-አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። እንደ ጁላይ 2006 እ.ኤ.አ. ማይክሮሶፍት 71,553 ሠራተኞች በ102 ሀገሮች ሲኖረው፣ ዓመታዊ ገቢው 44.28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነው። እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማምረትና ማዳበር ዋና ዓላማው ነው። ዋና መስሪያቤቱ በሬድመንድ፣ ዋሽንግተን፣ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ታዋቂ ምርቶቹ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ስርአተ ክወና እና ማይክርሶፍት ኦፊስ ግሴት ሶፍትዌር ያጠቃልላሉ። ከሶፍትዌሮች ሌላ፥ ኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ የኬብል ቴሌቪዥን፥ ኤም.ኤስ.ኤን. ዌብሳይት፥ ማይክሮሶፍት ኢንካርታ የኢንተርኔት መዝገበ ዕውቀት፥ የቤት መዝናኛ እና ሌሎችም ምርቶችና አገልግሎቶችን ያቀርባል።

ረኔ ዴካርት

ሬኔ ደካርት (René Descartes) (መጋቢት 31፣ 1596 – ሐምሌ 1650;) ፈረንሳዊ ሳይንቲስት፣ ሂሳብ ተመራማሪ እና ፈላስፋ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የዘመናዊ ፍልስፍና አባት በመባል ይታወቃል። ሶስት ምክንያቶች ይጠቀሳሉ። የመጀመሪያዊ፣ ከጥንት ዘመን ጀምሮ ይሰራበት የነበረውን ምሁራዊ አሪስጣጣሊያውነትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከአስተሳሰብ ዘዴው ያሰዎገደ ፈላስፋ በመሆኑ። ሁለተኛው ምክንያት የአዕምሮ እና አካል ሁለት እና እማይቀላቀሉ ነገሮች መሆን አስተሳሰብን ለመጀመሪያ ጊዜ ስላስተዋወቀ። ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ፣ በአስተዎሎት እና ሙከራ ላይ የተመሰረተ አዲስ ዓይነት ሳይንስ ስላስተዋወቀ ነበር።

የካርቴዢያን ሰንጠረዥ ተብሎ በሚታወቀው አዲስ የጂዎሜትሪ እና አልጀብራ መቀየጫ ዘዴ በዚህ ሰው የተፈጠረ ሲሆን፣ በሂሳብ ጥናት ላይ ስር ነቀል ለውጥ አምጥቷል። ስለሆነም የትንተና ጂዎሜትሪ አባት በመባል ይታወቃል። ዴካርት፣ ከሒሳብ በተረፈ በሳይንስ ጥናቶች ላይ በመሳተፍ በዘመኑ የሳይንስ አብዮት በአውሮጳ እንዲፈነዳ ጉልህ አስተዋጾ አድርጓል።

ዴካርት በ17ኛው ክፍለ ዘመን ግዙፍ ስም ያገኘ ፈላስፋ ሲሆን በተለይ በአውሮጳ አህጉር በምክኑያዊነት (rationalism) ፍልስፍና ታዋቂነትን ያተረፈና ከሱ ፍልስፍና ተነሰተው በማስፋፋት እነ ባሩክ ስፒኖዛ እና ሌብኒትዝ ለምክኑያዊ ፍልስፍና ጥበብ ታላላቅ ድርሻ ሊያበረክቱ ችለዋል። በዚህ ተቃራኒ ግን ዳሳሻዊነት (empiricism) ፍልስፍናን ያራመዱ ፈላስፎች፣ ለምሳሌ ሎክ፣ ሆብስ፣ በርክሊ፣ ሩሶና ሁም የምክኑያዊነት ፍልስፍናውን አጥብቀው ተቃውመዋል። ከፍልስፍና ጽሁፎቹ ውስጥ አትኩረተ ህሊና በፍልስፍና መሰረት ላይ (Meditations on First Philosophy) የተባለው ጽሁፉ እስካሁን ዘመን ድረስ በዩንቨርስቲወች ውስጥ እንደ ዋና የትህርት ክፍል ይሰጣል።ደካርት ብዙ ጽሁፍ ቢያቀርብም፣ ባሁኑም ሆነ ቀደምት ክፍለ ዘመናት ስሙ ገኖ የሚታወቀው በአንዲት ጥቅስ ነው፣ እሱዋም «ስለማስብ፣ አለሁ»፣ በላቲኑ «Cogito ergo sum» ተብሎ ይታወቃል።

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ

ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (ቻይንኛ፦ 南京大学 /ናንጂንግ ዳሥዌ/) በናንጂንግ፣ ቻይና የሚገኝ ጥንታዊ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው።

መጀመርያው በ250 ዓም ናንጂንግ ታይሥዌ ተብሎ እንደ ኮንግ-ፉጸ ተቋም ተመሠረተ፣ ስለዚህ ለ1,760 ዓመት ክፍት ሆኗል። ይህ ከ571 ዓም በኋላ ናንጂንግ ዋና ከተማ በሆነባቸው ጊዜዎች ናንጂንግ ጐዝርጅየን ሆነ። ዋና ከተማ ባልሆነባቸው ጊዜዎች ደግሞ ናንጂንግ ሹዩዋን (ናንጂንግ አካዳሚ) ይባል ነበር።

በ1894 ዓም ናንጂንግ ሹዩዋን «ዘመናዊ» ትምህርት ቤት (በጃፓናዊ አራያ) ተደረገ። ከዚያ ጀምሮ የሚከተሉት ስያሜዎች ነበሩት፦ ሳንጅየንግ ልምዳዊ ኮሌጅ (1894 ዓም)፣ ልየንግጅየን ልምዳዊ ኮሌጅ (1898 ዓም)፣ ናንጁንግ ከፍተኛ ልምዳዊ ትምህርት ቤት (1907 ዓም)፤ ብሔራዊ ደቡብ-ምሥራቃዊ ዩኒቨርሲቲ (1913 ዓም)፣ ብሔራዊ ናንጂንግ ቹንግሻን ዩኒቨርሲቲ (1919 ዓም)፣ ጅየንግሱ ዩኒቨርሲቲ፣ ብሔራዊ መካከለኛ ዩኒቨርሲቲ (1920 ዓም)፣ ብሔራዊ ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (1941 ዓም)፣ በመጨረሻም ናንጂንግ ዩኒቨርሲቲ (1942 ዓም)።

መጀመርያው ተቋም «የኮን-ፉጸ ስድስቱ ሞያዎች» አስተማረ። 1) የኮንግፉጸ ሥርአተ ቅዳሴ፣ 2) የቻይና ባህላዊ ሙዚቃ፣ 3) ቀስትን ማስፈንጠር፣ 4) ሰረገላ መንዳት፣ 5) የቁም ጽሕፈት፣ 6) ሥነ ቁጥር ነበሩ።

በ462 ዓም ጥናቶቹም፦ 1) ሥነ ጽሑፍ፣ 2) ታሪክ፣ 3) የኮንግ-ፉጸ ትምህርት፣ ፬) የዳዊስም ትምህርት፣ ፭) የዪንግ-ያንግ ጥናት (የተፈጥሮ ጥናት) ነበሩ።

በዚያ ዘመን ታዋቂ ከሆኑት ተማሮችና መምህሮች መካከል፦

ጌ ሆንግ (275-335 ዓም) - የዳዊስምና የአልኬሚ ጸሐፊ

ዋንግ ሺጂ (295-353 ዓም) - የቁም ጽሕፈት ሊቅ

ንጉሥ ጋው ዘደቡብ ጪ (419-474 ዓም) - የደቡብ ጪ መስራች ሆነ

ዙ ቾንግዢ (421-492 ዓም) - የሂሣብ ተመራማሪ

ዦንግ ሮንግ (460-510 ዓም) - የሥነ ግጥም ደራሲበ1373 ዓም 10,000 ተማሮች ነበሩ። ጥናቶቹም፦ የኮንግ-ፉጸ ስነ ጽሑፍ፣ ታሪክ፣ ሥነ-ጽሑፍ፣ ሥነ ቁጥር፣ ሕግ፣ የቁም ጽሕፈት፣ ፈረሰኝነት፣ ቀስትን ማስፈንጠር፣ ወዘተርፈ. ነበሩ። ተቋሙ በ1400 ዓም ዮንግሌ መዝገበ ዕውቀት አሳተመ።

ዉ ቸንግኤን (1492-1574 ዓም) - ባለቅኔ

ዠንግ ቸንጎንግ (1616-1654 ዓም) የታይዋን ወራሪበዚሁ ዘመን ተማሮች ነበሩ።

በ1913 ዓም የነበሩት ክፍሎች፦ ሥነ ጥበብ፣ ትምህርት፣ ግብርና፣ ምህንድስናና ንግድ ነበሩ። ዛሬም በጣም ብዙ ዘርፎች ሲኖሩ ከአገሩ ፪ኛው ዋና ዩኒቨርሲቲ ነው። በኬሚስትሪ ዘርፍ ደግሞ በክቡርነት ከአለም ፫ኛ ነው። 14,000 ያህል ተማሮች አሉበት።

አማርኛ ኖርሽክ

ሚኪ

ቃል በቃል የሆነው ትርጉም እንዲህ ይታያል።

አምራፌል

አምራፌል በኦሪት ዘፍጥረት 14 መሠረት በአብራም (አብርሃም) ዘመን የገዛ የሰናዖር ንጉሥ ይባላል።

በሲዲም ሸለቆ (በጨው ባሕር አጠገብ) የተገኙት 5 ከተሞች የኤላም ንጉሥ የኮሎዶጎምር ተገዦች ሆነው

ከዐመጹበት በኋላ፥ አምራፌል ከኮሎዶጎምር 3 ጦር ጓደኞች መካከል ሆኖ አብረው በዘመቻ ላይ ሔዱ። በመጀመርያ «ራፋይምን በአስጣሮት ቃርናይም፥ ዙዚምንም በሃም፥ ኤሚምንም በሴዊ ቂርያታይም መቱ፤ የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ። ተመልሰውም ቃዴስ ወደ ተባለች ወደ ዓይንሚስፓጥ መጡ፤ የአማሌቅን አገር ሁሉና ደግሞ በሐሴሶን ታማር የነበረውን አሞራውያንን መቱ» (ቁ. 5-7)። እነኚህ በሲዲም ሸለቆ ዙሪያ የነበሩት አገሮች ናቸው።

ከዚያ የሲዲም ሸለቆ 5 አመጻኛ ነገስታት ለውግያ ተሠለፉ። እነርሱም የሰዶም ንጉሥ ባላ፥ የገሞራ ንጉሥ ብርሳ፥ የአዳማ ንጉሥ ሰነአብ፥ የሰቦይም ንጉሥ ሰሜበር እና «ዞዓር የተባለች የቤላ» ንጉሥ ነበሩ። 4 ነገሥታት በ5 ነገሥታት ላይ ስለ ሆነ፣ ይህ ብዙ ጊዜ «የነገሥታት ጦርነት» ተብሏል።

በውግያው የሲዲም ሸለቆ ሓያላት ተበተኑና የነኮሎዶጎምር ሠራዊት ከብታቸውንና ብዙ ምርከኞች ዘርፈው ሔዱ። ከነዚህም ውስጥ የአብራም ዘመድ የሆነው ሎጥ ተማረከ።

ሰለዚህ አብራም በሰማው ጊዜ፣ 318 ሎሌዎቹን አሠለፈና እስከ ዳን (በስሜን ከነዓን) ድረስ ተከተላቸው። አገኝቷቸው መታቸውና አብራም እነኮሎዶጎምርን አሸንፎ እስከ ሖባ ድረስ (በደማስቆ ሶርያ አካባቢ) አሳደዳቸው።

በመጽሐፈ ኩፋሌ ይህ ታሪክ በአጭሩ ሲሰጥ፣ የሰናዖር ንጉሥ ስም አማልፋል ተጽፎ ይታያል (11:33)።

እድሜ

እድሜ ትክክለኛ የአማርኛ አፃፃፉ ዕድሜ ሲሆን የአንድን ነገር ወይም የሆን ክንውን ከተፈፀመ የሚያስቆጥረው ጊዜ ነው።

እጀን አሳልፎ መስጥት

እጀን አሳልፎ መስጥት ማለት በወንጀል የሚፈልግ ስውን ኣሳለፎ ምሰጥት ነው።

ውክፔዲያ

ውክፔዲያ የባለ ብዙ ቋንቋ የተሟላ ትክክለኛና ነጻ መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ነው። ማንኛውም ሰው ለውክፔዲያ መጻፍ ይችላል። ውክፔዲያ፣ ውክሚዲያ የተባለ ገብረ-ሰናይ ድርጅት ከሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች አንዱ ነው። ወደ 272 በሚጠጉ የተለያዩ ቋንቋዎች ፅሁፎች አሉት። ውክፔዲያ በኢንተርኔት ከሚገኙ ታዋቂ መዛግብተ ዕውቀት አንዱ ነው።

ውክፔዲያ ድረ-ገፅን መሰረት ያደረገና ማንም ሰው በቀላሉ እንዲያስተካክለው ተደረጎ የተዘጋጀ፣ በብዙ ቋንቋዎች የሚቀርብ ነጻ የኢንተርኔት መዝገበ እውቀት ወይም ኢንሳይክሎፒድያ ነው። ውክፔዲያ የሚለውን ስያሜ ያገኘው “ዊኪ” (ትርጉሙ ፈጣን ማለት ነው) የሚለውን ቃል ከሀዋይኛ ቋንቋ በመወሰድና “ኢንሳይክሎፒድያ” ከሚልው የእንግሊዘኛ ቃል ጋር በማዳቀል ሲሆን እያንዳንዱ የውክፔዲያ ገጽ እራሱ ከሚይዘው መረጃ በተጨማሪ አንባቢን ይበልጥ ግነዛቤ ለማስጨበጥ ከሚረዱ ሌሎች ተዣማጅ ገፆች ጋር ያለውን የትስስር መረጃም በተጨማሪነት አካቶ የያዘ ነው።

ውክፔዲያ የተመዘገበ (የሚታወቅ) አድራሻ ሳይኖራቸው ኢንተርኔት ላይ ያለምንም ክፍያ በፈቃደኝነት የሚጽፉ የበርካታ ግለሰቦች የጋራ የትብብር ውጤት ነው። ስለሆነም ከአንዳንድ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ገደብ ከተጣለባቸው ገጾች በስተቀር ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚና ፈቃደኛ የሆነ ሰው፤ በብዕር ስም፣ ትክለኛ ስምን በመጠቀም ወይም ደግሞ ያለምንም ስምና አድራሻ፣ ዊክፔዲያ ላይ የፈለገውን ሀሳብ የማስፈርና አስተዋጾ የማድረግ አሊያም ቀድሞ በሰፈረ ጽሁፍ ላይ ተጨማሪ መረጃን የማካታት፣ ስህተትን የማረምና የማስተካከል ፈቃድ ተሰጥቶታል።ውክፔዲያ ከተመሰረተበት ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለና በብዛት ከሚጎበኙና ኢንተርኔት ላይ ከሚገኙ በረካታ የማጣቀሻ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ሲሆን 2011 እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር ብቻ ከ400 ሚሊዎን በላይ አዳዲስ ጎብኝዎች ድረገጹን እንደጎበኙት ኮም ስኮር ያካሄደው የጥናተ ዘገባ ያመለክታል። ውክፔዲያ ከ82,000 በላይ አርታኢዎች፣ ከ270 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያጠናቀሯቸውን ከ19,000,000 በላይ የሚሆኑ መጣጥፎችን አካቶ የያዘ ድረ-ገጽ ነው። ውክፔዲያ በአሁኑ ጊዜ 3,874,529 የእንግሊዘኛ መጣጥፎችን የያዘ ሲሆን በየቀኑ ከመቶ ሺህ በላይ ጎብኝዎች እንደሚጎበኙትም ይገመታል። በተጨማሪም በተለያዬ የአለም ክፍል የሚኖሩ ግለሰቦች በሚያደርጉት የጋራ አስተዋጾ በየቀኑ ከአስር ሺህ በላይ መጣጥፎች የተለያዩ ማስተካከያዎች የሚደረግባቸው ሲሆን ሌሎች በሺዎች የሞቆጠሩ አዳዲስ መጣጥፎች ደግሞ ውክፔዲያን በየቀኑ ይቀላቀላሉ።ምንም እንኳን መሰረታዊ የውክፔዲያ መርሆች የሚባሉት አምስት ቢሆኑም ይህንኑ መዝገበ-ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ይበልጥ ለማሻሻልና ለማጎልበት የሚያግዙ ሌሎች በርካታ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በውክፔዲያ ማህበረሰብ ተቀርጸው ተግባር ላይ የዋሉ ሲሆን ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መመሪያዎችና ደንቦች አስተዋጾ ማድረግ ካልጀመረ በስተቀር ማንኛውም ሰው የማወቅ ግደታ የለበትም።በሌላ በኩል፣ ውክፔዲያ አንድ ሰው ካለው የሙያ ችሎታ ይልቅ ለሚያበረክተው አስተዋፆ ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል፣ ባህልና መነሻ (ዳራ) የሚገኝ ማንኛውም ሰው የውክፔዲያ አስገዳጅ ፖሊሲዎችን አሟልቶ እስከተገኘ ድረስ፣ ውክፔዲያ ላይ የፈለገውን መጣጥፍ እንዳንድስ የመጨመር አሊያም ማንኛውም ውክፔዲያ ላይ የሚገኝ ሌላ ጽሑፍ፣ ማጣቀሻና ምስል የማየት የማሻሻልና የማረም አንዳደም ሙሉ ለሙሉ የመለዎጥና ፈቃድ አለው። በመሆኑም ውክፔዲያ በተለያዩ አስተዋጾ አድራጎዎች በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግበት እንደመሆኑ መጠን፣ አድስ ከሚካተቱት መጣጥፎች ይልቅ ቀደም ሲል በድረ ገጹ የተካተቱ መጣጥፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታረሙና እየተሻሻሉ የሚሄዱ በመሆናቸው የተሻለ የሃሳብ ጥራት፣ የመረጃ ሚዛናዊነትና ሙሉዕነት እንደሚኖራቸው ይታመናል።

የኖህ መርከብ

የኖህ መርከብ ወይም ሐመር (ዕብራይስጥ፦ תיבת נח /ተይባት ኖዋሕ/፤ ዓረብኛ፦ سفينة نوح /ሣፊና ኑህ/) በመጽሐፍ ቅዱስ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 6—9)፣ በቁርዓንም (ሱራ 11 እና 71)፣ እንዲሁም በሌሎች «አብርሐማዊ» የተባሉ ሃይማኖቶች ጽሑፍ ዘንድ፤ ኖህን፣ ቤተሠቡንም፣ ከዓለም እንስሶችም ምሳሌዎች ከማየ አይኅ ለማዳን የተሠራ ታላቅ መርከብ ነበረች።

በዘፍጥረት የተገኘው መሠረታዊ ታሪክ እንደሚለው፣ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ክፋት አዝኖ ብልሹውን ዓለም ለማጥፋት ወስኖ ነበር። ሆኖም ኖህ ጻድቅ ሆኖ እራሱን፣ ቤተሠቡንም የመሬት እንስሶችንና አዕዋፍንም የምታድን መርከብ እንዲገነባ አዘዘው። የጥፋት ውኃ ከዚያ ምድሩን አጥፍቶ ውሆቹ መልሰው የብስ እንደገና ታየና መርከቢቱ በአራራት ተራሮች ላይ ዐረፈች። በመጨረሻ እግዚአብሔር ከኖህና ተወላጆቹ ጋራ ቃል ኪዳን ገባ።

ለዚህ መተረክ ብዙ ጊዜ በአብርሃማዊ ሃይማኖቶቹ በኩል ሰፊ ዝርዝሮች ተጨምረዋል። እነዚህ ዝርዝሮች ከሥነ-መለኮታዊ ትርጉሞች ጀምሮ ለተግባራዊ ጉዳዮች የሆኑ መላምታዊ ፍቾች እስከሚነኩ ድረስ ሊሆኑ ይችላሉ። በ19ኛው ክፍለ-ዘመን ላይ፣ በተለይ በምዕራብ ዓለም በብዙዎቹ የሳይንስና የሥነ ጽሑፍ ሊቃውንት አስተያየት፣ መተራረኩ አፈ ታሪክ ብቻ እንጂ በዕውኑ አይሆንም በማለት ተጠራጠሩ። ዳሩ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛነት የሚያምኑት ሰዎች እስካሁን አይነተኛና ዕውነተኛ ታሪክ መሆኑን ቆጥረውታልና እስከዚህ ቀን ድረስ ለመርከቢቱ ማረፊያ ተራራ አንዳንድ ፍለጋ ሲካሄድ ነው።

በሌሎች ቋንቋዎች

This page is based on a Wikipedia article written by authors (here).
Text is available under the CC BY-SA 3.0 license; additional terms may apply.
Images, videos and audio are available under their respective licenses.